Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Update
Silver
Platinum
Golden
Cloudbridge
Traininginstitute
Samitech
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.23K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 160

2022-12-12 13:38:13
ፅንስ እያቋረጠች ከቤቷ ጓሮ እንሰት ስር ቀብራለች በሚል የተጠረጠረችው ግለሰብ...

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዉብ አሪ ወረዳ አይዳማሪ ተብሎ በሚጠራዉ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችዉ ወይዘሮ የባህላዊ(የልምድ) አዋላጅ ነኝ በማለት ትጠራለች።

ወይዘሮዋ ነብሰጡር እናቶች ወደ ጤናጣቢያ ሄደዉ በህክምና ሙያተኞች የወሊድ ድጋፍ አገልግሎት ማግኘት እንዳይችሉ በማድረግ ምጥ የያዛቸዉና ለመዉለድ የተቃረቡ ወጣት ሴቶችን ስታዋልድ እንዲሁም ፅንስ ስታቋርጥ የፅንሱ ህይወት ሲጠፋባት በራሷ ጓሮ እንደምትቀብር ከህብረተሰቡ ለፖሊስ ጥቆማ ደርሶ በቁጥጥር ስር ትውላለች።

ፖሊስ ከጤና ጽህፈት ቤትና ከሴቶችና ህፃናት ጋር በጋራ በመሆን ባደረገዉ ማጣራትም የአራት ህፃናት(ፅንስ) በድን ገላ ከተጠርጣሪዋ ጓሮ እንሰት ስር ተቀብሮ መገኘቱን ገልጿል።

ተጠርጣሪዋን በቁጥጥር ስር አውሎ የማጣራት ስራውን መጀመሩን ገልጾ ምርመራዉ ሲጠናቀቅ ይፋ እንደሚደረግ ከደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine
24.6K viewsedited  10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 12:51:27
የኩፍኝ ክትባት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተጨማሪ ኒውትሪሽን ጋር ከታህሣስ 13 ቀን ጀምሮ ይሰጣል።

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኩፍኝ በሽታ መድኃኒት ክትባት ከትላንትናው እለት ጀምሮ ማሠራጨቱን አስታውቋል።

በአገልግሎቱ የመድኃኒት ክምችት አያያዝ አስተዳደር የክትባት መድኃኒት ተጠሪ አቶ ሀብታሙ አለማየሁ የክትባት መድኃኒቱ በመላው ሃገሪቱ ለሚገኙ አጠቃላይ ክልልሎች የሚካሄድ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም 16 ሚሊየን 298 ሺ 009 ሕፃናትን መከተብ ይቻላል የተባለ ሲሆን ክትባቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተጨማሪ ኒውትሪሽን ጋር ከታህሣስ 13 ቀን ጀምሮ እንደሚሠጥና እስከ 5 ዓመት የእድሜ ክልል ያሉ ህፃናት መከተብ እንዳለባቸው ጠቅሷል።

@tikvahethmagazine
23.7K viewsedited  09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 12:50:31
በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ላይ በተፈጸመ ስርቆት ተቋሙ የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ አጋጥሞታል

በ2014 ዓ.ም ብቻ 24 የሚደርሱ ከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊ የብረት ማማዎች ሙሉ ለሙሉ የወደቁ ሲሆን የብረትና የኮንዳክተር ዘረፋ እንደተፈጸመባቸው እና በቁጥር 30 ሺ 257 የሚሆኑ የተለያዩ የታወር ብረቶች ደግሞ በቁማቸው ካሉ ማማዎች ተፈታተው መወሰዳቸው ተገልጿል፡፡

ከወደቁትና በቁማቸው ከተዘረፉት ማማዎች 756 ቶን ብረት ሲሰረቅ በገንዘብ ሲሰላም 72 ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ብር የሚገመት ኪሳራ መድረሱንና የተሰረቀውን ብረት መልሶ ለመተካት ተቋሙ 23 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ብር ማውጣቱ ተነግሯል፡፡

በ2014 ዓ.ም በስርቆት፣ በመልሶ ግንባታና ከአገልግሎት መቋረጥ ጋር ተያይዞ የባከነውን 2 ሺ 396 ሜጋ ዋት ሰዓት ኃይል ጨምሮ ተቋሙ ከመቶ ሚሊዮን ብር ያላነሰ ኪሳራ እንዳጋጠመው ታውቋል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ተከሰው በሚቀርቡ ወንጀለኞች ላይ የፍትህ አካላት የሚጥሉት ቅጣት አስተማሪ አለመሆኑና ግብዓት ለማግኘት ሲሉ ስርቆቱን የሚደግፉና የሚረከቡ የብረታብረት ፋብሪካዎችና ባለሀብቶች እንቅስቃሴ ሊፈተሸ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

