Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የሰርጥ አድራሻ: @mirttshefoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 32.56K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-06-13 01:34:25
ግን ለምን
የውስጤን ዘርግፌ እኔነቴን ብሰጥሽ
ምኞት፣ፍላጓቴን ገልጬ ብነግርሽ ፣
ፍቅሬን አጣጥለሽ ዝቅ አርገሽ ገመትሽው
መውደዴን አርቀሽ ማፍቀሬን ጠላሽው ።
        
መውደዴን አርክሰሽ ማድነቄን አቅልለሽ ፣
መቅረቤን አውግዘሽ እንዳልነበር አርገሽ ፣
ከጓዳና ወጠሽ አጋልጠሽ ሰጠሽው ፣
ማፋቀሬን ገደልሽው ።

https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
3.4K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  22:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 01:30:05 የአምላክህ ልጅ ነህ!

በእራስህ እንደምታፍር ይሰማሃል? ቀና ማለት ትልቅ ሸክም ሆኖብሃል? ውስጥህ ተረብሿል? ብርታት አጥተሃል? ዋጋህን ለመጨመር ተቸግረሃል? እራስህ ላይ ለመሰልጠን፣ እራስህን ለመግዛት አቅም አንሶሃል? እንግዲያውስ ይህን ንግግር ከልብህ አንስተህ በቃልህ ደጋግመህ ለእራስህ ንገረው፦ "ልበ ብርቱ መንፈሰ ጠንካራ፣ ለአለም ፈተና የማልበገር በእግዚአብሔር የምታመን፣ በአምላኬ መፅናትን የተማርኩኝ፣ በሙላት መፈጠሬ የማያጠራጥረኝ፣ በአሁን ስቃዬ እራሴን የማልለካ፣ አቅሜን የማልገድብ፣ መማር፣ ማወቅን፣ መንቃትን የማላቆም፣ ከእራሴ የሚልቅ፣ ከከባቢዬ የገዘፈ ለሀገር፣ ለአህጉርና ለአለም የሚበቃ ብሩህ ተስፋ ያለኝ፣ እምነቴን ዋና ስንቄ፣ የአምላኬን መንፈስ ጋሻዬ አድርጌ የምጓዝ፣ ስብራቴን ለማከም ማንንም የማልጠብቅ፣ በአምላካዊ ፍቅር በታደለኝ ጥበብ እራሴን የማድን እኔ ብርቱ የአምላኬ ልጅ ነኝ።" ብለህ ለእራስህ ደጋግመህ ተናገር።

አዎ! ጀግናዬ..! አንተ የአምላክህ ልጅ ነህ! የደጉ አባትህ፣ ፍቅር የሆነው፣ በፍቅር የሚያኖርህ፣ ፍቅሩን በየቀኑ የሚገልፅልህ፣ ውሎህን የሚያሳምርልህ፣ መንገድህን የሚጠርግልህ፣ መዓትህን የሚያርቅልህ አዎ! የእርሱ የህያው አምላክህ ልጅ ነህ። አለምን አትፍራ፣ ህይወትህን ከልክ በላይ አታግዝፋት፤ በምድራዊ ዱብዳ፣ በጊዜያዊ ችግር፣ በጊዜያዊ እጦት አትሸማቀቅ። በተለዋዋጭ አለም ፍፁም የማይለዋወጥ በፊትም፣ ዛሬም፣ ነገም ያው ፍቅር የሆነ አምላክ እንዳለህ አስታውስ። በእርግጥ አለም ውስጥ ብዙ አይንን የሚስቡ፣ ለጆሮ የሚጥሙ፣ ስሜትን የሚገዙ፣ ለማድረግ፣ ለመስራት ብሎም የእራስ ለማድረግ የሚያስጎመዡ አያሌ ነገሮች ይኖራሉ። ነገር ግን እንደሚጠበቁት ጥምን አይቆርጡም፤ አምሮትን አያወጡም፤ ስሜትን አያረኩም፤ ውስጣዊ ሰላምን አይሰጡም።

