Get Mystery Box with random crypto!

ወርቃማ ንግግሮች

የቴሌግራም ቻናል አርማ golden_speech — ወርቃማ ንግግሮች
የቴሌግራም ቻናል አርማ golden_speech — ወርቃማ ንግግሮች
የሰርጥ አድራሻ: @golden_speech
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.15K
የሰርጥ መግለጫ

ሰው የለበስክ ሰው እንጂ ልብስ የለበስክ ሰው አትሁን.. ሰውነት የአለም ምርጡ ጌጥህ እሱ ነውና።
አስተያየት እንቀበላለን.. @Golden_SpeechBot
https://youtube.com/channel/UCgP-E0miz3BhJ0YAGJ2zCHg

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-02 02:16:12
የተቀመጥኩበት የዛፍ ቅርንጫፍ ከተሰበረ ፣ የያዝኩት ገመድ ከተበጠሰ በቃ ምንም ተስፋ የለኝም አትበል። ራስህን ሙሉ በሙሉ ጥለህ ሰዉን አትደገፍ። ቅርንጫፉ ቢሰበር ከአላህ በታች በክንፍህ ተማመን። ገመዱ ቢበጠስ አሁንም አላህን አጥብቀህ ያዝ።
የምትጠብቀው ሥራ፣ የምታልመው ትዳር፣ የምትጓጓለት መልካም ዜና ጫፍ ደርሶ ቢሰናከል  እንዳትሰበር ካሁኑ ጠንከር !!።
ዱንያ በድንገተኛ ትዕይንቶች የተሞላች ናትና ለሁሉም ዓይነት ሁነት መዘጋጀት መልካም  ነው።

መሳአል ኸይር

Abx
3.0K views23:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 00:43:00
አንድ ሰውዬ በኬኒያ ሀገር ለመታከም ወደ መንግስት ሆስፒታል አቅንቷ 'X-ray' ከተነሳ በኋላ ፣ በጥሩ ጤንነት ላይ ያለች በረሮ ሳምባው ውስጥ እንዳለች ይነገረዋል ።

ወደ ሲንጋፖር ሄዶም መታከም እንዳለበት ይነግሩታል ።
ታማሚውም ወደ ሲንጋፖር ሄዶ ሲታይ ፣ የታየው በረሮ ሳምባው ውስጥ ሳይሆን 'X-ray' ከሚያነሳው ማሽን ውስጥ የተገኘ መሆኑን ያስረዱታል ።

ብዙ ግዜ የምንያበትን ነገር ሳናፀዳ አሊያም የምንመለከትበት መስታወት ሳናነፃ የሌላውን እድፍ ለመናገር እንሮጣለን ፣ እድፉ እኛ ምንለው ነገር ሳይሆን አስተሳሰባችን ወይም የምናይበት መነፅር ነው !
ሼር
2.5K views21:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 20:29:02
አላህ ከምትፈልገው በላይ ያማረ ምኞቶችን ይፈጥርልሃል ፣ የትናቱ ማጣትህ በዛሬው ማግኘትህ የትናንቱ ምስቅልቅሎች በዛሬው ስጦታው ትናንትን ያስረሳሃል። የመከራን ገፅታዎች በፊትህ ላይ ደምስሶ የከበደህን የነፍስህን ጫና አቅልሎ የድሎትን ብርሃን ያበራልሃል ሁሌም የሱ ብርሃን አይጠፋም ነፍስህ ከስጋህ እስከምትለይ የሱ የእዝነት ብርሃን ባይኖር ከስረን በቀረን ነበር።

~ ስለዚህም ነገሮቻችሁን ሁሉ ለአላህ አደራ ስጡ።
2.5K views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 18:20:51
አሏህ  ሆይ !
፨ ወዳንተ ካልሆነ ልመናም ጩኸት ነው!
፨ ባንተ ላይ ካልሆነ ተስፋም ባዶነት ነው!
፨ ስላንተ ካልሆነ ንግግርም ውሸት ነው!
፨ ካንተ ጋር ካልሆነ  ንግድም ኪሣራ ነው!
፨ ስለ ክብርህ ካልሆነ ፍቅርም እንግልት ነው!
፨ በመንገድህ ካልሆነ ሞትም መከራ ነው!!

