Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 195.15K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 162

2022-11-10 12:35:13
የድሬዳዋ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት የፌስቡክ ገጽ ከቁጥጥር ውጪ መሆኑ ተገለጸ

የድሬዳዋ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት (Dira Dawa Mass Media Enterprise) የፌስቡክ ማኅበራዊ ድረ ገጹ ከቁጥጥር ውጪ መሆኑ ተገልጿል። የድሬዳዋ አስተዳደር ኮሚውኒኬሽን ቢሮ በድርጅቱ ገጽ እየተለቀቁ ያሉ መረጃዎች ድርጅቱን የማይወክሉ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethmagazine
25.4K viewsedited  09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 12:33:53
#Bahirdar

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ  በባህርዳርና አካባቢው ለአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ የተሰጠ ቦታ ወደ ሪል ስቴት አስቀይረናል በሚል አክሲዮን እየሸጡ እንደሆነ ተደርሶበታል ብሏል።

ቢሮው ይህ ይህ ሁኔታ ፍፁም #ሀሰት ስለሆነ ህብረተሰቡ ጥንቄ እንዲያደርግ የጥንቃቄ መልዕክት ብሎ ባሰራጨው መልዕክት ገልጿል።

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው በበኩላቸው ለሪል ስቴት አክሲዮን በሚል ሽያጭ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው ከግለሰብ እስከ 200,000 ብር ድረስ መሰብሰብ መጀመሩንና ይህም ከተጀመረ መቆየቱን ገልጸዋል።

@tikvahethmagazine
24.3K viewsedited  09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 12:33:25
ሰፊ የሆነውን የሎጂስቲክስ ዓለም በደንብ ለማወቅ የሚፈልጉም ሆኑ በሙያው ላይ ተሰማርተው ያላቸውን ዕውቀት ለማዳበርና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም የሚሹ ሁሉ ይመርጡታል፤ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለውን የፊያታ ዲፕሎማ ሥልጠና!

በኢትዮጵያ ውስጥ በብቸኝነት ሥልጠናውን እየሰጠ የሚገኘውና ሥልጠናውን ወስደው የተመረቁ ባለሙያዎች ምስክርነታቸውን የሚሰጡለት ማኅበራችን አሁንም በማታ እንዲሁም በቅዳሜና እሑድ ክፍለ-ጊዜዎች ሥልጠናውን ለመጀመር በምዝገባ ላይ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ገጻችንን t.me/EFFSAAOfficial ይጎብኙ!
ወይም
በስልክ ቁጥራችን 0903 182525 ወይም 011 558 9045 ላይ ይደውሉልን!

በአካል ለመምጣት ከፈለጉ አድራሻችን ካዛንችዝ ንግሥት ታወርስ ሆቴልና አፓርትመንቶች 4ኛ ፎቅ (ኢሊሊ ሆቴል ፊት ለፊት) ላይ ነው፡፡
9.1K views09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 19:32:06
ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የተገነባው የዓሊ ከተማ-ዋቤ ድልድይና ኮንክሪት አስፋልት መንገድ

በፌደራል መንግስት የተገነባውና ሁለት ቢሊዮን አንድ መቶ ሃምሳ ሦስት ሚሊዮን ስልሳ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ አንድ ብር ወጪ የተደረገበት የዓሊ ከተማ-ዋቤ ድልድይና ኮንክሪት አስፋልት መንገድ መጠናቀቁ ተገልጿል።

መንገዱ 56.5 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን የአራት ድልድዮች ግንባታና ከባድ የቆረጣ ሥራን በማለፍ በታለመት ጊዜ መጠናቀቁ ተነግሯል። ግንባታው በአጠቃላይ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ማውጣቱ ተገልጿል።

የፕሮጀክቱ ዕውን መሆን ምርቶችን በስፋት እና በጥራት ወደ ማዕከላዊ ገበያ በማድረስ ኢኮኖሚያዊ ፍይዳው የጎላ ሲሆን በዋናነት ሮቤ፣ ዓሊ እና ዋቤ ከተሞችን በቅርበት በማገናኘት፥ የቱሪዝም መዳረሻ የሆኑትን የሶፍ ዑመር ዋሻ፣ የሳነቴ አምባ እና የዲንሾ ብሔራዊ ፓርክ ለጎብኝዎች ምቹ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተገልጿል።

