Get Mystery Box with random crypto!

የዛምቢያ ፖሊስ የ27 ኢትዮጵያውያን አስከሬን በዛምቢያ ዋና ከተማ እሁድ እለት መገኘቱን አረጋግጧል | TIKVAH-MAGAZINE

የዛምቢያ ፖሊስ የ27 ኢትዮጵያውያን አስከሬን በዛምቢያ ዋና ከተማ እሁድ እለት መገኘቱን አረጋግጧል።

የፖሊስ ምርመራ እንደሚያመለክተው ከ20 እስከ 38 ዓመት የሆናቸው ወንዶች ንግዌሬ በተባለ አካባቢ ባልታወቁ ሰዎች አስክሬናቸው ተጥሎ መገኘቱ ተናግሯል።

ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች እንደሆኑ እንደሚታመን የተነገረ ሲሆን አንድ ግለሰብ በህይወት እያለ በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ለህክምና መወሰዱ ተገልጿል።

27ቱ አስከሬኖች ለምርመራ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ተነግሯል። ፖሊስ እንዲሁም ሌሎች የጸጥታ አካላት ምርመራ ላይ መሆናቸውም ነው የዜና አውታሮች የዘገቡት።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ በደረሰው አደጋ የተሰማውን ሀዘን ገልጾ የተሰራጨውን ዘገባ እንደሚያጣራ አሳውቋል።

ግለሰቦቹ በህገወጥ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ ሲሉ ህይወታቸውን ማጣታቸው መዘገቡን የጠቆመው ሚንስቴሩ አደጋውን ለማጣራት ባለሙያዎችን ወደ አካባቢው በማሰማራት ከዛምቢያ መንግስት ጋር እንደሚሰራም አረጋግጧል፡፡

ቀደም ሲል በተመሳሳይ ሁኔታ ማላዊ ውስጥ ህይወታቸው ያለፉ ወገኖችን ሁኔታ ለመመርመር በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተመራ ቡድን በአገሪቱ እንደሚገኝም አስታውሷል፡፡

@tikvahethmagazine