Get Mystery Box with random crypto!

1ሺህ 167 ኢትዮጵያውያን ወንዶች ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል በዛሬው ዕለት በሶስት | TIKVAH-MAGAZINE

1ሺህ 167 ኢትዮጵያውያን ወንዶች ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል

በዛሬው ዕለት በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳኡዲ አረቢያ በችግር ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1ሺህ 167 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱ ዜጎች መካከል 1ሺህ 165 ወንዶች ሲሆኑ 2 ደግሞ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው ተብሏል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉም ተገልጿል።

ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 7968 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@tikvahethmagazine