Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የሰርጥ አድራሻ: @mirttshefoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 32.19K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 31

2023-02-14 03:16:33 #_ስልካችንን_ስንጠቀም_ማድረግ_የሌለብን_11_ተግባሮች
1 በዝናብ ሰዓት Networking የሆኑ ነገሮች ማጥፋት (Airplane mode ላይ ማድረግ) Bluetooth ,main network መብረቅ ይስባል)

2 FM (ኤፍ ኤም) (በErphon) አለማዳመጥ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ስማርት ስልኮች FM Antenna ስለሌላቸው ኢርፎኑን እንደአንቲና ነው የሚጠቀሙት ስለዚህ በኢርፎን ስናዳምጥ Electro magnetic ራዲየሸኑ ጭንቅላታችን ላይ ጉዳት ያደርሳል ፡፡

3 ስልክን ቻርጅ እያደረጉ ማንኛውንም ነገር አለመጠቀም በተለይ አለመደመጥ (Wifi አለመጠቀም Gaming አለመጫወት ፡፡

4 Earphone ሙዚቃ ስናዳምጥ Equalizer በመጠቀም ድምፁን Bass ላይ ማድረግ (ምክንያቱም Normal ድምፅ ስንጠቀም ያለው ለጆሯችን ቀጭን ድምፅ ስለሚያወጣ ያሳምመናል የHz አለመጣጣም ፡፡

5 ትልልቅ magnetic field ያላቸውን ነገሮች አቅራቢያ ስልካችሁ አለማስቀመጥ ፡፡

6 የስልክ እስክሪን Bluelight የሚባል አደገኛ ጨረር ይለቃል በተቻለ መጠን የስልካችንን Brigtness መቀነስ( Blue light Fiter APp መጠቀም)

7 የባትሪ ቻርጅ በጣም low ሲሆን ወይም ሲቀንስ ስልኩን ያለመጠቀም ልማድ ይኑርዎ ምክንያቱም ቻርጅ ሲቀንስ የሚረጨው ጨረር መጠን ይጨምራል ፡፡

8 ሞባይል ሲነጋገሩ ከጆሮዎ የተወሰነ ሴንቲሜትር ራቅ ማድረግ Electromagnetic Radiation ከተባለ ጨረር ራስዎን ይጠብቁ ፡፡

9 የሞባይል ስልክ ታቅፈው አይተኙ ከአልጋ 1.8 meter ማራቅ ማታ ሲደወል ከሚለቀቀው ጨረር ራስዎን ይጠብቁ ፡፡

10 ነፍሰጡር ሞባይል ሲይዙና ሲጠቀሙ ይጠንቀቁ የጽንሱ ሕዋሳት ለElectronics Radation እጅግ በጣም አለርጅክ ናቸው ስለዚህ አጠቃቀሙ ከጽንሱ ራቅ ባለ ስፍራ ይሁን አላስፈላጊ አጠቃቀምን ለምሳሌ ረዥም ሰዓት ማውራትና ቶሎ ቶሎ መደዋወል መቀነስ አለብዎ ፡፡

11 ብረት ነገር ባሉበት ቦታዎች ዙርያ ሞባይል አይጠቀሙ (ብረት የኤሌክትሪክ ማግኔቲክ ራድየሹን ወይም የጨረሩን ጉልበት ያጠነክረዋል (ስለዚህ መኪና ውስጥ አውሮፕላን ውስጥ ሊፍት ውስጥ ባቡር ውስጥ ጋራጅ ውስጥ ወዘተ አስቸኳይ ወይም አጣዳፊ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በተቻለ መጠን ሞባይል አይጠቀሙ የሚጠቀሙም ከሆነ በአጭር ደቂቃ ብቻ ይሁን ፡፡

በተለይ እድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ሞባይልን ባይጠቀሙ ወይም ባያዘወትሩ ይመረጣል ፡፡ ጨረሩ የጭንቅላት ሴሎችን በእጅጉ ይጎዳል ፡፡ በበለጸጉ ሃገሮች ከ15 ዓመት በታች የልጆች ሞት የሚከሰተው በጭንቅላት እጢ አማካኝነት ነው ፡፡እባክዎ በተቻለ መጠን ራስዎን ይጠብቁ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
3.2K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 00:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 03:09:05 እየሰራህ ነው!

