Get Mystery Box with random crypto!

በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ላይ በተፈጸመ ስርቆት ተቋሙ የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ አጋጥሞታል በ | TIKVAH-MAGAZINE

በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ላይ በተፈጸመ ስርቆት ተቋሙ የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ አጋጥሞታል

በ2014 ዓ.ም ብቻ 24 የሚደርሱ ከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊ የብረት ማማዎች ሙሉ ለሙሉ የወደቁ ሲሆን የብረትና የኮንዳክተር ዘረፋ እንደተፈጸመባቸው እና በቁጥር 30 ሺ 257 የሚሆኑ የተለያዩ የታወር ብረቶች ደግሞ በቁማቸው ካሉ ማማዎች ተፈታተው መወሰዳቸው ተገልጿል፡፡

ከወደቁትና በቁማቸው ከተዘረፉት ማማዎች 756 ቶን ብረት ሲሰረቅ በገንዘብ ሲሰላም 72 ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ብር የሚገመት ኪሳራ መድረሱንና የተሰረቀውን ብረት መልሶ ለመተካት ተቋሙ 23 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ብር ማውጣቱ ተነግሯል፡፡

በ2014 ዓ.ም በስርቆት፣ በመልሶ ግንባታና ከአገልግሎት መቋረጥ ጋር ተያይዞ የባከነውን 2 ሺ 396 ሜጋ ዋት ሰዓት ኃይል ጨምሮ ተቋሙ ከመቶ ሚሊዮን ብር ያላነሰ ኪሳራ እንዳጋጠመው ታውቋል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ተከሰው በሚቀርቡ ወንጀለኞች ላይ የፍትህ አካላት የሚጥሉት ቅጣት አስተማሪ አለመሆኑና ግብዓት ለማግኘት ሲሉ ስርቆቱን የሚደግፉና የሚረከቡ የብረታብረት ፋብሪካዎችና ባለሀብቶች እንቅስቃሴ ሊፈተሸ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

መረጃው፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

@tikvahethmagazine