መረጃው፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

@tikvahethmagazine
22.5K viewsedited  09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 12:50:20
አብዱ የሻወር ውሃ ማሞቂያ ሽያጭና ጥገና
ጤና ይስጥልን ቤተሰቦች
.. የተለያዩ የሻወር ውሃ ማሞቂያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘን ቀርበናል
.... sterling, lorenzeti, atmor, milano, arston, florence.. እንዲሁም ሌሎችን .....
በብቁ ባለሙያዎቻችን ያሉበት ድረስ በመምጣት እንገጥማለን እንዲሁም የተበላሸ ካሎት እናስተካክላለን
ለበለጠ መረጃ 0921461805/0941074778
telegram link https://t.me/abduawe
22.5K views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 12:50:04
በሲኤምሲ ሚካኤል ጀርባ
3000 ሱቆች በአንድ ቦታ?
አዎ በአንድ ቦታ
የት ካሉ በአያት ግራንድ ሞል
በአይነቱ እና በስፋቱ ተወዳዳሪ በሌለው የገበያ ማዕከል
ዛሬዉኑ ሱቅ ይግዙ
በማይደገም አጋጣሚ ይጠቀሙ

ብሩክ ሠጠኝ
0912898237
Telegram

https://t.me/Bruk_Ayat_Realstate
https://t.me/Bruk_Ayat_Realstate
24.6K views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 09:59:04 ልጆችን ፎቶ አንስቶ ቪዲዮ ቀርጾ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማጋራት ምን ጥንቃቄ ያስፈልገዋል?

ማኅበራዊ ሚዲያ ትልቅ ተጽዕኖ በሚፈጥርበት በአሁኑ ሰዓት ብዙ መረጃዎች ይንሸራሸራሉ። አንዱ ማኅበራዊ ሚዲያ ከሚጠቀማቸው መረጃዎች መካከል የግል መረጃዎች ይጠቀሳሉ።

ስማችንን፣ ሥራችንን፣ ውሏችንን፣ ቤተሰባዊ ጉዳዮቻችንን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ባጋራን ቁጥር ዲጂታል ማንነት (Digital Identity) እየፈጠርን እንሄዳለን።

ይህ ማለት እኛ ላለፉት 10 ዓመታት ማን እንደሆንን፣ ምን አይነት ባህሪያት እንዳሉን፣ ማንን እንደምንደግፍ፣ ማንን እንደምንጠላ የመሳሰሉት መረጃዎች በቀላሉ ማግኘት ያስችላል። ይህ ማለት ማንነታችንን በዲጂታል ዱካችን (Digital Footprint) መለየት ያስችላል።

በተለይ የቲክቶክ ማኅበራዊ ትስስር አጠቃቀም ዝንባሌ በጨመረበት በአሁኑ ወቅት የአዋቂዎች ብቻ ሳይሆን ወላጆች ልጆቻቸውን ቪዲዮ እየቀረጹ መልቀቅ፣ ፎቶ አያነሱ ማጋራት፣ ስለልጆቻቸው መረጃ መጽሐፍ በስፋት እየተስተዋለ ያለ ተግባር ነው።

አብዛኞቹ ወላጆች ይህንን በሚያደርጉበት ወቅት የሚያጋሩት መረጃ "በወደፊት የልጄ ህይወት ላይ ምን ያስከትላል?" የሚለውን ጥያቄ በአግባቡ አያጤኑትም።

ስለ ልጆቻችንን መረጃ (ጹሑፍ፣ ፎቶ፣ ቪዲዮ) ከማጋራታችን በፊት እነዚህን ጠቃሚ ነጥቦች ማጤን ያስፈልጋል?

- መረጃዎች(ጹሑፍ፣ ፎቶ፣ ቪዲዮ) አንድ ጊዜ በማኅበራዊ ሚዲያው ከተለቀቁ በምንም አይነት መልኩ ልንቆጣጠራቸው አንችልም።

- ዛሬ ሊያዝናኑን የሚችሉት ምስሎች ከ15 ዓመት በኋላ ተመሳሳይ ነገር ላይፈጥሩ ይችላሉ።

- የሚለቀቀው መረጃ ለልጄ ከዓመታት በኋላ ጥሩ ወይስ መጥፎ ሊሆን ይችላል ብሎ ቀድሞ ማሰብ ያስፈልጋል።

- በማኅበራዊ ሚዲያ የሚያጋሩት መረጃ በልጆ ማንነት ላይ አወንታዊም ሆነ አሉታዊ አስተዋፅኦ የማኖር እድሉ ከፍተኛ መሆኑን መረዳት እንዲሁ ጠቃሚ ነው።

ምን የከፋ ነገር ሊከሰት ይችላል?

