Get Mystery Box with random crypto!

#ጥንቃቄ የአንድ ብሩን ሳንቲም በሺዎች በሚቆጠር ገንዘብ እንገዛለን ከሚሉ አጭበርባሪዎች ኅብረተሰ | TIKVAH-MAGAZINE

#ጥንቃቄ

የአንድ ብሩን ሳንቲም በሺዎች በሚቆጠር ገንዘብ እንገዛለን ከሚሉ አጭበርባሪዎች ኅብረተሰቡ ራሱን እንዲጠብቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳስቧል።

ከሰሞኑ በተለያዩ ማኅበራዊ ድረገፆች አራት የግዕዝ ፊደላት ያሉትን የአንድ ብር ሳንቲም በ2 ሺህ ብር እና ከዚያም በላይ እንገዛለን የሚሉ ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ ማስታወቂያዎች በስፋት ተስተውለዋል።

ማስታወቂያዎቹ ኅብረተሰቡን ለማጭበርበር እየተነገሩ ያሉ እና ከእውነት የራቁ መሆናቸውን ያሳወቀው ብሔራዊ ባንኩ፣ ኅብረተሰቡ ራሱን ከአጭበርባሪዎች ሊጠብቅ እንደሚገባ ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በበኩሉ፣ ድርጊቱ በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን አሳውቆ በዚህ ማጭበርበር ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ግለሰቦች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ አስጠንቅቋል፡፡(EBC)

@tikvahethmagazine