Get Mystery Box with random crypto!

ልጆችን ፎቶ አንስቶ ቪዲዮ ቀርጾ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማጋራት ምን ጥንቃቄ ያስፈልገዋል? ማኅ | TIKVAH-MAGAZINE

ልጆችን ፎቶ አንስቶ ቪዲዮ ቀርጾ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማጋራት ምን ጥንቃቄ ያስፈልገዋል?

ማኅበራዊ ሚዲያ ትልቅ ተጽዕኖ በሚፈጥርበት በአሁኑ ሰዓት ብዙ መረጃዎች ይንሸራሸራሉ። አንዱ ማኅበራዊ ሚዲያ ከሚጠቀማቸው መረጃዎች መካከል የግል መረጃዎች ይጠቀሳሉ።

ስማችንን፣ ሥራችንን፣ ውሏችንን፣ ቤተሰባዊ ጉዳዮቻችንን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ባጋራን ቁጥር ዲጂታል ማንነት (Digital Identity) እየፈጠርን እንሄዳለን።

ይህ ማለት እኛ ላለፉት 10 ዓመታት ማን እንደሆንን፣ ምን አይነት ባህሪያት እንዳሉን፣ ማንን እንደምንደግፍ፣ ማንን እንደምንጠላ የመሳሰሉት መረጃዎች በቀላሉ ማግኘት ያስችላል። ይህ ማለት ማንነታችንን በዲጂታል ዱካችን (Digital Footprint) መለየት ያስችላል።

በተለይ የቲክቶክ ማኅበራዊ ትስስር አጠቃቀም ዝንባሌ በጨመረበት በአሁኑ ወቅት የአዋቂዎች ብቻ ሳይሆን ወላጆች ልጆቻቸውን ቪዲዮ እየቀረጹ መልቀቅ፣ ፎቶ አያነሱ ማጋራት፣ ስለልጆቻቸው መረጃ መጽሐፍ በስፋት እየተስተዋለ ያለ ተግባር ነው።

አብዛኞቹ ወላጆች ይህንን በሚያደርጉበት ወቅት የሚያጋሩት መረጃ "በወደፊት የልጄ ህይወት ላይ ምን ያስከትላል?" የሚለውን ጥያቄ በአግባቡ አያጤኑትም።

ስለ ልጆቻችንን መረጃ (ጹሑፍ፣ ፎቶ፣ ቪዲዮ) ከማጋራታችን በፊት እነዚህን ጠቃሚ ነጥቦች ማጤን ያስፈልጋል?

- መረጃዎች(ጹሑፍ፣ ፎቶ፣ ቪዲዮ) አንድ ጊዜ በማኅበራዊ ሚዲያው ከተለቀቁ በምንም አይነት መልኩ ልንቆጣጠራቸው አንችልም።

- ዛሬ ሊያዝናኑን የሚችሉት ምስሎች ከ15 ዓመት በኋላ ተመሳሳይ ነገር ላይፈጥሩ ይችላሉ።

- የሚለቀቀው መረጃ ለልጄ ከዓመታት በኋላ ጥሩ ወይስ መጥፎ ሊሆን ይችላል ብሎ ቀድሞ ማሰብ ያስፈልጋል።

- በማኅበራዊ ሚዲያ የሚያጋሩት መረጃ በልጆ ማንነት ላይ አወንታዊም ሆነ አሉታዊ አስተዋፅኦ የማኖር እድሉ ከፍተኛ መሆኑን መረዳት እንዲሁ ጠቃሚ ነው።

ምን የከፋ ነገር ሊከሰት ይችላል?

- መረጃዎች ሁልጊዜ እኛ ባስቀመጥነው መንገድ ብቻ አይሰራጭም። በመሆኑም የልጆቻችን ፎቶ ወይም ቪዲዮ ቅርጹ ተለውጦ ለመጥፎ ነገር ማስታወቂያ፣ መነገጃ፣ መረጃ ማስተላለፊያ ሊውል ይችላል።

ምን ማድረግ ይመከራል?

- መረጃዎችን መገደብ አንዱ ዘዴ ነው። ይህም በሁለት አይነት መልኩ ማካሄድ ይቻላል።

#አንዱ እኛው ራሳችን ሁሉንም የልጆቻችንን መረጃ፣ እንቅስቃሴና ውሎ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ አለማጋራት ነው።

#ሁለተኛው የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾቻችንን የግል ደኅንነት (Privacy Setting) ማዘመንና ተደራሽነታቸውን መገደብ ይቻላል።

- የግሎን የዲጂታል ክህሎት (Digital Literacy) ማሳደግ ለዚህም ሆነ ለግሎ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በጎ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

በዚህ ጉዳይ ያሎትን ምልከታ እንዲሁም ገጠመኝ ያጋሩን እንወያይበት https://t.me/tikvahforum/17007

@tikvahethmagazine