****
፨ አላህ ሲቀር ሁሉም ነገር ጠፊ ነው ።
፨ አኺራ ሲቀር ሁሉም አገር አላፊ ነው  ።
፨ ጀነት ሲቀር ሁሉም ድሎት ረጋፊ ነው  ።
፨ ጀሀነም ሲቀር ሁሉም መከራ ጤና ነው  ።

ያ አሏህ!!
ያ ረሕማን!
ያዘልጀላሊ ወልኢክራም!

ይህ ዉዴታህንና ቅበላህን ከጅለው የተነሱ ባሮችህ ድምፅ ነው።

ወደንሃል ዉደደን፤
ለመንህ ስማን፤
ተማፀንህ ተቀበለን፤
2.6K views15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 01:21:15 #እግረ_መንገድ ①

ኢማሙ ገዛሊይ (ቀደሰላሁ ሲረሁ) በኢሕያቸው ላይ ነፍሲያን በብርቱ ስለ መያዝ ካነሱት ዘገባዎች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል። አንድ ጊዜ አንጋፋው ዐብደላህ ኢብኑ ሙባረክ የተጠቀለለ እንጨት ተሸክመው ሰዎች አገኟቸውና በድንጋጤ እርስዎ ያልዎት ልጆች እኮ ለዚህ ይበቃሉ አሏቸው። አዎን በቂ ናቸው ግና እኔም ነፍሴ ይህን ትቃወም ይሁን የሚለውን ለመሞከር ብዬ ነው ብለው መለሱላቸው።

ዐዋቂዎች፣ ተናጋሪዎች፣ ዝነኞች ማንኛውም ሰዎች የሚያደርጉትን ነገር ለካሜራ ፍጆታ ሳይኾ ተናንሰው ማድረግ አለባቸው። ገበያ መካከል ለቤቱ ፍጆታ ሲተራመስ እንደማየት ማለት ነው። ሁሉንም ነገር በሰው መወከል ላይኖርብህ ይችላል ከሕዝብ ጋር መመሳሰል ለነፍሲያ የሚጠቅማት ልምምድ ነው።

ወደ እግረ መንገዱ ልመለስ

ጥዋት አንድ ሰው አገኘሁና አንድ ሐዲስ ጣል አደረግኩለት " ኦውው እኚህን ሸይኽ ከተማ ውስጥ ያስተዋውቋቸው እኔ ነኝ" አለኝ ሳቄ መጣና በል አታውቃቸውም እርሳቸውን ብታውቃቸው ኖሮ እንዲህ አትልም እርሳቸው ያስተማሩት ከነፍስ መጥፋት እንጂ በነፍስ መኩራትን አይደለም ብዬው ተሳስቀን አለፍን።

ወደ ትምሕርት እንቀይረው ዐሊሞች ሲመክሩን የዐዋቂ ፈተና ከማዳመጥ በላይ ማወራትን መውደዱ ነው ይላሉ። (ዙህድ ኢብኑ ሙባረክ ላይ ያለ ምንጭ ነው።)

ያወቅናቸው ነገሮች ኹሉ ሊሰጡን የሚገባው ትህትናን ነው። የምናውቀውን ነገር ሰው ቢነግረን እንኳን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳደመጠ በትዕግስት ማድመጥ ነፍሲያን ለመቆጣጠር አጋዥ ነው።

የሰዎች ስም ሲጠራ በማይመለከተህ ቦታና ኹኔታ የምትዞር ከሆነ፣ ሰዎችን በመንገድ ሲሄዱ አስቁመህ ወዴት ነው የምትሄዱት ማለትህ ከተዝኪያ ችግር የሚመነጭ ነው ብለውም የሚመክሩ አልሉ።

እናም በመጨረሻ ምን ተማርክ ብትሉኝ ማወቅ ዓላማው ፍራቻና መተናነስ እንደሆነ ነው። ሳናስበው መታወቅና መደነቅ ከመጣ ደግሞ ነፍስ ደስ ደስ እንዳይላት ዘንድ ዝቅ ማለት ነው። ኸይር ሥራን መቅበር ነው። ኸይር እያስታወሱ መኖር ኸይርን እንደመፋቅ ነው። ሰዎችን ዝም ብሎ ማወደስ ደግሞ የማረድ ያህል ነው። (ሐዲስ ነው) ስለዚህ? ነገሮችን ወደአላህ ማስጠጋትና ማመሰገን ከሁሉም ይልቃል።

