Get Mystery Box with random crypto!

በመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት 533 የቤተሰብ አባላት እየተፈናቀሉ መሆኑ ተነገረ በደቡብ ወሎ | TIKVAH-MAGAZINE

በመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት 533 የቤተሰብ አባላት እየተፈናቀሉ መሆኑ ተነገረ

በደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ ውጫሌ ከተማ ግራር ገንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሰፈር በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት 268 ሴቶችን ጨምሮ 533 የቤተሰብ አባላት በአደጋው ምክንያት እየተፈናቀሉ መሆናቸውና የጉዳቱ ሰለባ መሆናቸውን ተጠቁሟል።

የተፈጥሮ አደጋው በየቀኑ እየጨመረ መሆኑንና እስካሁንም 170 የመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱ ሲገለጽ የአደጋው መንስኤ እስካሁን በውል አለመታወቁንና በዞን ባለሙያዎች የአደጋው ምክንያት እንዲጠና ጥያቄ መቅረቡን ተነግሯል።

በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ሳይደርስም ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው ዘመድ ቤት እንዲጠለሉም የተነገረ ሲሆን የደረሰው አደጋ ከወረዳው አቅም በላይ መሆኑን እና የበላይ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥያቄ መቅረቡን ከአምባሰል ወረዳ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@tikvahethmagazine