እነሱ ሲያወሩብህ አንተ እየሰራህ ነው ፤ እነርሱ ሲያሙህ ፣ ሲያብጠለጥሉህ ፣ ስምህን በክፉ ሲያነሱ ፣ አለመቻልህን ሲተነትኑ አንተ አንገትህን ደፍተህ እንዳልሰማህ ግዴታህን እየተወጣህ ነው ፤ ጉዳይህን እየፈፀምክ ነው ፤ የተሻለውን ምህዳር ለእራስህ እየፈጠርክ ነው ። ማውራት ስራ ነው ፤ ሰዎችን እየተከታተሉ አቅማቸውን ማሳነስ ፣ በመስፈርት ማስጨነቅና ጥረታቸውን ዋጋ ማሳጣት ግን ክፋት ነው ። የፈለከውን አይነት ሰው የመሆን መብት አለህ ፤ መብትህንም ለመፈፀም የማንም ድጋፍና ይሁንታ አያስፈልግህም ። ሰዎች በሚሰራና ከእነርሱ ተለይቶ እራሱን ለማሻሻል በሚጥር ሰው ላይ ከአመታት በፊት ያወሩ ነበር ፣ ዛሬም እያወሩ ነው፣ ነገም እንዲሁ እያወሩ ይቀጥላሉና ይህ አዲስ ነገር አይደለም ። የወሬውን ፣ የሐሜቱን ፣ የትቺቱን ሜዳ ለእነርሱ ተውላቸው ፣ አንተ የስራውን ፣ የጥንካሬውን ፣ የብርታቱን ሜዳ አጥብቀህ ያዝ ። የሚያዋጣህን ካንተ በላይ የሚያውቅልህ ሰው የለም ። የሚያወራብህ ፣ አስተያየት የሚሰጥህ ፣ የሚያብጠለጥልህ ፣ የሚተችህ ሁሉ ካንተ ተሽሎ እንዳልሆነ ተገንዘብ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ብዙዎች ቀላሉን ሲመርጡ አንተ ከባዱን በሃላፊነት እየተወጣህ ነው ፤ ሌሎች ስም በማጥፋት ሲጠመዱ አንተ ስራህን እየሰራህ ነው ፤ አንዳንዶች ዋጋህን ሊያሳንሱ ፣ ክብርህን ሊያጎድሉ ሲጥሩ አንተ በፈለከው መጠን ህይወትህን እየመራህ ነው ። እንደ ባሪያ ትሰራለህ ፣ ትለፋለህ ፣ ትደክማለህ ፣ ትተጋለህ ፣ ላብህን ታፈሳለህ ፤ እንደ ንጉስ በክብር ፣ በፍቅር ፣ በነፃነት ትኖራለህ ። ማንም ስለስራህ ምንም ቢል አይገድህም ፤ ማንም ያልሆንከውን ስም ቢለጥፍብህ አያስጨንቅህም ፤ የትኛውም ሰው በማይመለከተው እየገባ ሊያወክህ ቢሞክር ትኩረት አትሰጠውም ፤ እርሱን የምትሰማበት ጊዜ አይኖርህም ። ሊያቆሙህ ይደክማሉ እንጂ አያቆሙህም ፤ ሊያሰናክሉህ ይለፋሉ እንጂ አያሰናክሉህም ፤ ስሜትህን ሊጎዱ ብዙ ቃላት ይሰነዝሩብሃል እንጂ ስሜትህን በፍፁም አይጎዱትም ። ካንተ ፍቃድ ውጪ የትኛውም ተፅዕኖ ሊያቆምህም ሆነ ወደኋላ ሊመልስህ አይችልም ።

አዎ! ስራህ ማምለጫ ብቻ ሳይሆን አላስፈላጊ ጫናዎችን መከላከያህ ነው ። ስላመንክበት ታደርገዋለህ እንጂ ስላመኑበት አታደርገውም ። ያንተን ጉዳይ ለመፈፀም መንገድ አታጣም ፤ ከልብህ ልታሳካው የምትፈልገውን ነገር በምንም ሁኔታ ውስጥ ሆነህ ታሳካዋለህ ፤ ታደርገዋለህ ። የምትመኛቸው አበርታች ቃላት ፣ የምትናፍቃቸው ድጋፍ ሰጪና አነቃቂ ንግግሮች እንዳሰብከው የቅርብ ከምትለው ሰው ላይገኙ ይችላሉ ። አንተ ስለእራስህ ለእራስህ የምትነግረው ግን ከማንም የበለጠ አነቃቂና አበርታች ቃል እንደሆነ አስተውል ። በጫናዎች ብዛት ፣ በሰዎች አሉታዊ ንግግር ፣ በሁኔታዎች አለመመቻቸት ብትወድቅ የምትነሳው እራስህ ነህ ። ትችላለህ! መቻልህን በተግባር አሳይ ፤ ታውቃለህ! እውቀትህን ኑረው ፤ አቅሙ አለህ! በህይወትህ ግለጠው ፤ ሰዎች ከሚያስቡህ በላይ ነህ! መሆንህን በእራስህ መንገድ አረጋግጥላቸው ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.5K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  00:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 03:06:40 ሃሳብህ ምንድነው?