አዎ! ከድካምህ ለማረፍ መንፈስህን ጠግን፣ ከሩጫህ ፋታ ለመውሰድ በእግዚአብሔር መንገድ ተመላለስ፤ ህይወትህን እንደ አዲስ ለማነፅ የአምላክህን ድንቅ ስራ፣ የፈጣሪህን የስነ-ፍጥረት ጥበብ አስተውል። ጨለማን እንዲሁ በዝምታ በአርምሞ ፈጠረ ጨለማም ሆነ፤ ብረሃንንም በቃሉ በነቢበ ብረሃን ይሁን አለ ብረሃንም ሆነ። በዝምታ ረቂቁን ጨለማ የፈጠረ፣ በቃሉ ብቻ አስደናቂውን ብረሃን ወደ ምድር ያመጣ አምላክ ላንተ ህይወት ብረሃን መስጠት፣ ጨለማህን መግፈፍ ምንያክል ቀለሉ እንደሆነ አስብ። ነገር ግን በእርሱ ላይ ያለህን እምነት ይፈልጋል፤ ፅናትህን፣ ፍፁም እርሱን ማስቀደምህን፣ ከውስኗ ሰውኛ አቅምህ በተሻለ ስልጣኑን ለእርሱ እንድትሰጥ ይፈልጋል። አምላክህን አስቀድም ህይወትህንም አንተ ቅደም፣ አንተ አሸንፋት።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
3.1K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  22:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 01:29:34 ድጋሜ አታገኘውም!

ተሳስተህ የምትማረውን ትምህርት ድጋሜ አትማረውም፤ ያመለጠህን ጊዜ ድጋሜ አታገኘውም፤ በብዙ ጥረት የምታካብተውን ልምድ እንደገና አታገኘውም። ምድርን መሰናበቻህ ሲቀርብ ከምትነቃ አሁን በጊዜ ንቃ፤ ድጋሜ ለማታገኛቸው ስጦታዎችህ ትኩረት ስጣቸው፤ ውድነታቸውን ውድ ነገር በማድረግ ግለፅላቸው፤ ልብህን ለማሞቅ ቁጭ ብለህ መቆዘም ሳይሆን ተነስተህ የፈለከውን አድርግ። ሽልማት እያሰብክ እራስህን አታድክም፤ ቁስ ባትሸለም ውስጣዊ ሃሴትን የሚሸልምህ፣ የማያልቀውን ደስታ የሚያድልህ ተግባር ውስጥህ አለ። የምትናፍቀው ለውጥ፣ የምትመኘው ከፍታ፣ የምታስበው ስኬት በጥረትህ ልክ የሚመጣ ጉዳይ ነው። ተስፋን በብዙ ተንከባከበው፤ ለእምነትህ ድጋፍ ሁነው፤ የታላቅነት አመለካከትህን አጥብቀህ ያዘው፤ በእራስመተማመንህን ከምንም በላይ ዋጋ ስጠው፤ ዛሬህ ላይ በሚገባ ሰልጥን። ታሪክ ሆኖ በኩራት የምታወራበትን ቅፅበት አሁን መፍጠር ጀምር።

አዎ! ጀግናዬ..! ድጋሜ አታገኘውም፤ እንደገና አይመጣምና እያንዳንዱን የህይወት ስጦታህን፣ ቀንህን፣ ጤናህን፣ ሰላምህን፣ እውቀትህን፣ ጥበብህን፣ ማስተዋለህን፣ ብለሃትህን እንደ ብርቅ፣ አላቂና ውድ ነገር በአግባቡ ተጠቀመው። እንዲሁ እንደ ቀላል የሚባክን፣ ዋጋ የሌለው፣ ተስፋህን የማያጎላ፣ ለምኞትህ የማያቀርብህ ስጦታ እንደማይሰጥህ አስብ። በብረሃናማው ጊዜህ በሚገባ መኖር ከቻልክ ፀሃይህ መጥለቅ ስትጀምር፣ የድካም ዘመንህ ሲመጣ፣ ተፈጥሮ ስትሰለጥንብህ አንዳች የሚያስቆጭህ ነገር አይኖርም። የአሁኗን ቅፅበት ድጋሜ የመኖር እድል እንደማታገኝ መረዳትህ ብቻ በሙሉ ስስት እንድትጠቀማት ሊያደርግህ ይገባል።

አዎ! አስቸኳይ ሃላፊነት፣ ጊዜ የማይሰጥህ ተጠያቂነት፣ ድጋሜ የማይፈፀም ግዴታ እንዳለብህ አስታውስ። ህይወትን በሙላት የመኖር ሃላፊነት፣ መኖርህን ትርፋማ የማድረግ ግዴታ፣ ለእያንዳንዱ ቅፅበቶችህ፣ ለእያንዳንዱ ስጦታዎችህ ዋጋ የመስጠት፣ ትርጉም የመፈለግ ተጠያቂነት አለብህ። የሚጠይቅህም ሌላ ማንም ሳይሆን የእራስህ እውነተኛ ማንነት፣ ውስጥህን በሃሴት ለመሙላት፣ ከፍታህን ለማምጣት የሚታገለው ድንቁ ማንነትህ ነው። ቀላል ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን በየትኛውም መንገድ ሊደረግ ይገባል። መጨረሻህ ቁጪት፣ ስቃይና የልብ ስብራት እንዲሆን ካልፈለክ አሁን ነቃ በል፤ ህይወትህን ሙሉ አድርጋት፤ በእያንዳንዱ ቀናት ውስጥ በመኖርህ፣ የእራስ ፍለጋ ጉዞ ውስጥ በመሆንህ፣ እራስህን ለማሳደግ በመጣርህ በእርግጥም ኩራት ይሰማህ፤ በምርጫህና በውሳኔህ ሃሴት አድርግ፤ በማንነትህ ሁሌም ደስ ይበልህ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.7K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  22:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 17:56:30
ህፃን እድላዊት ፍቅሩ ገና የስምንት ወር ልጅ እያለች ነበረ በደምዋ ውስጥ የHiv ቫይረስ የተገኘባት ። ከዛን ግዜ ጀምሮ በዚህ በለጋ እድሜዋ ከፀረ-Hiv መዳኒት ጋር እየታገለች መኖር የሕይወት እጣ ፋንታዋ የሆነባት የምታሳሳ ታዳጊ ህፃን ናት ።

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባት ከወገብ በታች ደግሞ ሙሉ ፓራላይዝድ በመሆኗ እናትዋ በወገብዋ አዝላት የዜሮ ክፍልን ጀምራ ከአንደኛ ክፍል ያቋረጠችና መማር እየፈለገች ከጓደኞቿ ተለይታ ከ6 ዓመት በላይ ከቤት ሳትወጣ መኖር ግድ የሆነባት ህፃን ናት።

ህፃን እድላዊት አሁን ላይ በብርሸለቆ የወታደር ማሰልጠኛ ካንፕ ውስጥ የምትኖርና ከአባትዋ ጡረታ በወር 1000 ብር በሚገኘው ገቢ ስለምትኖር እንኳን በቂ ሕክምና ለማግኘት ቀርቶ ለምትወስደው ፀረ - Hiv መዳኒት እራሱ የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት ያልቻለች ልብን የምትሰብር ታዳጊ ልጅ ናት ።

እድላዊት ቢያንስ ሕክምና ማግኘት ብትችል መራመድ የምትችል ልጅ ስለሆነች ቀሪ እድሜዋ በተስፋ የተሞላ እንዲሆንላት በፈጣሪ ስም ስለ እድላዊት እማፀናችዋለሁ ።

እዚህ ቻናል ላይ እንኳን ያለነው 43 ሺህ ሰው እያንዳንዱ 1 ብር ቢልክ አስባችኋል 43ሺህ ብር ብዙ ነገር ያግዛታል ።

ወ/ሮ አታክልት ታደሰ(እናት) #1000149256532 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

0906852090 አትክልት ታደሰ
3.7K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 12:13:22
➦ ፈጣሪን ሀብት ገንዘብ ስጠኝ ብሎ ብቻ ከመለመን የምሰጠኝ ነገር መጥፊያዬ እዳይሆን አንተ ጠብቀኝ ብሎ ፀሎት ማረጉ የተሻለ ነዉ ➟ ወንድማችን አዲስ ባጃጅ ገና ታርጋ እንኳን ያልገባለት 0:0 ከመሸጪያዉ ቦታ ገዝቶ አዲስ ቤት ተከራይቶ ለቤቱ ምንጣፍ ገዝቶ እየሄደ ቤቱም ሳይደርስ ባጃጇም ስራ ሳትጀምር በመንገድ ቀረች ወቶ ከመቅረት ፈጣሪ ይጠብቀን
4.7K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 09:30:50 ለዛሬ ተቆጠቡ!

ለዛሬ ተቆጠቡ እራሳችሁን ቆጥቡ ፤ ነገሮች ላይ ጠንቃቃ ለመሆን ሞክሩ ፤ ከተለመደው አድካሚ ውሎ ፋታ ውሰዱ ፤ ከሚያሳስበችሁ ብሎም ከሚያስጨንቃችሁ ጉዳይ ገለል በሉ ፤ እራሳችሁን ያዝ ፣ ጠበቅ ፣ ቆንጠጥ አድርጉት ። የሁልጊዜ ሩጫችሁ ውጫዊ እይታን ለማግኘት ከሆነ ወደ እራሳችሁ ተመለሱ ፤ የዘወትር ፀሎታችሁ ከሰው በታች ላለመሆን ከሆነ ከዛ በላይ ብቁ መሆን ፣ ትርፋማ መሆን ፣ እሴት መጨመር ላይ አተኩሩ ። በምርጫችሁ ጎዳና ላይ በተለየ ብርታት ስለሚያስቀምጣችሁ ፤ አዲስ ልዩ ብሩህ ውሎን ስለሚያድላችሁ ፤ እድገታችሁን እንድትመለከቱ ስለሚያደርጋችሁ ፣ ዋጋችሁን እንድትጨምሩና እንድታድጉ ስለሚያስችላችሁ በየጊዜው በፍቅር ለሚታደሏችሁ ቀናት ደስ ይበላችሁ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ለዛሬ ተቆጠብ! ለዘመናት አይተህ ፣ ለረጅም ጊዜ ተከትለህ ፣ ለጊዜያት አስበሀው ካልቀየረህ ፣ እሴት ካልጨመረልህ ፣ ዋጋህን ከፍ ካላደረገልህ ሰውና ጉዳይ እራስን ቆጥብ ። ቁጠባ ጨርሶ እንደመተው አይደለም ። እንደ ቀድሞ ሙሉ በሙሉ ማይጠቅሙ ነገሮች ውስጥ ተዘፍቆ ማስተዋልን ከማጣት ይልቅ በቅርብ ርቀት ሆኖ ነገሩን በአንክሮ መመልከት ፣ በጥልቀት ማጥናትና በተለየ መንገድ መረዳት ነው ። ቁጥብነት ያስከብራል ፤ ቁጥብነት ጥንቃቄን ያላብሳል ፤ ስሜታዊነትን ያስታግሳል ፤ በሰዎች ዘንድ የተለየ ስፍራን ያሰጣል ፤ ዋጋን ይጨምራል ፤ ለመመርመር እድል ይሰጣል ። እራስን መግዛት ፣ እራስ ላይ መሰልጠን በጭፍን ከመነዳት ፣ በጭፍን ከመፍረድ ፣ በጭፍን ከመኮነን ይታደጋል ።

አዎ! ዛሬ ለፍላጎትህ የምትቆምበት ፣ ለውስጣዊ እርካታህ ቅድሚያ የምትሰጥበት ፣ በማንም በጭፍን ከመነዳት የምትወዳውንና የሚያስፈልግህን የምትመርጥበት ቀን ነው ። ጨከን ማለትን ተለማመድ ፤ ከባዱን መንገድ ለመምረጥ እራስህን አዘጋጅ ፤ አውቀህ ለመፈተን ፣ በተለየ አቅጣጫ ለመጓዝ ፤ እራስህ ላይ እርምጃ ለመውሰድ እራስህን አደፋፍር ። ጥራት ያለው ፣ የተረጋጋ ፣ በአንድ አቅጣጫ የሚጓዝ ፣ ትርፋማና አስደሳች ህይወትን ስለመምራት ማሰብ ጀምር ። የእስካሁኑ ሩጫህ ካልቀየረህ ፣ የእስካሁኑ ድካምና ልፋትህ ስሜት ካልሰጠህ ቆም ብለህ እራስህን ጠይቅ ፤ ምን እንደጎደለህ እወቅ ፤ ለምን እንደሆነ ተረዳ ። የምትለወጠውና የምታድገው ያለማቋረጥ ስለሮጥክ ፣ ጠንክረህ ስለሰራህ ፣ ያለእረፍት ስለደከምክ ብቻ ሳይሆን በዋናነት ጠንክረህ ስላሰብክ ፣ አስተውለህ ስለምትራመድና በየጊዜው እራስህን ስለምትመዝን እንደሆነ ተረዳ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
5.3K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 09:27:25 ምንድነው የምትሰጠው?

