Get Mystery Box with random crypto!

#ቡናባንክ ከ13 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች ያሉት ቡና ባንክ አ.ማ ዓመታዊውን የባለአክሲዮኖች 13 | TIKVAH-MAGAZINE

#ቡናባንክ

ከ13 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች ያሉት ቡና ባንክ አ.ማ ዓመታዊውን የባለአክሲዮኖች 13ኛ መደበኛ እና 6ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እሁድ ሕዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ም አካሂዷል።

የቡና ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አምባሳደር ዓለማየሁ ሰዋገኝ የባንኩን የ2021/22 ዓመታዊ ሪፖርት ለባለአክሲዮኖች ሲያቀርቡ ባንኩ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ፦

- ከግብር በፊት 1.19 ቢሊየን ብር ትርፍ ማስመዝገቡንና ከ27 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

- በአጠቃላይ 7.6 ቢሊዮን ብር ያበደረ ሲሆን ይህም በአጠቃላይ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ያበደረው የገንዘብ መጠን በ41.3 በመቶ በማሳደግ 25.85ቢሊዮን ብር ያደረሰው መሆኑም ተገልፃል።

- የባንኩ ካፒታል 1.2 ቢሊየን ብር እድገት አሳይቷል። ይህም የባንኩን አጠቃላይ የካፒታል መጠን 5.1 ቢሊዮን ብር አድርሶታል፡፡

- የባንኩ ጠቅላላ ሃብት በበጀት ዓመቱ የ8.16 ቢሊዮን ብር ዕድገት አሳይቶ 34.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል።

- ባንኩ 58 አዲስ ቅርንጫፎችን ከፍቷል፡፡ ይህም ባንኩ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ የከፈታቸውን ቅርንጫፎች መጠን 343 አድርሶታል።

- የባንኩን አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር በዓመቱ መጨረሻ ወደ 1 ሚሊዮን 960 ሺ 853 ከፍ ብሏል።

- “ኻዲም” (KHADIM)” በተሰኘው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ያገኘው ያገኘውን አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን  ብር 896.6 ሚሊዮን አድርሶታል ብሏል። ይህም ካለፈው ዓመት አፈፃፀም ጋር ሲነጻጸር የብር 272.5 ሚሊዮን ወይም የ43.7 በመቶ ጭማሪ ማሳየት መቻሉም ተጠቁሟል፡፡

@tikvahethmagazine