Get Mystery Box with random crypto!

ቤተሰቦቹ ነጋ ጠባ «እስከዛሬ ያደረክልን አንድም ነገር የለም፤ የምንኖረው የሾቀ ህይወት ነው» እያ | ወርቃማ ንግግሮች

ቤተሰቦቹ ነጋ ጠባ «እስከዛሬ ያደረክልን አንድም ነገር የለም፤ የምንኖረው የሾቀ ህይወት ነው» እያሉ በንዴት አንጀቱን የሚያሾቁት አባት ነበር። ከተወሰነ ዓመት በኋላ በህመም አልጋ ላይ ወደቀ። ከህልፈቱ በፊት አንድ ኑዛዜ አስተላለፈ። ከቤቱ ውስጥ ተቆፍሮ የተቀበረ ትልቅ ኃብት እንዳለ የሚጠቁም ፍንጭ ሰጠ። ከሞተ በኋላ የቤተሰቡ አባላት ቤቱን አፍርሰው መሬቱን ቆፈሩት። ትልቅ ሳጥን አገኙ። ሲከፍቱት በውስጡ አንድ ደብዳቤ ተቀምጧል። ደብዳቤው ምን ቢል ጥሩ ነው ?

«እንደኔ ጀግና ከሆናችሁ ቤቱን እንደ አዲስ ገንቡት»

ምጥን አስተምህሮ


በዚህ ዘመን ለኢትዮጵያዊያን ደሳሳ ጎጆ ቢሆን እንኳ ከቤት በላይ ትልቅ ኃብት የትም አይገኝም። አይቀሬው የሞት ጥሪ መጥቶ ከምትኖርበት ቤት ያለፈቃድህ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስክትወጣ ድረስ ገመናን ሁሉ በሚሸፍነው ቤትህ ውስጥ ሆነህ ይህንንስ ማን አየው አልሐምዱሊላህ እያሉ መኖር በራሱ የኃብቶች ሁሉ ትልቅ ኃብት ነው።