Get Mystery Box with random crypto!

#ጋርዳማርታ በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ በ3,710 ሄክታር ማሳ ላይ የለማው የመኸር ግብርና ሥ | TIKVAH-MAGAZINE

#ጋርዳማርታ

በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ በ3,710 ሄክታር ማሳ ላይ የለማው የመኸር ግብርና ሥራ በአከባቢው በተከሰተው ድርቅ ሙሉ በሙሉ መውደሙን ተከትሎ 32,275 ቤተሰብ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ችግር መጋለጣቸው ተገልጿል።

በመኸር እርሻ ሥራ ከ3,710 ሄ/ር ማሳ ላይ 75,324 ኩንታል ምርት የተጠበቀ ቢሆንም በአከባቢው በተደጋጋሚ የተከሰተው የዝናብ እጥረት ያስከተለው ድርቅ የአርሶ አደሩን ህይወት ከባድ ፈተና ውስጥ እንዲወድቅ ማድረጉ ተነግሯል።

አከባቢው የእርሻ ሥራ የሚያከናውነው ሙሉ በሙሉ የዝናብ ውሃን መሠረት አድርጎ በመሆኑ ለተከታታይ 2 እና 3 ዓመታት የተከሰተው ድርቅ በግብርና ሥራዎች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንዳሳደረባቸውና የእንስሳት ልማትም ከፍተኛ የመኖ እጥረት መከሰቱም ተግልጿል።

በአከባቢው የተከሰተው የረሃብ ሁኔታ ከአርሶ አደሩ አቅም በላይ በመሆኑ መንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና አርሶ አደሮችን እንዲታደግ የጋርዳ ማርታ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጥሪውን አቅርቧል።

@tikvahethmagazine