"አብዝተህ የምታስበውን ነገር ትሆናለህ ።" የናፖሊዮን ሂል አባባል ነው ። እና ምን እያሰብክ ነው ? ምንም ካልክ በእርግጥም ምንም ልትሆን ነውን ? አብዝተህ ፣ ደጋግመህ ስላምታስበው ነገር ማሰብ ጀምር ። የምርም ውስጥህ የሚመላለሰው ፣ ትኩረትህን የያዘው ፣ ፋታ የነሳህ ሁነኛና አንተን ሊገልፅህ የሚችለው ሃሳብ ምንድነው ? የተኛውም ተደጋጋሚ ሃሳብ ሃሳብ ሆኖ እንደማይቀር አስተውል ። በሂደት ወደ ስሜት ይቀየራል ፤ ስሜትም እያደር ማንነት (character) ይሆናል ። የምታስበውን ትሆናለህ ማለትም፣ ስሜትህ የተገዛለተን ፣ ማንነትህ የተቀበለውን ሃሳብ በእውን ሆነሀው ትገኛለህ ማለት ነው ። ሃሳብህ አንተን የማይሆንበት አንድና አንድ መንገድ ወደ ስሜትና ወደ ማንነት ካላደገ ብቻ ነው ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሃሳብህ ምንድነው ? ይህ ነው ብለህ ልትገልፀው የምትችለው ፣ ያለሁበትን ሁኔታ ይወክልልኛል ፣ ስለእራሴ ሳስብ ይመጣብኛል የምትለው ሃሳብ ምንድነው ? ተፍጨርጭሮ ህይወትን እንደ ሁኔታው መግፋት ፣ ለእለት ጉርስ ደፋ ቀና ማለት ፣ የጎደለውን እየሞሉ ህይወትን መቀጠል ወይስ ተዓምራትን እየሰሩ ማስገረም ፤ ከእራስ በላይ ለሌሎች መድረስ ፣ የታላቅነተንን ፅዋ መጎናፀፍ ? አንድ ነገር አስታውስ ሃሳብ በእራሱ ድፍረትን ይጠይቃል ፤ ትልቅ ነገርን መመኘት በእራሱ የማይናወጥ አቋምን ይፈልጋል ። ሊገልፅህ የሚችል ሃሳብ ካለህ በእርግጥም በታላቅነት ደረጃ የሚያስቀምጥህ ፣ ለተሻለ ስፍራ የሚያበቃህ ፣ በተዓምራት የሚመራህ ሊሆን ይገባል ። ስለምታስበው ማሰብህን እንዳትረሳ ። ስሜትህ ሃሳብህ ውስጥ አለ ፤ ማንነትህ ደግሞ ስሜትህ ውስጥ አለ ። ማንነትህን መገንባት ከፈለክ ሃሳብህን ከማስተካከል ጀምር ።

አዎ! በተዛባ ሃሳብ የተስተካከለ ስሜት ሊኖርህ አይችልም ፤ ባልተገባና በማይማርክ ስሜትም የተሻለ አስደሳች ማንነት ሊኖርህ አይችልም ። ድርጊትህ ከሃሳብ የመጣ እንደሆነ በሙሉ ስሜትና ትኩረት የመከወን እድሉም እጅግ ከፍተኛ ነው ። ስለምታደርገው የመጠንቀቅህን ያክል የሃሳብ ጥንቃቄም ያስፈልግሃል ። ውስጥህ የሌለ ሃሳብ በማንነትህ ሊገለጥ አይችልም ፤ ብትጠላውም ማሰብህን እስካላቆምክ ድረስ ጥላቻው በእራሱ ወደ ፍላጎት ተቀይሮ መጥፎውን ባህሪህን ስትደጋግም ትገኛለህ ። መጥፎ ባህሪያትህን መጥላትህ በእነርሱ ዙሪያ ያለህን ሃሳብ ማቆም ካልቻለ በምንም ሁኔታ ልትተዋቸው አትችልም ። ሃሳብህን መዝን ፣ ስሜት ከመሆኑ በፊት ፣ በማንነትህ ከመገለጡ አስቀድሞ የተቻለህን ማስተካከያ አድርግበት ። የእኔ የምትለው ሃሳብ በመልካም ጎኑ የሚገልፅህና ሊያኮራህ የሚገባ ሃሳብ መሆን እንዳለበት እመን ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.9K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  00:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 03:39:29 ግዴታ አይደለም!

