Get Mystery Box with random crypto!

የዱር እንስስት መሰባሰብ በበረሃ ላይ የተተከለ ድንኳን ችካሎቹ በአጋጣሚ ቢነቀሉ ነፋስ የትም ወ | ወርቃማ ንግግሮች

የዱር እንስስት መሰባሰብ


በበረሃ ላይ የተተከለ ድንኳን ችካሎቹ በአጋጣሚ ቢነቀሉ ነፋስ የትም ወስዶ በምድረ በዳ እንደሚጥላቸው ሁሉ ተራሮችም ከመሬት ሲነሱ አቧራ ብናኝ ሆነው በመጥፋታቸው ምድር የተንጣለለች ሜዳ ሆናለች ሰውም በመላእከት እየተነዳ ይርመሰመስባት ጀምሯል


ቀደም ብሎ እንደተገለፀው ተራሮቹ በሚያስደንቅና ይሆናል ተብሎ በማይገመት - ሁኔታ ተፈርፍረውና ቦንነው ድራሻቸው ጠፍቷል ፣ ሰውም በከፍተኛ ደረጃ በፍርሃት ተውጦ ይቅበዘበዛል ሁሉም ሰው በዚህ ታይቶ በማይታወቅ አስደንጋጭ ቀን አጀማመር በፍርሃት ቢዋጥም ገና የወደፊቱን ሁኔታ ሲያስበው - ሊመጣ የሚችለውን የከፋ አደጋ በመገመት በሰቃ ይተነፍሳል። መቅሩር በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ጌታውን መለመኑን አልተወም አላህ ሆይ እባክህ እዘንልኝ አንተ እጅግ አዛኝ ነህና አለ
መስሩር በበኩሉ ድንጋጤው አይሎል በሁለም አቅጣጫ አደጋ እያደነው መሆኑ ተሰምቶታል። ምን ይኽ ብቻ።


ሁኔታው ከዚህ የከፋ ቢሆንም ሞት የማይገኝበትና ምቾት የሌለው መሆኑ ነው ትልቁ አሳር መሬት እየተከፈተችና እየተሰነጠቀች በውስጧ ያሉትን ሙታን በምትተፋበት ወቅት የዱር አራዊትና እንስሳት እንዲሁም ጅኖችም ከሁሉም አቅጣጫ እየወጡ ከሰው ጋራ ይተራመሱ ገብተዋል
የሰውን ልጆች ከቀኝ በኩል በቅርብ የተቀላቀሏቸውን ጅኖች ተፈጥሯዊ መልካቸውን ሲያዩዋቸው በጣም አስቀያሚ መሆናቸው ሌላ ችግር ሆኖባቸዋል ሆኖም ከአጠቃላዩ ቀኑ ይዞት ከመጣው አስፈሪና አስደንጋጭ ነገር ጋር ሲነፃፀር የጅኖቹ መልከ ጥፉነት እዚህ ግባ የሚባል ችግር አይደለም::

ከዚህ ይልቅ የባህሮች መቃጠልና የተራሮች ተነቅሎ መንኮታኮት ነው ታላቅ መባትና ፍርሃት በሰው ልጆች ልብ ላይ የለቀቀባቸው ጅኖች በከዋክብቶች መካከል እንዲሁም ወደ ምድርና ወደ ሰማይ እንደፈለጉ እየበረሩና እየሮጡ ሲጫወቱ አስደናቂ እንዳልነበሩ ዛሬ ግን ሁሉም ቅስማቸው ተሰብሮና በሀሳብ ተውጠው እንገታቸውን
ደፍተዋል ወደ ታላቅ የሆነ የዱር አራዊትና የቤት እንስሳት መንጋ በሰው ልጆች ሰልፍ በግራ በኩል መሰባሰብ ጀመረ ቁጥራቸው ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ ነው የሚሄደው ከመሬት ውስጥ እያንዳንዱ መን እየወጣ በተጠጋ ቁጥር አንገቱን ደፍቶ በፍርሃት ሲራመድ ይታያል ብዙ ዓይነት የአራዊት ዝርያዎች አንበሳ፣ ነብር፡ የተራራ ፍየሎች ውሻ፡ አእዋፋት ዝሆኖችና አውራሪሶች ወዘተ ሁሉም አንድ ላይ ተቀላቅለው ይነጉዳሉ


የአንበሶች መንጋ መስሩርን ሲቀርቡት በድንጋጤ ይርበተበት ጀመር፡፡ በምድረ ዓለም እያለ ብዙ አንበሶችን በአደን ገድሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ከእነዚህ አናብስት አንዱ ቂሙን ሊበቀለኝ ይዘነጥለኝ ይሆናል ከሚል ነው ስጋቱ የመነጨው ፣ ይሁን እንጂ የአንበሶቹ መንጋ አጠገቡ እንደደረሱ ብዙም ትኩረት ሳይሰጡት ሩጫቸውን ቀጠሉ መስሩር አሁን ልብ ያለው ነገር ከእነዚያ አንበሶች ጋር የዱር ፍየሎች ያሉ መሆኑን ነው አንበሶቹ በፍየሎቹ መኖር - ግድ አልነበራቸውም፡፡

እንደዚሁም ፍየሎቹ ከአንበሶች ጋር መሆናቸው ምንም የሚያስፈራቸው አይመስልም ይህ ሁኔታ የሚያሳየው የዚህ ቀን ድንጋጤ የዱር እንስሳትን ባህሪ ፍፁም በመቀየር ደመነፍሳቸው ስለሚመገቡት ነገር እንዲያስበ እንዳላደረጋቸው ነው እንግዲህ ሁኔታውን ሲያጤነት የጅኖችና የዱር አራዊት በዚህ ስፍራ መተራመስ የቀኑን አስፈሪነት ይበልጥ እንዲባባስ አድርጐታል ማለት ይቀላል።
መስሩር እና መቅሩር አሁንም ተቀራርበው ነው የሚጓዙት ምንም እንኳን መስሩር በጭንቀት እየተንጠረጠረ ቢሆንም ቅሉ በዚህ ጊዜ መስሩር ወደ መቅሩር ቀረብ ብሎ አንዳንድ ግራ የሚገቡ ጥያቄዎችን ያቀርብለት ጀመር ከሞትን ምን ያህል ጊዜ ሆነን? ማለቴ ምን ያህል ጊዜ ነው ከመሞታችን በፊት የኖርነው? ማለቴ ምን ያህል ጊዜ ሆነን ከሞትንና ከተነሣን?


መቅሩር ለዚህ ጥያቄው መልስ ሲሰጥ እንዲህ አለ " ሁሉንም ነገር የሚያውቀው አላህ ነው እኔ በበኩሌ ትንሽ ቀናት እንዲያውም ጥቂት ስዓታት የቆየሁ ሆኖ ነው የሚሰማኝ እንደማስበው ከትንሽ ቀናት በፊት በሕይወት ነበርን ከጥቂት ሰዓታት በፊት ደግሞ የሞትን ይመስለኛል በእውነቱ ምኑም አልገባኝም

ይቀጥላል…