አላህ ወደ ውስጥ ያሳየና
360 views22:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 23:21:42
እህትና ወንድሞቼ!
የተምር ቁራጭ ከእሳት ካራቀን…
ምፅዋት የኃያሉን ጌታ ቁጣ ካጠፋ…
"ሱብሐነላህ ወቢሐምዲሂ ሱብሐነላሂል—ዐዚም" የሚለው ጥቂት ቃል ሚዛናችንን ካከበደ…
የአንድ ቀን ጾም ሰባ ዓመት በሚያስኬድ ርቀት ያህል ከእሳት ካራቀን…
ዉዱእ ስናደርግ ኃጢኣታችን የሚረግፍ ከሆነ…
ጀነትን ሩቅ ናት ብለን ለምን እናስባለን?!
:
አሽሀዱ አል—ላኢላሃ ኢል—ለላህ አስተግፊሩላህ ነስአሉከል ጀነተ ወነዑዙ ቢከ ሚነን—ናር
852 views20:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 07:00:47 ታላቁ ዐሊም እና የአቡ ሐኒፋ ሸይኽ ሐማድ ኢብኑ ሰለማ እንዲህ ይላሉ:-

"በዕለተ ቂያማ ከአላህ - ሱብሐነሁ ወተዐላ- እና ከወላጆቼ ማን እንዲተሳሰብህ ትፈልጋለህ ብባል ከወላጆቼ በላይ  የሚያዝንልኝን አላህ እመርጣለሁኝ ! "

    /አቡኑዐይም ፣ ሒልየቱ አል አውሊያእ /
398 views04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:47:16 እንኳን ለተከበረው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሰን አደረሳችሁ በአሉ የሰለም የፍቅር ይሁንል

በዓሉን ስናሳልፈው የቲሞችን አቅመ ደካሞችን እንዘይራቸው እንዳብሳቸው ከሀራም ተቆጥበን በከይር ነገር እናሳልፈው።

~ አመት አመት ይደጋገምብን የከርሞ ሰው ይበለን።

~ መልካም በዓል ይሁንልን

~ from Ibnu mohammed
522 viewsedited  17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 21:26:48
ሰልማን አል-ዐውዳ ሚስቱን በመኪና አደጋ በማጣቱ ከሐዘን ጋር ጎጆ መቀለሱን የሰማችው የባለቤቱ ጓደኛ ብዕርን ከወረቀት ጋር አዋህዳ ደብዳቤን ላከችለት
Mahi Mahisho

ንግግሯን እንዲህ ትጀምራለች
"ከሚስትህ ጓደኞች መካከል አንዷ ነኝ የውድ ሚስትህ የኡሙ ሙዓዝ ሞት በእጅጉ አሳዝኖኛል። ያለፍክበትን ሀዘንም ሰምቻለሁ.. ምናልባት ያስታግስህ ዘንድ እነሆ ታሪኬን ፅፌልሀለው። ቀልብህን ከፍተህ አንብበው ...

ስለ ሐዘን የተነገረ ስለ ህመም የተተረከ የመጀመሪው ታሪክ አይደለም። እንደ እኔ የሚወዱትን ሰው አጥተው የሚሰቃዩ፣ ወላጅ ወንድሞቻቸውን ተነጥቀው የሚኖሩ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ።

በሂጅሪያ አቆጣጠር በ1431 የረመዳን 27ኛው ቀን ላይ ይጀምራል። በአንድ መኪና ተሳፍረን ዑምራ ለማድረግ ወደተከበረው የአላህ ቤት ልንሄድ ከቤተሰቦቼ ጋር ወስነናል። ወንድሞቼ መኪናቸው ቤት አቁመው መጡ። ስምንት ነበርን.. ወላጆቼ፣ እህቶቼና ወንድሞቼ ሙሉ ቤተሰቡ አብሮን አለ። አባቴ እናቴን ጋቢና ከጎኑ አስቀምጦ መኪናውን ያሽከረክራል።

ሁላችንም ቁርኣንን ይዘናል። ጉዞው ረጅም ሰዓትን ስለሚፈጅ መኪና ውስጥ አኽትመን ልንወርድ አስበናል። ሐረም እስክንደርስ በዚክርና በዱዓ ልናሳልፍ ተስማምተናል። እህቴ እየቀራች ታለቅሳለች። ሌላኛዋም የዕንባ ጎርፍን ከዓይኗ ታፈልቃለች። ተራ በተራ እያየኋቸው
ዕንባቸው የሚፈሰው ለምን እንደሆነ ጠየቅኳቸው..?
"ቁርአንን ሳነብ የአላህ ድምፅ ለኔ ቅርብ ሆኖ አገኘዋለሁ" አለችኝ አንዷ።

