Get Mystery Box with random crypto!

የኩፍኝ ክትባት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተጨማሪ ኒውትሪሽን ጋር ከታህሣስ 13 ቀን ጀምሮ ይሰጣል። | TIKVAH-MAGAZINE

የኩፍኝ ክትባት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተጨማሪ ኒውትሪሽን ጋር ከታህሣስ 13 ቀን ጀምሮ ይሰጣል።

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኩፍኝ በሽታ መድኃኒት ክትባት ከትላንትናው እለት ጀምሮ ማሠራጨቱን አስታውቋል።

በአገልግሎቱ የመድኃኒት ክምችት አያያዝ አስተዳደር የክትባት መድኃኒት ተጠሪ አቶ ሀብታሙ አለማየሁ የክትባት መድኃኒቱ በመላው ሃገሪቱ ለሚገኙ አጠቃላይ ክልልሎች የሚካሄድ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም 16 ሚሊየን 298 ሺ 009 ሕፃናትን መከተብ ይቻላል የተባለ ሲሆን ክትባቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተጨማሪ ኒውትሪሽን ጋር ከታህሣስ 13 ቀን ጀምሮ እንደሚሠጥና እስከ 5 ዓመት የእድሜ ክልል ያሉ ህፃናት መከተብ እንዳለባቸው ጠቅሷል።

@tikvahethmagazine