Get Mystery Box with random crypto!

የ“ኤርፖርት ሲቲ” ግንባታ በተያዘው በጀት ዓመት ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ። ከ | TIKVAH-MAGAZINE

የ“ኤርፖርት ሲቲ” ግንባታ በተያዘው በጀት ዓመት ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ።

ከሦስት ዓመት በፊት ይፋ የተደረገው የ”ኤርፖርት ሲቲ” ግንባታ በተያዘው በጀት ዓመት ለመጀመር የሚያስችለውን ሥራ እያከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።

በኦሮሚያ ክልል ከቢሾፍቱ ከተማ ጥቂት ወጣ ባለ ሥፍራ ላይ እንደሚገነባ የተገለጸው ይህ ፕሮጀክት፤ ዘመናዊ ሆቴሎች፣ ከቀረጥ ነጻ የግብይት ሥፍራና የካርጎ ሎጂስቲክ ማዕከል ይኖረዋል ነው የተባለው።

የአውሮፕላን ማረፊያው ግንባታ ሲጠናቀቅ በዓመት 100 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።

በቀጣይም የፕሮጀክቱን ዲዛይን ለሚሰሩ ኩባንያዎች ጨረታ እንደሚወጣ ጠቅሰው በተያዘው ዓመት ሁሉንም የዝግጅት ሥራዎችን በማጠናቀቅ ወደ ግንባታ ለመግባት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 5 ቢሊዮን ዶላር በጀት የተያዘለት ሲሆን፤ በአምስት ዓመታት ውስጥ ተገንብቶ እንደሚጠናቀቅም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ እንደ አስፈላጊነቱ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ ሊገነባ እንደሚችልም ጠቁመዋል። (ENA)

@tikvahethmagazine