እኔም ንግግሯን ሰምቼ በጥልቅ ማስተንተን መቅራቴን ቀጠልኩ። አባቴ እየነዳ ዕንቅልፍ አሸለበው። መኪናው ከተራራው አናት ላይ መንከባለል ጀመረ። ጥልቀት ወደሆነ ሸለቆ እየተንከባለለ ይገለባብጠን ያዘ። ከዛፍ ጋር ተላትሜ ቀረሁ የቀሩት ቤተሰቦቼ ሸለቆው ውስጥ ወደቁ።
የመግሪብ ሰላት አዛን እያለ ነበር። አላፈጠርንም ብዙ ደም ከሰውነቴ በመፍሰሱ ራሴን ሳትኩ። አስታውሳለሁ ስነቃ ባባ እያልኩ መጮኽ ጀመርኩ። እየተንፏቀቅኩ መፈለጉን ተያያዝኩት።

የአካል ስብራትና ጉዳት ቢደርስብኝም ድንጋጤው ህመሜን አስረስቶ በሆዴ እያንከባለለ እነሱ ዘንድ አደረሰኝ። እናቴን መጎተት ጀመርኩ። ሞታ አገኘኋት። አባያዋ ሰውነቷ ላይ እንደ ከፈን ተጠቅልሏል። ከሰውነት አካሏ አመልካች ጣቷ ብቻ ነበር የሚታየው። ሁሉም ተሰትሯል። እህቶቼን ሰውነታቸው ተገልጧል። ልሸፍናቸው ሞከርኩ.. ወደማይቀረው አለም ተሸጋግረው አገኘኋቸው። አመልካች ጣታቸው ለሸሃዳ እንደተቀሰረ ነው። ወንድሞቼም ሞተዋል። እንደምንም እየተሳብኩ እነሱንም እየሳብኩ አንድ ቦታ ሰበሰብኳቸው።

የማታዋ ጨረቃ ምሽቱን አድምቃዋለች። የውሻ ድምፅና ጨለማው ከአየሩ ጋር ተዋህዷል። ወደመኪናው ተመልሼ በእንፉቅቅ አባቴ ጋር ደረስኩ። በህይወት አለ። መላ ሰውነቱ እየደማ ነው። ወደ ደረቴ አስጠግቼ አቀፍኩት። "እዚህ ረጅም ሰዓት አትቆዪ.. ወደ ተራራው ጫፍ ወደ መንገዱ ሂጂና ሰው እንዲረዳሽ ተጣሪ ወንድሞችሽን አድኚ" አለኝ በተቆራረጠ ድምፅ።

የውሻዎቹን ድምፅና ጨለማውን መፍራቴን ነገርኩት። ጭኑን ተደግፌ "እየደማሁ ነው መንቀሳቀስ ከብዶኛል" አልኩት። ወደ ደረቱ አስጠጋኝና አደራ ዲንሽ ላይ አደራ እያለ ሸሃዳ ይዞ ወደማይቀረው ዓለም ተሸጋገረ። ብቻዬን ቀረሁ።

እያለቀስኩ ዱዓና ዚክር ላይ ተጠምጄ ራሴን ሳትኩ። አደጋው ከተፈጠረ ሁለተኛውን ቀን ይዟል። መኪናው ሲወድቅ ማንም አላየንም ነበርና ሊረዳን የመጣ ሰው አላገኘንም። በሶስተኛው ቀን አንድ እረኛ ከብቶቹን አሰማርቶ ሲንጎራደድ ከርቀት ተመለከተን። ለጥበቃዎች አሳውቆ በሄሊኮፕተር የታገዘ የነፍስ አድን ቡድን ወደሆስፒታል ይዞን አቀና።

አምስት ወራት ሙሉ ኮማ ውስጥ ቆየሁ። ስነቃ የሆነውን ነገር አስታወስኩ። ቅዠትና ህልም መስሎ ታየኝ። አባቴን እናቴን ወንድሞቼንና እህቶቼን በአንድ ጀንበር አጣሁ። ክስተተሀ ምናል ባልነቃሁ እኔም እነሱን በተከተልኩ አስባለኝ። ሁለት አመታት በሀገረ ካናዳ ጭንቅላቴ፣ አንገቴ፣ ጀርባዬና ዳሌዬ የደረሰባቸውን ከባድ ስብራት እየታከምኩ ህክምና ላይ አሳለፍኩ። በደም መፍሰስ ምክንያት እናት የመሆንን በረከት አጣሁ። ብዙ ሙከራዎች በዶክተሮች ቢደረጉም አልተሳኩም። ሕይወቴን ወይም ልጆች የማግኘት ፀጋዬን ሊያሳጣኝ የሚችለው ቀዶ ጥገና ምርጫው ከባድ ነበር ግን ሆነ።

