Get Mystery Box with random crypto!

የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከ17 ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ማመንጨት ችሏል። ከጥቅምት | TIKVAH-MAGAZINE

የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከ17 ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ማመንጨት ችሏል።

ከጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ኦፕሬሽን ከገቡ 16 የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ተርባይኖች 17 ጌጋ ዋት ሠዓት ኃይል ለማመንጨት ታቅዶ 17 ነጥብ 7 ጌጋ ዋት ሰዓት በማመንጨት የዕቅዱን 104 ነጥብ 1 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡ 

የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት እያንዳንዳቸው 2 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው 48 የንፋስ ተርባይኖች የሚኖሩት ሲሆን ከዚህ ወስጥም የ32 የንፋስ ተርባይኖች የተከላ ሥራ ተጠናቋል፡፡ ከተተከሉት መካከልም 16ቱ ተርባይኖች ወደ ኦፕሬሽን ገብተው ኃይል ማምረት ጀምረዋል፡፡

@tikvahethmagazine