Get Mystery Box with random crypto!

በይቱል-ዐንከቡት የሸረሪት ድር(በይቱል-ዐንከቡት) ሲባል ቁርአንን ማንበብ ወደሚችል ሰው አዕምሮ | ወርቃማ ንግግሮች

በይቱል-ዐንከቡት

የሸረሪት ድር(በይቱል-ዐንከቡት) ሲባል ቁርአንን ማንበብ ወደሚችል ሰው አዕምሮ ቀድሞ የሚመጣው ደካማ ቤትነቱ ነው።ይህም አሏህ በቁርአኑ ቤቱን በደካማነቱ ባህሪይ ገልፆ በማንሳቱ ምክኒያት ነው።

وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنكَبُوتِ ۖ

"ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡"

(አል-ዐንከቡት፥41)

ታዲያ በጣም ያስገረመኝ በሂጅራው ክስተት ነቢያችን ﷺ እና ባልደረባቸው በዋሻው በነበሩበት ሰዓት ከቁረይሾች አሰሳ ከታደጋቸው አስባባት አንዱ በዋሻው መግቢያ ላይ የነበረው የሸረሪት ድር ነበር።የቁረይሽ አሳሾች ሰይዳችንﷺ ከሲዲቅ ጋር ወደ ተቀመጡበት ዋሻ መግቢያው ጋር ሲደርሱ:-
"(ሙሐመድ) እዚህ ቢኖር የሸረሪት ድር በደጃፉ አያደራም ነበር።" ብለው ነበር የተመለሱት።

አሏህ ይሁን ካለ አንተን ደካማ በተሰኘ ሰበብ ይጠብቅሃል።እርሱ ይሁን ካለ የሸረሪት ድር የእልፍ አዕላፍ ሰራዊትን መንገድ ይሰውራል።ከክፋት አይኖች ሁሉ ይከልልሃል።
እርሱ አላህ ነዋ!