አሁን ደህና ነኝ አልሀምዱሊላህ። ወደ ስራዬ ተመልሻለሁ ..ወደ ሪያድ ተዛውሬ ከአዲሱ ህይወቴ ጋር መኖር ጀምሬያለሁ .... ያሸይኽ... በሕይወትህ ውድ የሆነውን ሰው ያጣኸው አንተ ብቻ እንዳልሆንክ እንድታውቅ ታሪኬን አካፈልኩህ።

የእህቶቼ ሰርግ ሁለት ሳምንት ነበር የቀረው። ከመሞሸራቸው በፊት ዑምራ ማድረግ ፈልገን ወደ መካ በማቅናት ላይ ሳለን የአላህ ውሳኔ ቀደመ። አሁንም የሰርግ ልብሳቸው እኔ ጋር ነው። እስክሞት ድረስም አብሮኝ ይቆያል" በማለት ታሪኳን ትቋጫለች።
318 views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 05:21:29 #ዑዝላ

ዑዝላ ማለት መገለል ማለት የብዙዎችን አዕምሮ በተለያዩ ነገሮች እንዲወጠርና አላህን አብዝቶ ከማውሳት እንዲዘናጉ ከሚያደርጉ ማንኛውም ቦታዎች ራስን ማግለል ማለት ነው። አላህ ዘንድ ተወዳጅ ሥፍራ ማለት መስጂድ ነው። ይህ የኾነበት ምክንያት አላህ ብቻ በብዛት ስለሚጠራበትና በጸጥታው የተነሳ ነው። መስጂዶች የአማኝን ሰላም ካስጠበቁ፣ ወደ አላህና መልእክተኛው ጋር ሰዎችን ለማገናኘት የሚጣርባቸው ከሆነ የመስጂድ ግብ ተሳክቷል። የተጠላ ሥፍራ ማለት ደግሞ የገበያ ቦታዎች ናቸው። የገበያ ቦታዎች ብዙ ሰው የሚታለልባቸው፣ ወሬ የሚበዛባቸውና ወንጀሎች የሚፈጸምባቸው ቦታዎች ናቸው። በገበያ ሥፍራዎች ቀድሞ ማልዶ መገኘትም ሆነ ዘግይቶ አምሽቶ መውጣት ይጠላል። ምክንያቱ ደግሞ እርኩስ መናፍስት በቦታው ላይ ስለሚገለሉ ነው። የሱቅ ምሳሌው ግርግርና ጥቅም አልባ ወሬዎች የሚነዙበትም ሥፍራ ነው። ቦታው ላይ ሥራ የሌለው ሰው ያለ ዓላማ ቦታው ላይ አይገኝ እንደማለት ነው።

ከጾም ዓላማዎች መካከል ሰዎች በቀጥታ ከማይመለከታቸው ሐሳብ ራሳቸው ማቀብ እንዲችሉ ማድረግ ነው። ሌላው ቢቀር ጠቃሚ የሚመሰሉ አጀንዳዎች ውስጥ ሰዎች እንዲወጠሩ ይደረጋል። ይህ ደግሞ ሰ*ይጣናዊ ዓላማ ነው። ይህ ዓላማ ሰዎች ነፍሳቸውን የተሻለ አድርገው እንዲመለከቱ በማድረግ በከፍተኛ ኹኔታ ከትክክለኛው ኢማን የሚሸሹበትን ወጥመድ የሚዘረጋበት ነው።

መውላና ሸምሰ ተብሪዝ (ቀደሰላሁ ሲረሁ) እንዲህ ይላሉ፦

« ለልብህ መስተካከል ከሰዎች በ‘መገለል’ ውስጥ ታገዝ፤ ግርግር ልቦናን ያበላሻልና፤ ከአላህ ጋር ማውራት አብዛ ስሜትህን ሁሉ ለርሱ አቅርብ!»

ስለዚህም ሲባል ልባችንን ከመበላሸት ለመጠበቅ አላህን አብዝቶ ለማውሳት ያመች ዘንድ ሰዎች ሁሉ ግር ከሚሉበት ነገር እንነጠል እላለሁ።

አላህ ያስረዳና
341 views02:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