2023-06-25 02:54:10
#ከቂያማ_ምልክቶች መካከል፦
1/ ዝሙት ይስፋፋል
2/ ወንዶች ሀር ይለብሳሉ
3/ ሙዚቃ እንደሚፈቀድ ይነገራል
4/ ሴቶች ዘፋኞች በአጫዋችነት ይያዛሉ
5/ መጥፎ ቃላቶችን መለዋወጥ ይበዛል
6/ ዝምድናን መቁረጥ በስፋት ይስተዋላል
7/ ታማኝ ሰውን እንደ ከዳተኛ መቁጠርና መወንጀል
8/ ከዳተኛን ማገዝና ማቅረብ
9/ ድንገተኛ ሞት መከሰት
10/ መስጅድን እንደ መተላለፊያ መንገድ መጠቀም
11/ ጥሪያቸው ወይም ተልእኮአቸው ተመሳሳይ የሆነ ሁለት ቡድኖች ይፋ ጦር ይማዘዛሉ (የአልይና የሙአውያ ውጊያን ያመለክታሉ)
12/ የዘመን መቀራረብ ወይም የጊዜ መፍጠን (በረካ ማጣት)
13/ ፈተናዎች ይደራርሳሉ፣ ተንኮል ይስፋፋል
14/ ኢልም ከህፃናት ይፈለጋል
15/ የመሬት መንቀጥቀጥ
16/ ሰውነታቸውን አግባብ ባለው ልብስ ያልሸፈኑ ሴቶች ይበዛሉ
17/ እውቀት የሌላቸው ሰዎች ህዝባዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ይወስናሉ
18/ ሰላምታ በትውውቅ ላይ ብቻ ይመሰረታል
19/ ውሸት መናገር ይስፋፋል
20/ የንግድ ቤቶች ተቀራርበው ይገነባሉ።
21/ ለሰይጣን አገልግሎት የሚውሉ ግመሎችና ለሰይጣን አገልግሎት የሚውሉ ቤቶች ይገነባሉ! ማለትም፦
1-አንድ ሰው ከሚጠቀምባቸው ውጭ ያሉ ግመሎች በስድ ሲለቀቁ ሰይጣን ይጋልባቸዋል።
2-ከመኖሪያ ቤት ውጭ ያሉ ትርፍ ቤቶች ለረጅም ጊዜ ሰው ሳይገባባቸዉ ከቆዩ የሰይጣን መኖሪያ ይሆናል።
22/ ሰዎች በመስጅድ ውበት ይፎካከራሉ በውስጡ ይመፃደቃሉ።
23/ ሺበታቸውን በጥቁር ቀለም የሚያጠቁሩ ሰዎች ይመጣሉ።
እነዚህ ሰዎች የጀነትን ሽታ እንኳን አያገኙም።
24/ ሰዎች አላህን የመታዘዝ ባህሪያቸው ይመነምናል። ለአኬራ መስራትም ይቀንሳል።
25/ ስስት ይስፋፋል፣ ሁሉም ሰው ግለኛ ይሆናል፣ አዋቂ እውቀቱን ለማካፈል ይሳሳል።
26/ ሰዎች አላማውን በማያውቁት ውጊያ ውስጥ ይሳተፋሉ (ይጋደላሉ)።
"ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ በሰዎች ላይ ይህ ዘመን ይመጣል። ገዳይ በምን ምክንያት እንደገደለ አያውቅም-ተገዳይ በምን ምክንያት እንደተገደለም አያውቅም።
27/ የህዝብ ገንዘብ ያለ አግባብ ይመዘበራል።
28/ አማና (ታማኝነት) ይጓደላል።
29/ ባል ሚስቱን እየታዘዘ እናቱን ይበድላል።
30/ በአባቶች ላይ እየተፌዘ (አባት ሳይከበር) ጓደኛ ይከበራል።
31/ በመስጅድ ውስጥ ጩኸት ይበራከታል።
