Get Mystery Box with random crypto!

እንዲህም ይወደዳል . . ቃለ መጠይቅ ስለነበረብኝ ወደ ቢቢሲ የዜና ጣቢያ በኮንትራት ታክሲ ሄድኩ | ወርቃማ ንግግሮች

እንዲህም ይወደዳል
.
.
ቃለ መጠይቅ ስለነበረብኝ ወደ ቢቢሲ የዜና ጣቢያ በኮንትራት ታክሲ ሄድኩኝ።የጣቢያው ደጃፍ ስደርስም ለሹፌሩ ለአርባ ደቂቃ ያክል እንዲጠብቀኝ ጠየቅኩት።
ሹፌሩም ቤት ሄዶ የዊንስተን ቸርችልን ንግግር መስማት እንዳለበት በመግለፅ፤መጠበቅ አለመቻሉን በይቅርታ ገለፀልኝ።
ንግግሬን ለመስማት የነበረው የጋለ ስሜት እጅጉን አስደስተኝ።ማንነቴን ሳልገልፅለትም ከኪሴ አስር ፓውንድ በማውጣት ሰጠሁት።
የሰጠሁትን ገንዘብ ባየም ጊዜ ደስታና ግርምት ተቀላቅሎት እንዲህ አለኝ:-
"አንድ ሰዓትም ቢሆን እጠብቆታለሁ ጌታዬ! ቸርችል ከፈለገ ገደል ይግባ።"