Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.28K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 163

2022-12-05 20:33:52
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ100 የልብ ሕሙማን ሕጻናት ቀዶ ጥገና ወደሚያደርጉበት ሀገር ደርሰው የሚመለሱበትን ሙሉ የትራንስፖርት ወጪ እንደሚሸፍን አስታወቀ፡፡

በዛሬው ዕለትም አየር መንገዱ ለመጀመሪያ አራት ተጓዦች ሽኝት የተደረገላቸው ሲሆን በሽኝቱ ወቅትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄ በሽኝቱ ላይ እንደተናገሩት÷ ሕጻናትን ማዳን ግዴታችን ነው ብለዋል፡፡

በውጭው ሀገር የሚታከሙትን ሕጻናት የቆይታ እና የሕክምና ወጪ ደግሞ ሮተሪ ኢትዮጵያ እንደሚሸፍን ተገልጿል፡፡(FBC)

@tikvahethmagazine
18.7K viewsedited  17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 14:03:57
1ሺህ 167 ኢትዮጵያውያን ወንዶች ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል

በዛሬው ዕለት በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳኡዲ አረቢያ በችግር ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1ሺህ 167 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱ ዜጎች መካከል 1ሺህ 165 ወንዶች ሲሆኑ 2 ደግሞ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው ተብሏል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉም ተገልጿል።

ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 7968 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@tikvahethmagazine
14.7K viewsedited  11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 11:58:59
#InternationalVolunteerDay

የዓለም የበጎፈቃጀኞች ቀን በዛሬው ዕለት "Solidarity Through Volunteering ... አብሮነት በበጎፈቃደኝነት" በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ይውላል።

ስለ በጎፈቃድ አገልግሎት ይወያዩ  https://t.me/tikvahforum/15753

@tikvahethmagazine
18.9K viewsedited  08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 11:25:39
የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከ17 ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ማመንጨት ችሏል።

ከጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ኦፕሬሽን ከገቡ 16 የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ተርባይኖች 17 ጌጋ ዋት ሠዓት ኃይል ለማመንጨት ታቅዶ 17 ነጥብ 7 ጌጋ ዋት ሰዓት በማመንጨት የዕቅዱን 104 ነጥብ 1 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡ 

የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት እያንዳንዳቸው 2 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው 48 የንፋስ ተርባይኖች የሚኖሩት ሲሆን ከዚህ ወስጥም የ32 የንፋስ ተርባይኖች የተከላ ሥራ ተጠናቋል፡፡ ከተተከሉት መካከልም 16ቱ ተርባይኖች ወደ ኦፕሬሽን ገብተው ኃይል ማምረት ጀምረዋል፡፡

@tikvahethmagazine
18.4K viewsedited  08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 11:22:35
#ጋርዳማርታ

በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ በ3,710 ሄክታር ማሳ ላይ የለማው የመኸር ግብርና ሥራ በአከባቢው በተከሰተው ድርቅ ሙሉ በሙሉ መውደሙን ተከትሎ 32,275 ቤተሰብ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ችግር መጋለጣቸው ተገልጿል።

በመኸር እርሻ ሥራ ከ3,710 ሄ/ር ማሳ ላይ 75,324 ኩንታል ምርት የተጠበቀ ቢሆንም በአከባቢው በተደጋጋሚ የተከሰተው የዝናብ እጥረት ያስከተለው ድርቅ የአርሶ አደሩን ህይወት ከባድ ፈተና ውስጥ እንዲወድቅ ማድረጉ ተነግሯል።

አከባቢው የእርሻ ሥራ የሚያከናውነው ሙሉ በሙሉ የዝናብ ውሃን መሠረት አድርጎ በመሆኑ ለተከታታይ 2 እና 3 ዓመታት የተከሰተው ድርቅ በግብርና ሥራዎች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንዳሳደረባቸውና የእንስሳት ልማትም ከፍተኛ የመኖ እጥረት መከሰቱም ተግልጿል።

በአከባቢው የተከሰተው የረሃብ ሁኔታ ከአርሶ አደሩ አቅም በላይ በመሆኑ መንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና አርሶ አደሮችን እንዲታደግ የጋርዳ ማርታ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጥሪውን አቅርቧል።

@tikvahethmagazine
16.9K viewsedited  08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 11:21:48
ለመኖርያ ቤት ለቢሮ ለንግድ ቦታዎ ውብ እና ማራኪ የሆኑ ዲዛይኖችን በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ካለው የፊኒሺንግ ስራ ጋር ሰርተን እናስረክቦታለን። ይደውሉልን።

የምንሰጣቸው አገልግሎት
የኢንቴርየር ዲዛይን እና የፊኒሺንግ ስራ
አርቴክቸራል ዲዛይን
የኢፓክሲ ስራ ( Epoxy Work )
የእንጨት ፓርቲሽኖችን መስራት
አጠቃላይ የእንጨት ስራ
ብራንዲንግ

Contact us  @etheldesign1
0939902740
0919361804

Join Telegram: t.me/etheldesign
14.8K views08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 11:21:37
አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ!
አዲስ ነገር ከአያት አክስዮን ማህበር!
የመጨረሻዎቹ ጥቂት የአያት አክሲዬኖች በሽያጭ ላይ ናቸው!

ለእርስዎ፣ ለታዳጊ ልጅዎ፣ለቤተሰብዎ እና ወዳጅ ዘመድዎ እስከ 44% ትርፍ የሚያስገኝለዎትን የአያት አክሲዬንን በስጦታና ያበርክቱ!!!
አሁኑኑ ይደውሉ +251930653333

አያት የተሰማራባቸው የስራ ዘርፎች፦
- በሪል ስቴት ግንባታና ልማት (አያት ሪል ስቴት)
- በሆቴልና ቱሪዝም (ራስ ሆቴል፣ ሮሃ ሆቴል)
- በማርብል ማምረቻ ኢንዱስትሪ
- በጠጠር ማምረቻ ኢንዱስትሪ
- በብሎኬት ማምረቻ ኢንዱስትሪ
- በእንጨትና ብረታብረት ውጤቶች ማምረቻ ኢንዱስትሪ
- በትምህርት ኢንቨስትመንት (አልፋ ዩኒቨርስቲና ት/ቤቶች) እና በሌሎች ፋይናንሻል ኢንቨስትመንት
አያትን የሰማ ትርፋማ!
አያት አክስዮን ማህበር!
16.7K views08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 14:02:00
#ቡናባንክ

ከ13 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች ያሉት ቡና ባንክ አ.ማ ዓመታዊውን የባለአክሲዮኖች 13ኛ መደበኛ እና 6ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እሁድ ሕዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ም አካሂዷል።

የቡና ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አምባሳደር ዓለማየሁ ሰዋገኝ የባንኩን የ2021/22 ዓመታዊ ሪፖርት ለባለአክሲዮኖች ሲያቀርቡ ባንኩ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ፦

- ከግብር በፊት 1.19 ቢሊየን ብር ትርፍ ማስመዝገቡንና ከ27 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

- በአጠቃላይ 7.6 ቢሊዮን ብር ያበደረ ሲሆን ይህም በአጠቃላይ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ያበደረው የገንዘብ መጠን በ41.3 በመቶ በማሳደግ 25.85ቢሊዮን ብር ያደረሰው መሆኑም ተገልፃል።

- የባንኩ ካፒታል 1.2 ቢሊየን ብር እድገት አሳይቷል። ይህም የባንኩን አጠቃላይ የካፒታል መጠን 5.1 ቢሊዮን ብር አድርሶታል፡፡

- የባንኩ ጠቅላላ ሃብት በበጀት ዓመቱ የ8.16 ቢሊዮን ብር ዕድገት አሳይቶ 34.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል።

- ባንኩ 58 አዲስ ቅርንጫፎችን ከፍቷል፡፡ ይህም ባንኩ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ የከፈታቸውን ቅርንጫፎች መጠን 343 አድርሶታል።

- የባንኩን አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር በዓመቱ መጨረሻ ወደ 1 ሚሊዮን 960 ሺ 853 ከፍ ብሏል።

- “ኻዲም” (KHADIM)” በተሰኘው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ያገኘው ያገኘውን አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን  ብር 896.6 ሚሊዮን አድርሶታል ብሏል። ይህም ካለፈው ዓመት አፈፃፀም ጋር ሲነጻጸር የብር 272.5 ሚሊዮን ወይም የ43.7 በመቶ ጭማሪ ማሳየት መቻሉም ተጠቁሟል፡፡

@tikvahethmagazine
21.6K viewsedited  11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 13:39:31
የቦሩ ሜዳ አጠቃላይ ሆስፒታል 1ሺ 500 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ሊሰጥ ነው።

ከታህሳ 3/2015 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 9/2015 ዓ.ም ድረስ የቦሩ ሜዳ አጠቃላይ ሆስፒታል ከሂማሊያ ካታራክት ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ከ1 ሺ 500 በላይ ለሚሆኑ የኅብረሰብ ክፍሎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ተበጀ ገልጸዋል።

ከደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ጋር በመተባበርም በሁሉም ወረዳዎች የቅስቀሳና የልየታ ሥራ ተሠርቷል፡፡

የህክምና አገልግሎቱ የሚሰጠው በቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ሲሆን ተደራሽ የሚያደርገዉም ዝቅተኛ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በመሆኑ የትራንስፖርትና የምግብ ወጪን ጨምሮ ሁሉንም ወጭዎች በሂማሊያ ካታራክት የሚሸፈንና ታካሚዎች ምንም ዓይነት ወጪ እንደማያወጡ ሥራ አስኪያጁ አመላክተዋል፡፡

መረጃው የደቡብ ወሎ ዞን ኮሚውኒኬሽን ነው፤ ፎቶ -ፋይል

@tikvahethmagazine
20.5K viewsedited  10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 13:39:18
የመጨረሻዎቹን የአያት አክስዮን ማህበር የአክሲዬን ባለድርሻዎችን ይቀላቀሉ!

ለእርስዎ፣ ለታዳጊ ልጅዎ፣ለቤተሰብዎ እና ወዳጅ ዘመድዎ የአያትን አክሲዬን በስጦታ ያበርክቱ!!!

በ 3 ዓመት ውስጥ በየዓመቱ ከፍለው የሚያጠናቅቁት ዕድል ቀርቦልዎታል

አሁኑኑ ይደውሉ +251911690751/+251930653333

አያት የተሰማራባቸው የስራ ዘርፎች
- በሪል ስቴት ግንባታና ልማት (አያት ሪል ስቴት)
- በሆቴልና ቱሪዝም (ራስ ሆቴል፣ ሮሃ ሆቴል)
- በማርብል ማምረቻ ኢንዱስትሪ
- በጠጠር ማምረቻ ኢንዱስትሪ
- በብሎኬት ማምረቻ ኢንዱስትሪ
- በእንጨትና ብረታብረት ውጤቶች ማምረቻ ኢንዱስትሪ
- በትምህርት ኢንቨስትመንት (አልፋ ዩኒቨርስቲና ት/ቤቶች)
- በሌሎች ፋይናንሻል ኢንቨስትመንት
18.9K views10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