32/ ተንኮሉ ተፈርቶ ሰው ይከበራል-ችሎታና ስነ-ምግር ግን የለውም።
33/ ፖሊስ ይበዛል፤ ይህም ማለት ወንጀል መበራከቱን ያመለክታል።
34/ አንድ ሰው በእውቀቱ አናሳ ሆኖ እና በባህሪውም ገና ያልተገራ ሆኖ ሳለ ድምፁ የሚያምር ሆኖ በመገኘቱ ብቻ ሶላት እንዲመራ (እንዲያሰግድ) ይደረጋል።
35/ ሚስት ባሏን በንግድና በስራ ላይ ትጋራለች።
36/ ብእር ይበራከታል፤ ድርሰት እና ህትመት ይስፋፋል።
37/ ልጅ መመኪያ መሆኑ ቀርቶ መተከዣና መቆጫ ይሆናል።
38/ የዝናብ እጥረት ይስተዋላል።
39/ መኪና ይፈለሰፋል። "ከኡመቶቼ መካከል ወደ መጨረሻዉ የሚመጡት ሱሩጅ ወይም (መኪና) ላይ ይሳፈራሉ።
የመጎጎዣ አይነት ነው በመስጅድ በሮች ያቆሙታል (ይወርዳሉ) ሴቶቻቸው ግን የለባሽ እርቃን ናቸው።
40/ ፊትና በመብዛቱ ሳቢያ ሞትን መመኘት።
41/ ኢራቅ ማእቀብ ይጣልባታል - ምግብ እና እርዳታ ትከለከላለች።
42/ በመቀጠልም ሻም (ሶሪያ፣ ሊባኖስ፣ ዩርዳኖስ እና ፍልስጤም) ምግብና እርዳታ ይከለከላሉ ማእቀብ ይጣልባቸዋል።
43/ የነብዩ ሙሐመድ (ሰ•ዐ•ወ) ከዚህ አለም በሞት መለየት እንደ አንድ የቂያማ ቀን መድረስ ምልክት ተወስዷል።
44/ በይተል መቅደስ (እየሩሳሌም) በሙስሊሞች ቁጥጥር ስር መግባት።
45/ በጅምላ ጨራሽ በሽታም ሆነ ጦርነት የሰው ህይወት መጥፋት።
46/ ሙስና፣ ማጭበርበርና የዋጋ ንብረት እያየለ መምጣት።
47/ በአረቦችም ሆነ በሌሎች ወገኖች ቤት ውስጥ ጣልቃ ገብነት እና ፊትና (መከራ) ይስተዋላል።
48/ በሙስሊሞች እና በሮማውያን (አውሮፓ እና አሜሪካ) የጋራ ስምምነት ይፈረማል።
አውፍ ኢብን ማሊክ (ረ•ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰ•ዐ•ወ) እንዲህ ብለዋል፦
•የቂያማ-ቀን• ከመድረሱ በፊት ስድስት ነገሮች ይከሰታሉ፦
> የኔ ሞት
> ከዚያም በይተልመቅዲስ ይከፈታል
> ከዚያም ሁለት ሞት እውን ይሆናል
> አንድ ሰው መቶ ዲናር ቢሰጠው እንኳን ምንም አይመስለውም
> ከዚያ በኋላ ደግሞ ፊትና ይከሰታል።
> ከዚያም በናንተና በነጮች መካከል ስምምነት ይኖራል። ይከዷችሁል። ሰማኒያ (80) አላማ ይዘው ይመጣሉ እያንዳንዱ አላማ ደግሞ 12 ሺህ (ንዑስ አላማ) አለው።
ያአላህ! እዘንልን ከምናውቀውም ሆነ ከማናውቀውም ፊትና ጠብቀን፣ በዲናች አትፈትነን! በዲናችን ላይ የመጣውን ፊትና አንሳልን ያረብ!
ሙባረክ
2.6K views23:54