መረጃው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ነው።

@tikvahethmagazine
23.5K viewsedited  16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 17:00:09
#ጤናረቡዕ

የዛሬ እንግዳችን ዶ/ር ቤቴል ሳምሶን ይተዋወቁ

ዶ/ር ቤቴል የሴቶች እና ወጣቶች ጤና አንቂ ስትሆን፣ በተለይም የጡት እና የማህፀን በር ካንሰር ቅድመ ምርመራ ላይ፣ እንዲሁም ፆታዊ እና የስነ ተዋልዶ ጤና ላይ በመስራት በማህበረሰቡ ውስጥ የማንቃት ስትሰራ ነበር፡፡

በተጨማሪም እቴጌ(Etege) እና ሳባ(SABA) የተሰኙ የዲጅታል ጤና መድረኮች መስራች ስትሆን በሞያዋም ሀኪም ነች።

ዛሬ ምሽት 1:00 ላይ በ #TikvahMagazine ላይ በቀጥታ ስለ ጡት ካንሰር እንወያያለን

አዘጋጅ: ዶ/ር ፋሲካ ሽመልስ

እንዳያመልጦ!

@tikvahethmagazine
26.8K viewsedited  14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 13:07:21
#አዲስአበባ

በአዲስ አበባ ባለፉት ሶስት ወራት በትራፊክ አደጋ ከ 1.2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ደርሷል

በቀለበት እና ከቀለበት ውጭ ባሉት መንገዶች ላይ በተሽከርካሪዎች ግጭት የተነሳ ከ 1,268,000  ብር በላይ የሚገመት የመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ደርሷል።

ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ 21 ግጭቶች በቀለበት መንገድ በሚገኙ ሀብቶች ላይ ሲደርስ 39 ግጭቶች ደግሞ ከቀለበት መንገድ ውጪ በአጠቃላይ 60 የሚሆኑ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

በግጭት ጉዳት እየደረሰባቸው የሚገኙት የመንገድ ሀብቶች በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ተገዝተው በምሽት አገልግሎት እንዲሰጡ በተተከሉት የመንገድ ዳር መብራት ምሰሶዎች፣ የአቅጣጫና ርቀት አመላካች ሰሌዳዎች፣ የመንገድ ማካፈያ ግንቦችና የውሃ መውረጃ ቱቦዎችና ክዳኖች ላይ እና ሌሎች ንብረቶች ላይ መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethmagazine
12.7K viewsedited  10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 13:07:10
ሰፊ የሆነውን የሎጂስቲክስ ዓለም በደንብ ለማወቅ የሚፈልጉም ሆኑ በሙያው ላይ ተሰማርተው ያላቸውን ዕውቀት ለማዳበርና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም የሚሹ ሁሉ ይመርጡታል፤ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለውን የፊያታ ዲፕሎማ ሥልጠና!

በኢትዮጵያ ውስጥ በብቸኝነት ሥልጠናውን እየሰጠ የሚገኘውና ሥልጠናውን ወስደው የተመረቁ ባለሙያዎች ምስክርነታቸውን የሚሰጡለት ማኅበራችን አሁንም በማታ እንዲሁም በቅዳሜና እሑድ ክፍለ-ጊዜዎች ሥልጠናውን ለመጀመር በምዝገባ ላይ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ገጻችንን t.me/EFFSAAOfficial ይጎብኙ!
ወይም
በስልክ ቁጥራችን 0903 182525 ወይም 011 558 9045 ላይ ይደውሉልን!

