Get Mystery Box with random crypto!

ጥንቃቄ… በአቋራጭ ለማድግ ብላችሁ ለምታስቡ… እቤትዎ ቁጭ ብለው በወር ከመቶ ሺህ እስከ | ወርቃማ ንግግሮች

ጥንቃቄ…


በአቋራጭ ለማድግ ብላችሁ ለምታስቡ…


እቤትዎ ቁጭ ብለው በወር ከመቶ ሺህ እስከ አንድ ሚሊየን ብር መስራት የሚችሉበት ምርጥ መንገድ እኛ ጋር አለ… ተብሎ የተጻፈ ፖስት አየሁና በተቀመጠው ስልክ ደወልኩ

ስልኩን ያነሳው ጎረምሳ ጥቂት የማይመስል ወሬ ካወራኝ ቡሃላ …ስራውን ከመጀመርህ በፊት በኦንላይን ስልጠና መውሰድ አለብህ አሁን በምነግርህ አካውንት ለመመዝገቢያ 3ሺህ ብር አስገባና ደረሰኝ ላክ ከዚያ …ብሎ ሊቀጥል ሲል ይቅርታ ግን ትክክለኛ መገኛ አድራሻችሁ የት ነው? ቢሮ መጥቼ ክፍያ ልፈጽም ስለው …ጆሮየ ላይ ስልኩን ዘግቶ አሰናበተኝ… ድጋሜ ስሞክር አይሰራም እንደነቃሁበት አውቋል ብሎክ ሊስት ከቶኛል ማለት ነው

ለማንኛውም ይሄ አይነቱ የሶሻል ሚድያ ሳክስ ሿሿ ነው …ብዙ ሰው ይነቃል ብየ አስባለሁ ያልነቃችሁ ካላችሁ አተርፍ ባይ አጉዳይ እንዳትሆኑ ጥንቃቄ ያሻል ለማለት ያክል ነው

~