Get Mystery Box with random crypto!

##የመስሩርና የመቅሩር ታሪክ## ክፍል አስራ ስምንት የባሕሮች መቃጠል መስሩር በድንገት መራ | ወርቃማ ንግግሮች

##የመስሩርና የመቅሩር ታሪክ##

ክፍል አስራ ስምንት

የባሕሮች መቃጠል


መስሩር በድንገት መራመዱን አቆመ። በዚህ ጊዜ አጅበውት ከሚሄዱት መልአኮች አንዱ ለምን መራመድ አቆምክ? ሲል
ጠየቀው ጠየቀ። መስሩር በብስጭት እንደተሞላ የት ነው የምትወስዱኝ? በማለት ከፊት ለፊቱ ሲሄድ የነበረው መልአክ ለዚህ ጥያቄው ምንም ዓይነት መልስ አልሰጠውም:: ከኋላው እየተከተለው የነበረው ግን እንደሚከተለው በማለት መልስ ሰጠው ሰውዬ ሁላችንም ትዕዛዙን አክብረን እየሄድን ነው፡፡

ከአሁን በኋላ ምንም ዓይነት ወለም ዘለም ማለት የለም ገባህ? ወደፊት ቀጥል መስሩር እንደታዘዘው ወደፊት ለመጓዝ ተንቀሳቀሰ መቅሩር በበኩሉ ከጐኑ እየሄደ ቢሆንም ጉዞው ግን ዘና ያለ ይመስላል። መቅሩር በጉዞው ላይ ፈጣሪውን በማውሳት ስራ ላይ ምላሱን አስጠምዶ ነው እየተራመደ ያለው እንዲህ እያለ አላህን ይለምን ነበር ጌታዬ አላህ ሆይ! እባክህ እርዳኝ መቅሩር እንደ መስሩር ሁሉ ከፊቱና ከኋላው እንደጥላው ያጀቡት ኃይሎች እንዳሉ የተገነዘበ ቢሆንም ብዙም የተረበሸ አይመስልም።


መቅሩር ከሁለቱ አንዱን በጣም ዝቅ ባለ ድምፅ እንዲህ በማለት ጠየቀ ምን እየተካሄደ ነው ያለው ክቡራን?
ጠባቂዎቹም ሆነ ብለውና ትህትና ሳይጓደላቸው “ይህ የፍርዱ ቀን የመጀመሪያ ምዕራፍ ነው አሉት
ይህ አስፈሪ የሆነ ትዕይንት የመጀመሪያው ምዕራፍ ከሆነ የመጨረሻው ምን ሊሆን ነው? አለ መቅሩር
መላእክቱም ለዚህ አስተያየትና ጥያቄ መልስ ሳይሰጡ ቶሎ በል ፍጠን! በማለት ጉዟቸውን ቀጠሉ
ከአንዱ የሰዎች ስብስብ በኋላ ሌላ ከአንዱ ብሄር በኋላ ሌላው ብሄር እንዲሁም ከአንድ ሕዝብ በኋላ ሌላ ሕዝብ እየተግተለተለ ይተምማል።


ምድር ከመቃብሮቻቸው እየወጡ በሚተራመሱ ሰዎች ተጨናነቃለች ይህ የሚያሳየው ሁኔታው የአጽናፈ ዓለሙ ህልውና ማብቃቱንና የፍርዱ ቀን መቃረቡን የሚያሳይ ታላቅ ምልክት መሆኑን ነው፡፡

እየተተራመሰ ወደ አንድ አቅጣጫ ከሚነጉዱት ሕዝቦች ውስጥ አንድ ሰው እንዲህ በማለት ጮኸ ተመልከቱ ተመልከቱ ያንን ባሕር ብዙ ዓይኖች ሰውየው ወደጠቆመው ባህር ተወረወሩ በሚደንቅ አኳኋን ባህሩ እየተቃጠለ ነው ባህሩ ቤንዚን እንደሆነ ሁሉ እየተንቀለቀለ ይጦፋል። የባህሩ ውሃ እንደ እሳተ ገሞራ ነፋሪት ወደሰማይ እየተምዘዝገ ይወጣና መልሶ ይወድቃል በመቀጠልም እየተንጫረረና እየተረጨ ይጨሳል። ከዚያም የእሳት አሎሎ በመስራት እየተወነጨፈ ከተቀጣጠለ በኋላ አየሩን ወደ ሰማያዊነት በመቀየር ይትጐለጐላል።

መስሩርና መቅሩር በዚያ ሁልቆ መሳፍርት በሌለው ሕዝብ መሃል ቆመው እየሆነ ያለውን ነገር ፈዝዘው ያስተውላሉ በምድር ዓለም በነበሩበት ጊዜ የሚያውቁት ውሃ እሳትን ሲያጠፋ ነው:: ዛሬ ግን ሁኔታው የተገላቢጦሽ ነው የሆነው ውሃ እሳትን እያንቀለቀለ ሲያስጮኸው ተመለከቱ ከዚያ በኋላ ሁሉም ወደሚሄድበት አቅጣጫ መንቀሳቀስ ጀመረ
እንደመብረቅ ከየመቃብሮቻቸው ውስጥ እየፈነቀሉ የሚወጡት ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው የሚሄደው፡፡


ሁኔታውን ሲያስተውሉት መቃብር የሚተፋውን የሰው ልጅ ቁጥር መገመት ከባድ ነው ወንዶች፣ ሴቶች ፣ ህፃናትና አረጋውያን እንዲሁም የተለያዩ ቀለማት የፊት ቅርጽ ፣ ቋንቋ ምኑ ቅጡ ሁሉም በክረምት ወቅት ከመሬት እንደሚወጣ አሸን ይርመሰመሳል በዚህ ሁሉ ሕዝብ መሐል ያሉት መስሩርና መቅሩር በጉዟቸው ላይ ሁልጊዜም የሚራራቁት በትንሽ ጫማ ብቻ ነው የዚያ ሁሉ ወፈ ሰማይ ሕዝብ መጨረሻ እንዳይታይ ከአድማሱ ጥግ ያሉት ሰንሰለታማ ተራሮች ሰልፉን ያዘበራርቁት ጀምረዋል።


ይቀጥላል…