- መረጃዎች ሁልጊዜ እኛ ባስቀመጥነው መንገድ ብቻ አይሰራጭም። በመሆኑም የልጆቻችን ፎቶ ወይም ቪዲዮ ቅርጹ ተለውጦ ለመጥፎ ነገር ማስታወቂያ፣ መነገጃ፣ መረጃ ማስተላለፊያ ሊውል ይችላል።

ምን ማድረግ ይመከራል?

- መረጃዎችን መገደብ አንዱ ዘዴ ነው። ይህም በሁለት አይነት መልኩ ማካሄድ ይቻላል።

#አንዱ እኛው ራሳችን ሁሉንም የልጆቻችንን መረጃ፣ እንቅስቃሴና ውሎ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ አለማጋራት ነው።

#ሁለተኛው የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾቻችንን የግል ደኅንነት (Privacy Setting) ማዘመንና ተደራሽነታቸውን መገደብ ይቻላል።

- የግሎን የዲጂታል ክህሎት (Digital Literacy) ማሳደግ ለዚህም ሆነ ለግሎ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በጎ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

በዚህ ጉዳይ ያሎትን ምልከታ እንዲሁም ገጠመኝ ያጋሩን እንወያይበት https://t.me/tikvahforum/17007

@tikvahethmagazine
7.5K viewsedited  06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 09:58:35
#ጥቆማ

የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት የመታወቂያ ካርድ ህትመትን በተመለከተ ከአታሚ ድርጅቶች ጋር ወርክሾፕ ለማዘጋጀት አቅዷል።

በዚህም በካርድ ህትመቱ ላይ አብራችሁ መሥራት የምትፈልጉ የሀገር ውስጥ ድርጅቶች ከታች በሚገኘው ሊንክ ላይ በመመዝገብ ለወርክሾፕ ተሳትፎ መመዝገብ ትችላላችሁ።

ለመመዝገብ id.gov.et/printingamharic

@tikvahethmagazine
7.4K viewsedited  06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 09:58:24
አድቫንስ የመኪና ሽያጭ ማንኛውንም መኪና በጥሩ ዋጋ የሚገዙበት ቦታ, ብዙ  ዓይነት የክፍያ አማራጮች አሉን።

Yaris jiwela: 1,700,000
Suzuki dzire: 2,200,000
Suzuki swift: 2,200,000
Tucson:5,800,000
እና ሌሎች መኪኖች ማግኘት ትችላላችሁ

በ  BANK የ መኪናዉን 40% በ 4 ዓመት የሚከፈል እናመቻቻለን  ።

በ ተመጣጣኝ ዋጋ የፈለጉትን መኪና እኛጋ
ያገኛሉ ።

ለበለጠ መረጃ: +251943191128/ +251930493842

ወይም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/+ZEFaCwwUIn45MWRk
6.8K views06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 09:58:17
በሲኤምሲ ሚካኤል ጀርባ
በረጅም ጊዜ አከፋፈል የቤት ባለቤት ይሁኑ  
ዘመን ተሻጋሪ ሃብት በአነስተኛ ወለድ         
ገንዘብዎን ወደ ጥሪት ይቀይሩ
በተመጣጣኝ 9.5% ወለድ ተንደላቀው የሚከፈሉት ፡፡

በ15% ቅድመ ክፍያ ብቻ

ብሩክ ሠጠኝ
0912898237

Telegram
https://t.me/Bruk_Ayat_Realstate
https://t.me/Bruk_Ayat_Realstate
6.6K views06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 18:11:21
በመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት 533 የቤተሰብ አባላት እየተፈናቀሉ መሆኑ ተነገረ

በደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ ውጫሌ ከተማ ግራር ገንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሰፈር በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት 268 ሴቶችን ጨምሮ 533 የቤተሰብ አባላት በአደጋው ምክንያት እየተፈናቀሉ መሆናቸውና የጉዳቱ ሰለባ መሆናቸውን ተጠቁሟል።

የተፈጥሮ አደጋው በየቀኑ እየጨመረ መሆኑንና እስካሁንም 170 የመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱ ሲገለጽ የአደጋው መንስኤ እስካሁን በውል አለመታወቁንና በዞን ባለሙያዎች የአደጋው ምክንያት እንዲጠና ጥያቄ መቅረቡን ተነግሯል።

በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ሳይደርስም ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው ዘመድ ቤት እንዲጠለሉም የተነገረ ሲሆን የደረሰው አደጋ ከወረዳው አቅም በላይ መሆኑን እና የበላይ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥያቄ መቅረቡን ከአምባሰል ወረዳ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@tikvahethmagazine
18.8K views15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