እንደ አንድ ጥሩ ሰው ፣ እንደ አንድ ብርቱ ለሰው አዛኝ ሰው ፣ እንደ አንድ ቅንና የዋህ ሰው ይበልጥ የሚያስጨንቅህ ነገር ምንድነው ? የምትሰጠው ወይስ የምትቀበለው ? የምታደርገው ወይስ የሚደረግልህ ? የምታስገኘው ወይስ የምታገኘው ? የምታስጨምረው ወይስ የሚጨመርልህ ? ለየትኛው ይበልጥ ትኩረት ትሰጣለህ ? ልብህ ለየትኛው ያደላል ። መቀበል የለመደ ሰው ደስታው ሁሌም የሚሰጠውን ነገር በማሰብ የሚያገኘው ነው ። መስጠትን የለመደ ደግሞ ሲሰጥ ብቻ የሚያገኘውን ደስታ በሚገባ ያውቀዋል ። አዲስ ነገር ሲደረግልህ እንደምትደሰተው ሁሉ አዲስ ነገር ለሰዎች ማድረግም ደስታን ሊሰጥህ ይገባል ። የጠበከው ነገር ሲከናወንልህ ልብህ ሃሴት ያደርጋል ፤ ብዙዎች የሚጠብቁትም ባንተ በኩል ሲደረግላቸው ያንተን ስሜት አዳምጥ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ምንድነው የምትሰጠው ? እንደ ማንኛውም ሰው "ምን አለኝና" አትበል ። ምንም ባይኖርህ መስጠት እንደምትችል መለማመድ ይኖርብሃል ። ነገር ግን ማንም ምንም ሳይኖረው ፣ ምንም ሳይሰጠው ፣ ምንም የሚያካፍለው ሳይታደለው የተፈጠረ ሰው የለም ። ትኩረታችን ሁሉ ሰዎች ላይ ሆኖ ያለንን ነገር ግን ማስተዋል ያልቻልን ብዙዎች ነን ። ባለው ነገር የሚመካ ፣ በተሰጠው ነገር ደረቱን የሚነፋ ሰው ቢኖር አለኝ የሚለው ነገር ሲጠፋ ተሽመድምዶ እንደሚቀመጥ ምንም ጥርጥር የለውም ። ኩራትህ በተሰጠህ ፣ ባገኘሀው ወይም በታደልከው ሳይሆን በምትሰጠው ፣ በምታጋራውና በምታካፍለው ይሁን። የሚያኮራህ ነገር አንተ ጋር ያለ ነገር ሳይሆን ካንተ የሚወጣ ነገር ይሁን ።

አዎ! ሌላው ባይኖርህ ተስፋ አለህ ፣ ብርታት አለህ ፣ ቅንነት አለህ ፣ ደግነት ፣ መልካምነት ፣ የዋህነት አለህ ። ሰዎችን ከዚህ በላይ ለረጅም ጊዜ የሚጠቅማቸው ነገር የለም ። የምትሰጣቸው ገንዘበ ለጊዜው ችግራቸውን ይፈታል ፤ የምታጋረቸው ንብረት ለተወሰነ ጊዜ የተሻለ ህይወት ያሳያቸዋል ፤ በየጊዜው የምትመግባቸው የተስፋ ቃል ፣ እንደ ቀላል ጆሮ ሰተህ የምታዳምጣቸው ፣ ሲፈልጉህ አለሁላችሁ የምትላቸው ፣ ብርታትን የምታካፍላቸው ነገር ግን ከምታስበው በላይ ዋጋህን ይጨምራል ። ሁሌም ቢሆን ከምትቀበለው የምትሰጠውን አስበልጥ ፤ ከሚደረግልህ ለሰዎች የምታደርገውና የምታካፍለው ነገር ላይ አተኩር ፤ መስጠትን ፣ ማጋራትን ልመድ ፤ ውስጥህንም በመትረፍረፍ ሙላው ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
3.9K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 09:08:09 እራስህን ተመልከት!

የትኛውም ግንኙነት ውስጥ ከመግባትህ በፊት እራስህን ተመልከት ፤ ወዴትም በጭፍን ከመጓዝህ አስቀድሞ እራስህን መዝን ። እራሱን የማይወድ ሰው ሁሌም ፍቅርን ከሰው እየጠበቀ የሚሰቃይ ሰው እንደሆነ አስታውስ ። ግንኙነት ድርሰቶች ላይ እንዳለው ፍፁም እንከን አልባ አይደለም ፤ የተለያዩ የፍቅር ፊልም ላይ እንደሚገለፀው ሙሉ ማንነትህን የሚቀማህም አይደለም ። ድርሰት ከእውነታው ይልቅ የሰውን ትኩረት ለመሳብ የሚደረግ ነገር ይበዛዋል ። ደራሲው በፈለገው መልኩ ሊማርክህ ይችላል ፣ ተዋንያኖቹም እንዲሁ ያደርጋሉ ። ትክክለኛው ያንተ ህይወት እውነታ ግን ከዚህ የወጣ ነው ። እራስህን ሳትመለከት ፣ ደረጃህን ሳትረዳ ፣ ማንነትህን ሳታውቅ ፣ መስጠት የምትችለውን ሳትገነዘብ ፣ የምትቀበለውን ብቻ እያሰብክ በጭፍን የምትገባበት የትኛውም ግንኙነት አንደኛው የውድቀትህ ምክንያት ነው ።

አዎ! ጀግናዬ..! እራስህን ተመልከት! እራስህን በጥልቀት ጠይቀው። ሌላ ተጨማሪ ሰው ወደ ህይወትህ ከማስገባትህ በፊት ለእራስህ ያለህን ቦታ ገምግም ፤ ከሌላ ሰው ጋር ከመወዳጀትህ በፊት ከእራስህ ጋር ያለህ ወዳጅነት ምን እንደሚመስል እወቅ ። ለእራሳችን የማንሰጠውን ክብር ፣ ቦታና እንክብካቤ በተወሰነ ጊዜያት ለምናውቀው ሰው እየሰጠን መጨረሻችን ህመምና ስቃይ ሆኖ የሚገኝበት ጊዜ ጥቂት አይደለም ። አንተ ጨክነህ እራስህን አሳልፈህ ከሰጠህ ቦሃል ማንም አንተን የማዳን ግዴታ የለበትም ። እውነተኛ ግንኙነትና የድርሰቱ አለም በብዙ መልኩ እንደሚለያይ ካልተረዳህ እራስህን ከፉ ወጥመድ ውስጥ እያስገባህ ነው ። ከማንም ከምንም በፊት ቀዳሚው ለእራስህ የምትሰጠው ፍቅር ፣ ክብርና ቦታ ነው ። ሌላው የማጋራት ደረጃው ላይ ብቻ ስትደርስ የምታደርገው ነገር ነው ።

አዎ! ጀግኒት..! አንቺ ያልወደድሽውንና ያልተቀበልሽውን ማንነትሽን ሌላው እንዲወደውና እንዲቀበለው አትታገይ ። እራስሽን መጠገን ፣ ተፈላጊ ሰው መሆንሽን ማስመስከር ፣ ለምትፈልጊው ነገር ብቁ እንደሆንሽ ማረጋገጥ የእራስሽ ድርሻ ነው ። እራስሽን ደካማ የሚመጣውን ጠንካራ ፣ እራስሽን ተረጂ የሚመጣውን ሰው ረጂና ደጋፊ አድርጎ መሳል አቁሚ ። እራስሽን ካላጠነከርሽ ማንም ቢመጣ ሊያጠነክርሽ አይችልም ፤ እራስሽን ካልረዳሽ ማንም እስከመጨረሻው የሚረዳሽ የለም ። ለእራስሽ መወገን ካልቻልሽ ወገን እንደሌለሽ ቁጠሪው ፤ ምክንያቱም አንድ ቀን ብቻሽን መቅረትሽ አይቀርምና ነው ። ህይወትን ልክ እንደ ድርሰት ሳይሆን እንድ እራሱ እንደ ትክክለኛ ህይወት መኖር ጀምሪ ። ያየሽውን ሁሉ ለማድረግ ሳይሆን የሚገባሽንና የሚጠቅምሽን ለማድረግ እራስሽን አዘጋጂ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.6K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 09:06:26 እብድ ተባል!

እብድ አትሁን ነገር ግን በሚያዩህ እብድ ተባል ፤ የለየለት አለሌ አትሁን ነገር ግን ለሚከታተሉህ አለሌ ሁን ፤ ብቸኛ አትሁን ነገር ግን ለሰዎች ብቸኛ ሰው አልባ ሁን ። ትክክለኛው ማንነትህ አንተ ለእራስህ የሆነከው እንጂ ለሰዎች ሆነህ የምትታየው አይደለም ። የእብደት መለኪያ ብዙ ቢኖርም የተለየ መንገድ ስለመረጥክና እራስህን እንደ ጀግና ስለተመለከትክ እንደ እብድ ብትቆጠር ለእራስህ ትክክለኛው መንገድ ላይ እስከሆንክ ድረስ ግድ አይስጥህ ፣ ብዙ አትጨነቅ ። በማይመለከትህ ጉዳይ ከሰዎች ባለማውራትህ ፣ ወሬያቸውን ባለማዳመቅህ ፣ ከማይመጥንህ ስፍራ በመራቅህ ፣ የብቻኝነት ደሴትህን በመውደድህ ዝምተኛ ፣ ብቸኛና ሰው እንደማትወድ ልትቆጠር ትችላለህ ፤ ነገር ግን ከእራስህና ከአምላክህ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እስካለህ ድረስ ብቸኛ ልትሆን አትችልም ።

አዎ! ጀግናዬ..! የተባልከውን አይደለህምና እብድ ተባል ፤ የሆንከውን ነህና የማይሆን ስም ይውጣልህ ፤ እራስህን ታውቃለህና ትቺት ይቅረብብህ ፤ በፍፁም አትጨነቅ ። ባለን አጭር የመኖር ጊዜ ስለምንባለው ፣ ስለሚወራብን ጉዳይ ተጨንቀን ህይወታችንን ይባስ ልናሳጥራት አይገባም ። እራስህን ስታውቅ በኩራት መኖር ትጀምራለህ ፤ የት መድረስ እንደምትችል ፣ ደረጃህ ምን እንደሆነ ስታውቅ የልብህ ሙላት የአሰናካዮችህን አይን ያርቅልሃል ። ቀላልም ይሁን ከባድ እራስህን ሆነህ ለእራስህ መታገል የግድ ነው ። አሉታዊ ንግግርን መዝራት የለመደች ምላስ ለማንም አትመለስምና አስቀድሞ መንፈስን ማጠንከር ፣ እራስህን ማበርታት ያስፈልጋል ።

አዎ! ምንም ስታደርግ የማይጥማቸው ሰዎች ካሉ ፣ አንድ ነገር በከወንክ ቁጥር ለተቃውሞ የሚንደረደሩ ሰዎች ካጋጠሙህ ፣ ቀላሉን "በርታ" ማለት ከብዷቸው ከባዱን "አትችልም ይቅርብህ" ለማለት የሚሯሯጡ ሰዎች ወደ ህይወትህ ቢመጡ ማዳመጥ ሳይሆን ለአፍታም ጊዜ መስጠት አያስፈልግህም ። የሚለጠፍብህ ስም ፣ የሚወራብህ ወሬ ፣ የሚነገርብህ ጉዳይ አንተን እንደማይገልፅህ በተግባር አሳይ ። "እሱ እብድ ነው ፤ የሚያደርገውን አያውቅም ፤ የሚመክረው ሰው የለውም ፤ ዝም ብሎ ይለፋል ።" መባል የእንቅስቃሴህ ማሳያ ነው ። ምክንያቱም የተለየ ተግባር ላይ ያልተሰማራ ፣ ባልተለመደ አቅጣጫ የማይጓዝ ፣ በመደበኛው መንገድ የሚመላለስ ሰው እንዴትም እብድ ሊባል አይችልምና ነው ። የምትባለውን ተወት አድርገህ ፈልገህ የሆንከው ላይ አተኩር ፤ ከተሰጠህ ስም በላይ ያለህበት ስፍራ ያሳስብህ ፤ በእራስህ መንገድ መዳረሻህን እራስህ ወስን ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.3K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 09:04:34 መነቃቃትህን እርሳው!

አዎ! መነቃቃትህን እርሳው ለእራስህ የገባሀው ቃል ላይ አተኩር ፤ ለስሜትህ መገዛት አቁም ማድረግ የሚገባህን በጊዜው አድርግ ፤ በምታየው ፣ በምትሰማው መማረክህን አቁም ፣ አይንና ጆሮህ ግብህ ላይ ይሁን ። መነቃቃት ጊዜያዊ ነውና እርሱን መጠበቅ ከጀመርክ ተግባርህም ጊዜያዊ እንደሚሆን አትጠራጠር ፤ እንድ ዲም ላይት (dem light) ስትነቃቃ የምታደርገው ሲደብርህ የምታቆመው ተግባር የት ሊያደርስህ ይችላል ? ወዴትስ ይወስድሃል? ወዴትም ። በድግግሞሽ ስሜት ፣ በተደጋገመ ውጤት ያደክምሃል ፤ የጠበከውን ሳይሆን የሆንከውን ያሳይሃል ፤ የምትፈልገውን ሳይሆን ያደረከውን ፍሬ ያመላክትሃል ። ከሁሉም በላይ ዲሲፕሊን (discipline) ፣ እራስን መግዛት ፣ እራስን መገሰፅ ፣ ላወጣሃቸው የእራስ ደረጃዎች መታምን ፣ ማንም ባያየንም ፣ ማንም ቃላችንን ባይሰማም ለእራሳችን ለገባነው ቃል መታመን ይኖርብናል ።

አዎ! ጀግናዬ...! መነቃቃትህን እርሳው! ዲሲፕሊንን አስቀድም ፤ ከስሜት በላይ መሆንን ተላመድ ፤ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ውስጥ ትርጉም ማግኘትን አዳብር ። ሲመችህ ብቻ በምትሰራው እንቅስቃሴ የሰውነት አቋምህ አይቀየርም ፤ ሲደላህ ብቻ በምታስበው ሃሳብ እራስህን አታሻሽልም ፤ የፈለከው ሁሉ ተሟልቶ በምታደርገው ተግባር ብቻ ወደፊት መጓዝ አትችልም ። አንዳንድ ሁኔታዎች ልፋት እንጂ ቶሎ ውጤት አይኖራቸውም ፤ ያደክሙሃል እንጂ የሚታይ ነገር አትመለከትባቸውም ፤ እለት እለት ስትደክም ትመለከታለህ እንጂ በፍፁም ጠብ የሚል ነገር አታገኝባቸውም ። የአሁን ድካምህን ሳይሆን የወደፊት ውጤትህን አስበህ ትታገላለህ ፤ የአሁን መረበሽህን ረስተህ የመጪው መረጋጋትህ ላይ ታተኩራለህ ። ቢዘገይም የምትናፍቃትን ብረሃን ትመለከታለህ ፤ ቢቆይም ተስፋ ያደረከው ደረጃ ላይ እራስህን ታገኘዋለህ ፤ ቢያደክምህም የለፋህበት ዋጋ ይገፈልሃል ።

አዎ! ዲሲፕሊን ቀላል አይደለም ፤ ዋጋ መክፈል ፣ ወዶ መሰቃየት ፣ ውጤት ሳይኖር መድከም ፣ በማይታይ ትግል መጠመድ ፣ እለት እለት ከእራስ ጋር መሟገት ፣ ውጪ የምታየው ሌላ ውስጥህ የምታየው ሌላ ሲሆን የስሜትህን መቀያየር መቆጣጠር ከባድ ነው ። በዚህ ሁሉ ውጣውረድ ውስጥ ለእራስህ መታመን ካልቻልክ ይባስ ነገሮችን ታከብዳቸዋለህ ። የሚሰራ ሰው ፣ ለምን የሚሰራውን ስራ ከብዙዎች መርጦ እንደሚሰራው ካላወቀ በስሜቱና በጉልበቱ እየተጫወተ ነው ። ገንዘብ ለማግኘት ፣ ህይወትን ለማሸነፍ ፣ ሌሎችን ለመርዳት ፣ ህልሙን ለመኖር ሊሆን ይችላል ። ምክንያቱን በማነቃቂያው ቦታ የሚያስቀምጥ ከሆነ ዲሲፕሊንን የማያዳብርበት ፣ እራሱ ላይ የማያተኩርበት ፣ በምክንያቱ የማይገዛበትን አጋጣሚ አይኖረውም ። ለተግባርህ ጠንካራ ምክንያት ይኑርህ ፣ ለምታደርገው ነገር ዋጋ የሚያስከፍል ፅኑ ፍላጎት ይኑርህ ፤ በመነቃቃት ሳይሆን በምክንያትህ ተመራ ፤ ለምክንያትህ ብለህ እራስህን ግዛ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.1K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