የምትመኘውን ህይወት መፍጠር ፣ ከምትወደው ጋር ጊዜ ማሳለፍ ፣ በመረጥከው አኳሃን ደረጃህን ማሻሻል ፣ ያሰኘህን እያጣጣሙ መኖር ፣ በተሻለ የህይወት ምህዳር ውስጥ መገኘት ፣ ለሌሎችም ምቹ ስፍራን መፍጠር ግዴታህ ሳይሆን ወደህና ፈልገህ የምታደርገው ነገር ነው ። የትኛውም ምርጫህ ተቀፅላ ውጤት ይኖረዋል ። ምንም ስታደርግ ተከትሎት የሚመጣውን ነገር አስተውል ፤ የትም ስትገኝ ልታገኝ የምትችለውን ነገር ተረዳ ፤ ከማንም ስትወዳጅ ማንነቱን ለማጥናት ሞክር ። የማይጠቅምህ ነገር እንደማያስፈልግህ ማሰብ ጀምር ። ያለምክንያት ወዳንተ የሚመጣ ነገር የለም፤ አንተ ምንም ስለሆንክ ልታገኘው የምትችለው የተለየ ጥቅምም አይኖርም ። ጫናዎችን ወደ ጥንካሬ ፣ ውድቀትን ወደ ብርታት ፣ ስንፍናን ወደ ተነሳሽነት ፣ ማጣትን ወደ ትልቅ የስኬት ግብዓት የመቀየር ሃይል አለህ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ግዴታ አይደለም ፤ አደጋን ፈርተህ ፣ ድህነትን ጠለተህ ፣ በማጣት ተሰቃይተህ የምትዋደቅለት የህይወት ግብ አይኖርህም ። ምንም አድርግ ሁን ብለህ ፈልገህና መርጠህ እስካደረከው ድረስ የማታሳካበትና ከግብ የማታደርስበት ምክንያት አይኖርም ። ሰዎች ስላደረጉት ፣ ብዙዎች ስለሚፈልጉት ፣ ሌሎችን ስላስደሰተ ብለህ የምታደርገው አንዳች ነገርም አይኖርም ። የፈለከውን ማድረግ ፣ እንደ ምርጫህ መኖር ይህን ያክል ቀላል ላይሆን ይችላል ነገር ግን አደጋውን ለመጋፈጥ ዝግጁ እስከሆንክና የእራስህን ደስታ እራስህ መፍጠር እንደምትችል ካመንክ የግዳጅ ህይወት ሳይሆን የምርጫ ህይወት መኖር ትጀምራለህ ። ያንተ የሆነን ነገር ለማግኘት ማንንም ደጅ መጥናት እንደሌለብህ አስተውል ፤ የፈለከውን ለማግኘት ከአምላክህ ውጪ ማንንም መለመን እንደማይጠበቅብህ እወቅ ።

አዎ! ፍላጎትህ ስኬትና ታላቅነት ከሆነ ምርጫህ ፣ እይታህ ፣ እሳቤህና ተግባርህ ሁሉ በእርሱ ዙሪያ ሊሆን ይገባል። በጥረትህ ልክ ከሚረዳህ ፈጣሪ ውጪ ማንም ከተኛህበት ሊቀሰቅስህ አይመጣም ፤ ማንም በግፊትና ጫና ወደፊት ሊገፋህ አይመጣም ። ያንተ ጉዳይ ያንተ ነው ። ምርጫህ ያስከብርሃል፤ ምርጫህ ያዋርድሃል ። ስራህን ለመቀየር "ይህን ስራ አልወደውም" ማለት ብቻ በቂ እንዳልሆነ አስተውል ። ለማትወደው ስራ ይህን ያክል ጊዜ እየሰጠህ እንዴት ለምትወደው ስራ የተወሰነ ሰዓት ልታጣ እንደቻልክ እራስህን ጠይቅ ። በእርግጥ ለመኖር መስራስት አለብህ ፤ የምትወደውን ስራ ለመስራትም ጊዜ ሊኖርህ ይገባል ። የማትፈልገው ስፍራ ለመገኘትህ ካንተ ውጪ ማንም ሃላፊት አይወስድልህም ። የምትወደውን ምረጥ ፣ ጊዜ ስጠው ፣ በሂደት አሳድገው ፣ ከቆይታ በኋላም የህይወትህ ዋና ግብ አድርገው ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.4K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  00:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 03:37:45 ዛሬ ሌላ ቀን ነው!