በአካል ለመምጣት ከፈለጉ አድራሻችን ካዛንችዝ ንግሥት ታወርስ ሆቴልና አፓርትመንቶች 4ኛ ፎቅ (ኢሊሊ ሆቴል ፊት ለፊት) ላይ ነው፡፡
11.7K views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 13:07:00
የሽያጭ እውቀትን ወደ ክህሎት ማሳደግ ብርቱ ጥረት ይጠይቃል። አንድን ገዢ እንዴት ማለም፣ ማቅረብ፣ ምሳመን ማወቅ የሽያጭ ባለሙያ ለመባል በቂ ሊሆን ይችላል። በሽያጭ ሙያ ላይ ከ20 አመታት በላይ በተለያየ መስኮች ላይ በሰሩ ባለሙያዎች እየሰለጠኑ፣ እየተወያዩ፣ እየተመካከሩ፣ እየተመሩ መስራት ግን ስመጥር የሽያጭ ባለሙያ ያደርጎታል። ለሁለት ወር በምንሰጠው

የሽያጭ እና ግብይት
የዲጂታል ማርኬቲንግ
የደንበኛ አያያያዝ
የሽያጭ ማይንድሴት ክህሎት ስልጠና ላይ በመሳተፍ ይለውጡ፣ ይቀጠሩ!

+251967280828 / +251115572357
ቦሌ ብራስ፣ ዘርጋው ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103
11.3K views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 22:08:59
ዛሬ የተከሰተው ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ (የደም ጨረቃ)

ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ ወይም የደም ጨረቃ የሚባለው ጨረቃ ወደ ምድራችን ጥላ ማለትም በፔናምብራው እና አምብራ በተሰኙት የጥላው ክፍሎች ሲያልፉ ከፀሐይ የሚመጣው ብርሃን ነጸብራቅ ነው።

ይህም ከጸሐይ የሚወጣው ነጸብራቅ ሙሉ በሙሉ በምድር በመሸፈን እና በምድር ጫፍ የሚያመልጠው ብርሃን በከባቢ አየሩ ተንጸባቆ ስለሚያልፍ እንደ ሰማያዊ እና ቫዮሌት የመሳሰሉትን ቀለማት በታትኖ ሲያስቀራቸው ቀይና ብርቱካናማ ረጅም የሞገድ  ርዝመት ስላላቸው ከባቢ አየሩን በማለፍ ጨረቃን ይህን ቀለም ይሰጧታል።

በዛሬው ዕለት ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተው ይህ ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ ለ85 ደቂቃዎች የቆየ ሲሆን በ ሰሜን አሜሪካ፣ በአንዳንድ የደቡብ አሜሪካ ክፍሎች፣ በኤስያ፣ በአውስትራሊያ እና በኒውዝ ላንድ ታይቷል።

* መረጃውን የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የላከልን ሲሆን ፎቶው በቤጂንግ የተከሰተና ከAFP የተገኘ ነው።

@tikvahethmagazine
12.7K viewsedited  19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 21:37:36
በሳኡዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ዜጎችን ዳግም የማስመለስ ስራ ከ2 ሳምንት በኋላ ይጀመራል።

ከዚህ ቀደም ከሳዑዲ አረቢያ 102 ሺህ ዜጎችን ለማስመለስ ዕቅድ ተይዞ በ198 በረራዎች  71 ሺህ 697 ሰዎች ማስመለስ የተቻለ ሲሆን ከ2 ሳምንት በኋላ ሥራው ይጀምራል ተብሏል።

በዚህም ሳይመለሱ የቀሩ 30 ሺህ 303 ዜጎችን ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለማስመለስ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንና ከመጡ በኋላም የሚያርፉበት ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ  ዝግጁ መደጉ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም ዜጎችን በማስመለስ ሂደት የሌላ አገር ዜጎች እና ሌሎች ግለሰቦች ከተመላሾቹ ጋር በተጭበረበረ ሰነድ ለመግባት ሞክረው  አስቀድሞ በተደረገ የማጣራት ስራ ሊያዙ ችለዋል ነው የተባለው።

ከ16 ሴክተር መስርያ ቤቶች የተውጣጣው ብሄራዊ ኮሚቴው ዜጎችን ለማስመለስ የተሰሩ አጠቃላይ ዝግጅቶችን ዛሬ መገምገሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አሳውቋል።

@tikvahethmagazine
15.2K viewsedited  18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