Get Mystery Box with random crypto!

ደቢር ለና አንዳንዴ ሰው አሏህን አንድን ጉዳይ እንዲያሳካለት አምርሮ ይለምናል።ህይወቱም ሙሉ ለ | ወርቃማ ንግግሮች

ደቢር ለና

አንዳንዴ ሰው አሏህን አንድን ጉዳይ እንዲያሳካለት አምርሮ ይለምናል።ህይወቱም ሙሉ ለሙሉ በዚያ ዱዓው መሳካት ላይ የተንጠለጠለች እንደሆነች አድርጎ ያስባል።
አሏህም ዱዓውን ይቀበለዋል።ብዙ ረጅም ጊዜ ሳይልፍም ያ የተሳከላት ዱዓ ለርሱ ጥቅምን እንዳላመጣለት ይደርስበታል።በዚያ የተነሳም ለከባድ አደጋ መዳረሱን ያስተውላል።ዘመን ወደ ኃላ ቢመለስም ያንን ዱዓ ፈፅሞ እንደማያደርግ እርግጠኛ ይሆናል።

በሰዪዲና ኑህ ዱዓ ውስጥ የምናገኘው ጥልቅ ትርጉምም ይህንን ነው።


قَالَ رَبِّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ أَنْ أَسْأَلَكَ مَا لَيْسَ لِي بِهِ عِلْمٌ ۖ

«ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ለእኔ ዕውቀት የሌለኝን ነገር የምጠይቅህ ከመሆን እኔ ባንተ እጠበቃለሁ፡፡"

ሰይዲና ኑህ ይህን ዱዓ ያደረጉት አሏህ በነገራት ፍፃሜ እውቀቱ ስለሌላቸው ነገር እንዳይጠይቁት ከነገራቸው ወዲህ ነው።

فَلَا تَسْأَلْنِ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۖ إِنِّي أَعِظُكَ أَن تَكُونَ مِنَ الْجَاهِلِينَ

"በርሱ ዕውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ፤ እኔ ከሚሳሳቱት ሰዎች እንዳትሆን እገስጽሀለሁ» አለ፡፡"

ተመልከት።እንዲህ የተባሉት አሏህ ከፍጡራን መሃል በእውቀትም ሆነ ተቅዋ ላስበለጣቸው ከኡሉል-ዐዝም አንዱ ለሆኑት ነቢይ ኑህ ናቸው።ለርሳቸው እንዲህ ከተባለ እኛ ለዚህ መሰል ዱዓ እጅጉን የተገባን ነን።
ነገራትን በሙሉ ወደ አሏህ ከማስጠጋት የተሻለ መንገድ ማግኘት ለኛ አስቸጋሪ ነው።
ለዚህም ከሰለፎች መሃል የአንዱ ዱዓ እንዲህ ነበር:-
اللهم دبِّر لي؛ فإني لا أُحسن التدبير، واختر لي؛ فإني لا أُحسن الاختيار

"አሏህ ሆይ! ነገራቶቼን አስተናብርልኝ።እኔ ማስተናበርን አላሳምርም።(ከነገራት)መልካሙን መምረጥንም አልችልምና፤ ምረጥልኝ። ።