እነሆ አዲስ ሌላ ቀን ፣ እንሆ ሌላ የተለየ እጅግ ግሩም አስደሳች ድንቅ ቀን ። አዲስ ቀን የእራሱ ተስፋ ፣ የእራሱ መልካም ገፅታ ፣ የእራሱ የተለየ ድባብ አለው ። እንደፈለከው ታደርገው ዘንድም ሙሉ ስልጣን ተሰጥቶሃል ፤ ያንተ የሆነውን ፣ አምላክ ያደለህን ይህን ብሩህ ቀን ማንም አይቀማህም ፤ ማንም አይወስድብህም ። በቀንህ ውስጥ ዳግም እራስህን መፍጠር ፣ በአስደሳች ስሜት መታነፅ ፣ በተለየ ድባብ መታደስ ትችላለህ ። ቀንህን ዳግም እንደማታገኘው አውቀህ አጣጥመው ፤ ሌላ ጊዜ እንጂ ይህን ውድ ጊዜ ዳግም እንደማታገኘው ተረድተህ ከልብህ ኑርበት ። ቀናት ቀናት ላይ በተጨመሩልህ ቁጥር ህይወትህ ወደ መዳረሻዋ እየተጠጋች ነውና በተቻለህ መጠን ያለህን ጊዜ ዋጋ ስጠው ፤ በጥቃቅን ቅፅበታት ውስጥ እራስህን አግኝ ፤ ህይወትህን ነፍስ ስጠው ።

አዎ! ጀግናዬ..! ዛሬ ሌላ ቀን ነው ፤ የሃሳብ ክምርህ እንዳለፈ ቁጠረው ፤ ጭንቀትህ እንደተወገደ ይሰማህ ፤ አሁን በጣም ተረጋግተሃል ፤ ሰላም ተሰምቶሃል ፤ የዛሬ ውድ ዋጋ ፣ የአሁን የማይለካ ዋጋ በደምብ ገብቶሃል ። ህይወት ትናንት ወይም ነገ ሳይሆን ዛሬና አሁን እንደሆነ ተረድተሃል ። እጅግ በጣም ብዙ አስጊና አስጨናቂ የህይወት ገጠመኞች ይኖሩ ይሆናል ነገር ግን ዛሬህን የሚቀሙና አሁንህን የሚያበላሹ ከሆነ ፈጣን እርምጃ ልትወስድባቸው ይገባል ። ሁሌም እንዳሰብከውና ባቀድከው ልክ ላትኖር ትችላለህ ፣ አንዳንድ ያልታሰበና የተዛባ ነገር ሊገጥምህ ይችላል ። ይህም ሁነት ከትልቁ ሃሳብና እቅድህ ሊያስቀርህ አይገባም ።

አዎ! ታሪክን አትኖረውም በነገ ውስጥም አትገኝም ። ተጨባጩ ህይወትህ ዛሬና አሁን ነው ። ያልተጠበቁ ክስተቶች ተከስተዋል ፤ ያላሰብከው ድርጊት ተፈፅመዋል ፤ ነገሮች መሆን የማይገባቸውን ሆነዋል ህይወት ግን ይቀጥላል ፤ ሌላ አዲስ ቀን ፣ አዲስ ንጋት እንደ ሌላ እድል ይሰጠናል ። በምቾት ያልታጠረ ፣ ምንም ነገር እንዲረብሸው የማይፈልግ ፣ የውስጡ ሰላም አለመኖር አብዝቶ የሚያስጨንቀው ፣ ትናንሽ ክስተቶችም ቢሆኑ ለምን ተፈጠሩ እያለ የሚታወክ ሰው ህይወቱን በተረጋጋ መንፈስ ለመኖር በጣም ይቸገራል ። የሆነው ሆኖ አንተ በህይወት ስላለህ ብቻ ልታመሰግን ይገባል ፤ የደረሰብህ ደርሶብህ በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ሰላም ስለሆኑ ብቻ ደስ ሊልህ ይገባል ። ሁሌም ከዛሬ የተሻለ ቀን እንደሚመጣ ልታስብ ትችላለህ ሲመጣ ግን ዛሬ ሆኖ እንደሆነ አስተውል ። መጪውን ጊዜ ማስተካከል የምትችልበት ሁነኛውና ዋነኛው መንገድ ዛሬን በመኖርና ትርፋማ በማድረግ ብቻ ነው ። ዛሬህን ተጠቀም ፤ ህይወትህን ኑር ፤ ሙሉም አድርጋት ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.4K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  00:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 06:13:48 #ኢትዮጲያ_ብቻ_ለምትኖሩ
VPN በመጠቀም ካርድ እየተጋጣቹ ላላቹ ቀለል ያለ መፍትