2023-02-20 19:32:58
ሁሉን ነገር ሲረሳ የእርሱም ጉዳይ ተረሳለመሆኑ ይህ የትንሳኤ ቀን (ዕለተ ቂያማ ከተከሰተ ስንት ጊዜ ሆነው አስር ሺህ ወይስ ሃምሳ ሺህ ዓመታት አለፉ? ይህ ሁሉ ጊዜ በእርግጥ እንደ አንድ ቀን ብቻ ይቆጠራል ማለት ነው ምንም እንኳን ይህን ሁሉ ነገር ማሰቡና ማውጣት ማውረዱ ዋጋ ያለው ነገር ባይሆንም ጉዳዩ በመስሩር አእምሮ መመላለሱ አልቀረም።
በመሰረቱ የቀንና የሌሊት መፈራረቅ እንዲሁም የፀሐይና የጨረቃ መተካካት በዓለማዊ ሕይወት የሰው ልጅ ጊዜንና ቀናትን ለመስፈር የሚጠቀምባቸው ምልክቶች ቢሆኑም ዛሬ ግን ፀሓይ ብርሃኗን ተነጥቃ እንደአሮጌ ጨርቅ ተጨማድዳ ከተጣላች በኋላ ጊዜን መለካት ትርጉም ሊኖረው አልቻለም በመሆኑም ጊዜ ከእንግዲህ ብዙም ረብ ያለውና ግምት ሊሰጠው የሚችል ዋነኛ ጉዳይ አይሆንም፡፡
መላእክትም ታላላቅ የሆነ አካላቸውንና ብሩህ የሆኑ ግዙፍ ክንፎቻቸውን እያርገበገቡ ክፍት በሆኑት የሰማያት ደጃፎች በኩል ወደ ምድር መውረዳቸውን ቀጥለዋል ይህም ቢሆን ታዲያ በፍርሃትና በትህትና ስሜት ተሞልተው ይታዩ ነበር።
የዚህም ዋነኛው ምክንያት አላህ የተቆጣበት ቀን በመሆኑ ነው ፣ መላእክት ብቻ ሳይሆኑ ፍጥረት የተባለ በሙሉ የአላህን በታላቅ ሁኔታ መቆጣት አውቋል:: ለእርሱ ጥራትና ልዕልና የተገባው ጌታ) ከዚያ በኋላ ተመልሶ እንደዚያ ባለ ሁኔታ በማይቆጣበት አኳኋን ታላቅ የሆነው ቁጣው ነድዷል
ይህን በመሰለ አስጨናቂ ቀን በበዳዮች ላይ የሚደርስ ቅጣት እጥፍ ድርብ እንደመሆኑ ይህን በማሰብ የሚመጣው ስነልቦናዊ ቅድመ ቅጣቱ (መርበድበድና በፍርሃት መራዱ እንደዚሁ በጣም ከባድ ነው፡፡
በዚያ ሁሉ ጽልመት የዋጠው ሁኔታ አንድና ብቸኛው የብርሃን ምንጭ ከመልአክት አካል የሚገኘው ብርሃን ነው እነርሱም ከሰማያት ቀበሌዎች ከወረዱ በኋላ በሰልፍ በሶፍ ተሰድረውና አንገታቸውን ደፍተው በፀጥታ ቆሙ የሰው ልጅ እነዚያ ታማኝና ቅን የአላህ አገልጋዮች የሆኑት መላእክት ቀኑ ይዞት የሚመጣውን ነገር በመፍራት አንገት መድፋታቸውን ሲያስተውል ብርክ ይዞ ያንጠረጥረው ጀመር።
በጭንቅና ስቃይ ብዛት ጐላ ብሎ የሚታየው የነበረው የሰው ልጅ ጅኖችና የዱር አራዊቶች በቢሊዮኖች የሚቆጠር ድምፅ አላህ ፊት መቆማቸውን ሊያስተውሉ ከትንሽ ሹክሹክታ በስተቀር ሁሉም ፀጥ ረጭ አለ እርሱም እጅግ በጣም ሩህሩህ የሆነው የልቅና ጌታ ነው።
ሰማያት ቀስ በቀስ እንደሽንኩርት እየተላጡ ተፈረካክሰው አለቁ እንዲሁም የድሮዋ ምድር ከአገልግሎት ውጪ በመሆን አንዴ በንና ጠፋች። ከመጀመሪያው ጀምሮ እስከ ዓለም ፍፃሜ የተፈጠረ ፍጡር ሁሉ በአዲሷ ምድር አንድም ሳይቀር ተሰበሰበ።
ይች ምድር አዲስ እንደተኮላ ብር የነፃችና ጥርት ያለች ስትሆን በእርሷም አንዳችም ዓይነት ኃጢያት አልተፈፀመባትም አዲሷ ምድር በፀሐይ አለመኖር ለረዥም ዘመናት ሸፍኗት ከቆየው ፍፁም ፅልመት ተላቅቃ በጌታዋ ብርሃን እነሆ እንደገና ወገግ አለች። ዛሬ ከጥንቷ ፀሐይም ሆነ ጨረቃ ያልሆነ ልዩና አዲስ በሆነ ብርሃን ሁሉም ነገር በግልጽ ይታይ ጀምሯል ይህም ጽልመት የተወገደው ብሩክ በሆነው መለኮታዊ ብርሃን በመሆኑ አጠቃላዩን ሁኔታ (ትዕይንት) ብርሃን በሰለጠነበት ሂደት የተቃኘ አደረገው፡፡
በዚህ ቅጽበት ግን አንድ አሳዛኝ ሁኔታ በአንድ ግለሰብ ላይ ተፈጠረ ይኸውም የታሪካችን መዋቅር ከሚሽከረከርባቸው ግለሰቦች አንዱ የሆኑት የቀድሞው ቅምጥል አለቃ መስሩር ዓይናቸው የታወረ መሆኑ ነው፡፡ ኃያሉ አላህ ከሌሎች ከሃዲያን ላይ ብርሃናቸውን በመውሰድ እውር እንዳደረጋቸው ሁሉ መስሩርም የዚህ እጣ ተቋዳሽ እንዲሆን ተደረገ
በዚህ ክስተት ወቅት መስሩር እጅግ ከመደንገጡና ከመፍራቱ የተነሣ ቃላት ሊገልጹት በማይቻል ሁኔታ መጮህ ጀመረ። ይሁን እንጂ ድምጹ ከደረቱ ሳይወጣ ለራሱ ብቻ በሚሰማ ሁኔታ ባክኖ ቀረ እነሆ ከዚህች ሰዓት በኋላም ዘላለማዊ በሆነው ኩነኔ (ቅጣት) ውስጥ እንደገባ ሙሉ በሙሉ አረጋገጠ።
ከዚያም እንዲህ ሲል አጉተመተመ ጌታዬ ሆይ ለምንድን ነው እውር አድርገህ የቀሰቀስከኝ? እኔ በምድረ ዓለም ሳለሁ በእርግጥ ዓይናማ የነበርኩ ሲሆን?
ይቀጥላል…
413 views16:32