Get Mystery Box with random crypto!

የቦሩ ሜዳ አጠቃላይ ሆስፒታል 1ሺ 500 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ሊሰ | TIKVAH-MAGAZINE

የቦሩ ሜዳ አጠቃላይ ሆስፒታል 1ሺ 500 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ሊሰጥ ነው።

ከታህሳ 3/2015 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 9/2015 ዓ.ም ድረስ የቦሩ ሜዳ አጠቃላይ ሆስፒታል ከሂማሊያ ካታራክት ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ከ1 ሺ 500 በላይ ለሚሆኑ የኅብረሰብ ክፍሎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ተበጀ ገልጸዋል።

ከደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ጋር በመተባበርም በሁሉም ወረዳዎች የቅስቀሳና የልየታ ሥራ ተሠርቷል፡፡

የህክምና አገልግሎቱ የሚሰጠው በቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ሲሆን ተደራሽ የሚያደርገዉም ዝቅተኛ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በመሆኑ የትራንስፖርትና የምግብ ወጪን ጨምሮ ሁሉንም ወጭዎች በሂማሊያ ካታራክት የሚሸፈንና ታካሚዎች ምንም ዓይነት ወጪ እንደማያወጡ ሥራ አስኪያጁ አመላክተዋል፡፡

መረጃው የደቡብ ወሎ ዞን ኮሚውኒኬሽን ነው፤ ፎቶ -ፋይል

@tikvahethmagazine