Get Mystery Box with random crypto!

ፅንስ እያቋረጠች ከቤቷ ጓሮ እንሰት ስር ቀብራለች በሚል የተጠረጠረችው ግለሰብ... በደቡብ ክልል | TIKVAH-MAGAZINE

ፅንስ እያቋረጠች ከቤቷ ጓሮ እንሰት ስር ቀብራለች በሚል የተጠረጠረችው ግለሰብ...

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዉብ አሪ ወረዳ አይዳማሪ ተብሎ በሚጠራዉ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችዉ ወይዘሮ የባህላዊ(የልምድ) አዋላጅ ነኝ በማለት ትጠራለች።

ወይዘሮዋ ነብሰጡር እናቶች ወደ ጤናጣቢያ ሄደዉ በህክምና ሙያተኞች የወሊድ ድጋፍ አገልግሎት ማግኘት እንዳይችሉ በማድረግ ምጥ የያዛቸዉና ለመዉለድ የተቃረቡ ወጣት ሴቶችን ስታዋልድ እንዲሁም ፅንስ ስታቋርጥ የፅንሱ ህይወት ሲጠፋባት በራሷ ጓሮ እንደምትቀብር ከህብረተሰቡ ለፖሊስ ጥቆማ ደርሶ በቁጥጥር ስር ትውላለች።

ፖሊስ ከጤና ጽህፈት ቤትና ከሴቶችና ህፃናት ጋር በጋራ በመሆን ባደረገዉ ማጣራትም የአራት ህፃናት(ፅንስ) በድን ገላ ከተጠርጣሪዋ ጓሮ እንሰት ስር ተቀብሮ መገኘቱን ገልጿል።

ተጠርጣሪዋን በቁጥጥር ስር አውሎ የማጣራት ስራውን መጀመሩን ገልጾ ምርመራዉ ሲጠናቀቅ ይፋ እንደሚደረግ ከደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine