Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የሰርጥ አድራሻ: @mirttshefoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 32.43K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 35

2023-01-31 02:09:08
#_ዝም_ብለሽ_ስሚኝ
አንድ ቀን እንደኔው የፍቅር ትርጉሙ
ሰው ወደሽ ካየሽው ስቃዩ ህመሙ
ላንቺ ብዙ እንደሆንኩ ያኔ ይገባሻል
ስነግርሽ ዝም ያልሽው ዛሬ ይቆጭሻል

አሁን ምን ያደርጋል ቢያዝኑ ቢቆጩ
ፍቅር አገርሽቶ በእንባ ቢራጩ
ያ የኔ ምስኪኑ እንግልቱ ልቤ
የፍቅርን ትርጉም ባየው ሰው ቀርቤ
እኔም ቆጨኝ ዛሬ ያኔ ያለቀስኩት
ሌላ ሌላ ስትይ አንቺን አንቺን ያልኩት
#_ዛሬ_ግን
ልቤም ልብ ገዛ ሌላ ሰው ወደደ
አንቺን ለሰው ትቶ እሱ ከሰው ሄደ
በቃህ ሂድ ብለሽው ልቤ ሄዷል ቆርጦ
ይዟል አንቺን ትቶ የራሱን ሰው መርጦ
እኔስ የሰው ሆንኩኝ አንቺም ሰው ፈልጊ
ይመለሳል ብለሽ ተስፋ እንዳታደርጊ
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
5.2K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  23:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 01:53:26 18 40 60 መርህ!
18 40 60 Principle!

በአስራ ስምንት ዓመትህ ሰዎች ሁሉ ስላንተ የሚያወሩ ፣ አንተን ብቻ የሚመለከቱ ፣ የሚከታተሉህ ፣ የዘወትር ጉዳያቸው አንተ እንደሆንክ ታስባለህ ። በዚህም ልክ ከእራስህ በላይ ሰዎች ስለሚሰጡህ ስምና ከእነርሱ ስለምታገኘው ምላሽ በመጨነቅ ጊዜህን ታባክናለህ ፤ እራስህን ከማስደሰት በላይ ለሰዎች ደስታና እርካታ ትልቅ ዋጋ ትከፍላለህ፤ ሰው ምን ይለኛል በሚል ሃፍረት ትታሰራለህ ፤ ነፃነትህን ለማወጅ ባሰብክ ቁጥር የሰው ምላስ ከፊትህ ተደቅኖ ትመለከታለህ ፤ ባጠቃላይ ህይወትህ በሙሉ ለሰዎች በሚከፈል መሱዓትነት ይሞላል ። በአርባ ዓመትህ የሰው ነገር ምንም አይመስልህም ፤ ምንም ብትባል ግድ አይሰጥህም ፤ ስለፈለጉት ቢያወሩብህ ፣ ስምህን ቢያጠፉ ፣ ስራህን ቢተቹ ፣ አንተን ቢነቅፉህ ምርጫቸው እንደሆነ ይገባሃል ። በቀደሙት አመታት ሲያስጨንቁህ የነበሩ ጉዳዮች ማስጨነቃቸውን ያቆማሉ ፤ ሌላ የተለየ አጀንዳ ውስጥ ትገባለህ ። በስልሳ ዓመትህ የሁለቱንም ልዩነት ማመዛዘን ትጀምራለህ ፤ ለሰዎች ብለህ ያጣሀው ነገር ካለ በእርሱ ትቆጫለህ ፤ ማንም ግድ በማይሰጠው ጉዳይ ስትጨነቅ እንደነበር ታስተውላለህ ፤ የሰዎች ስጋትና ፍራቻ ሁሉ የውሸት እንደነበር ይገባሃል ።

አዎ! ጀግናዬ..! መርሁን አስተውል ፤ በሚገባ ተረዳው ። ብዙዎች ስላላወቁት ይሸወዳሉ አንተ ግን ካወከው ዘንዳ ፣ ከተረዳሀው ፣ ከገባህ ለመተግበር ወደኋላ አትበል ። ማንም ሰው ግድ ለማይሰጠው ጉዳይ እየፈራህና እየተጨነክ አትኑር ። ያዩኛል ፣ ይከታተሉኛል ፣ ይተቹኛል ፣ ምን ይሉኛል ብለህ የምትጨነቅላቸው ሰዎች በሙሉ የእራሳቸው የማያልቅ ጉዳይ አለባቸው ። ማንም ያንተ አዲስ ነገር መጀመር ፣ በተለየ መንገድ መጓዝ ፣ በአዲስ አቋም መታደስ አያሳስበውም ። ሁሉም የግሉ ሩጫ ላይ ነው ። ምናልባት በአጋጣሚ ሲያይህ የመጣበትን ቃል ሊሰነዝርብህ ይችላል ከዛ ቦሃላ ግን ትዝም አትለውም ። እያንዳንዱ ሰው በግል ጡዘት በተጠመደበት ጊዜ አይኖች ሁሉ እኔ ላይ ናቸው ብለህ አትሸወድ ።

አዎ! ሰበብ አታብዛ ደስታ የሚሰጥህን ፣ ያመንክበትን ፣ የሚጠቅምህን ነገር በጊዜ አድርግ ። ህይወትህን በፍረሃት አትሰራት ፤ መኖርን በማይሆን ገደብ አትከልላት ። በትንሹም ቢሆን ጥረትህን ጀምር ፤ ደስታህን ወደ መፍጠር ተሸጋገር ፤ የእራስህን አለም አበጃጅ ፤ ፈጣሪህ ያይሃል ፤ አምላክ ያውቅልሃል ፤ ይረዳሃል ፤ ይቀድምልሃል ። ስለመጪው ጊዜ ቁጪትና ብትስጪት የምትጨነቅበት ምክንያት የለህም ። በአጋጣሚ ያገኘህና የተመለከተህ ባላወቀህ መጠን ሊናገር ይችላል ፤ አስቦና ፈልጎ የሚመለከትህ ግን በእርግጥም ሊደግፍህ እንደሚመጣ አትጠራጠር ። ልዩነት መፍጠሩን አሁኑኑ ጀምር ፤ በልብህ የያዝከውን ፣ በአዕምሮህ ያነገብከውን ሃሳባዊ አለም ከምድራዊው ተጨባጭ አለም ጋር ቀላቅለው ። የመጣው ይምጣ ፤ የሆነው ይሁን ፤ የማይቀር ነገር እንደሆነ የመጣውን ተቀበል ። በእራስህ ተመማመን ፤ ለእራስህ ብለህ ድፈር ፤ ጠንክር ፤ ለእራስህ ብለህ ህይወትህን በሙላት ኑር ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
4.1K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  22:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 01:50:18 ግለትህ ይነዳሃል!

እውቁ አሜሪካዊ ፀሃፊ ኖርማን ቪሰት ፒል የግለትን ሃይል በዚህ መልኩ ይገልፃል ። "ግለት በመካከለኛነትና በስኬት መካከል ያለውን ልዩነት ያሳያል ።" ተነሳሽነት ፣ ሞቅታና ግለት ወሳኞቹ የስኬት ግበዓቶችህ ናቸው ። በብዙ አመራጭ ንቁና ዝግጁ ልትሆን ትችላለህ ግለትህና የማያባራው ውስጣዊ ፍላጎትህ ግን ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ ለተሻለ ስፍራ የሚያበቃህ ነው ። ሁሉም ሰው በአንድ አይነት አስደሳችና የተነቃቃ ስሜት መቆየትን ይፈልጋል ፤ ይህ የሚሆነው ግን ያለምንም የሃሳብ መዛባት መቆየት ሲችል ብቻ ነው ። ልቡ ያማረውን ፣ ውስጡ ያሰኘውን ነገር ከማድረግ ወደኋላ የማይል ሰው የየእለት ግለትና ንቃት ያስፈልገዋል ። ሴሜቱን በእራሱ ማስተካከል የሚችል ፣ ለእራሱ የተነሳሽነት ምንጭ የሚሆን ፣ እራሱን በተሻለ ደረጃ ብቁና ዝግጁ የሚያደርግ ፣ በማያቋርጥ ጥረት የሚያምን ፣ በየእለቱ 1% እያደገ ፣ እየጨመረ መጓዝ የሚችል ። ውስጥህ የተቀጣጠለው ግለት ለወጥና ቀጣይነት ላለው እርምጃህ እጅጉን ወሳኝ ነው ። ማንንም ፣ ምንም በመጠበቅ የሚባክን ጊዜ እንዳይኖር ያደርግልሃል ።

አዎ! ጀገናዬ..! ግለትህ ይነዳሃል! Your enthusiasm will drive you! ተነሳሽነትህ ወደፊት ይገፋሃል ፤ ንቃትህ በየጊዜው ለተሻለ ስፍራ ያበቃሃል ። የማያባራ ሃሳብ ይዘህ ግለትን ባትጨምርበት የሃሳብ ቋት ከመሆን አታመልጥም ። ትልቅነት በሃሳብ ሳይሆን በመሆን ነው ። የምትፈልገው ነገር እንደሚሆን በልብህ ስታምን የምትፈልገውን መሆን ትጀምራለህ ፣ የምትፈልገውን ስትሆንም የተመኘሀውን ደረጃና ማንነት ወደ እራስህ ትስባለህ ። የምትፈልገውን ለመሆንህም ወሳኙ ምክንያት ግለትህ ነው ፤ በጉዳዩ ላይ ያለህ ፅኑ ፍላጎት ፣ የማያባራ ምኞት ነው ። አንዳንዴ በመፈለግም ተስፋ አለመቁረጥ ወሳኙን ልባዊ ተነሳሽነት ያመጣዋል ፤ እልህ ውስጥ ይከተለዋል ፤ ከወትሮው በተለየ ስሜትን ያግላል ። ውስጥህ የሚነዳህ ነገር ካለ ፣ ውጫዊ ግፊት መጠበቅ ካቆምክ ሁሉንም የልብ መሻትህን ከመፈፀም የሚያግድህ ምድራዊ ሃይል አይኖርም ።

አዎ! ትልቅ ሃሳብ ይዘህ አትተኛም ፤ የሚያነቃ እቅድ አስቀምጠህ አትቀመጥም ፤ ስራ የሚፈልግ ህልም ኖሮህ በመካከለኛነት አዘቅት ውስጥ አትገኝም ፤ የሚያጀግን ብርቱ ሃይል አስቀምጠህ በተስፋ ቢስነት ስሜት አንገትህን አትደፋም ። የሚያስፈልግህን ልባዊ ግለት አምጣው ፤ በቁምህ ዳግም ነፍስ የሚዘራብህን ወሳኙን ንቃተ ህሊና ፍጠር ፤ ወደፊት የሚነዳህን ውስጣዊ ፍላጎት እድል ስጠው ። ትጀምራለህ ነገር ግን የመጨረስ ልምድ የለህም ፤ ታወራለህ ነገር ግን ለመጀመር ድፍረቱን ታጣለህ ፤ እውቀቱ አለህ ነገር ግን መተግበር አልቻልክም ። ከሁሉም በፊት በውስጥህ ግለቱን ፍጠር ፤ ፍላጎቱና ተነሳሽነቱ ላይ ስራ ። ፈልገህ የምታጣው ፣ ተመኝተህ የማታገኘው ነገር አይኖርም ። ሁሉም በእጅህ እንሆነ አስብ ፤ ተነሳሽነት ይኑርህ ፤ ፍላጎቱ ከውስጥህ ይምጣ ፤ የማያባራውን ግለት መፍጠር ቻል ፤ ስሜትህ ላይ በሚገባ ስራ ። በቀጣይ የሚያታግልህ መንገድ ሳይሆን በስሜት ብቻ የምትነዳበት ጉዞ ውስጥ እራስህን ታገኘዋለህ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
4.6K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  22:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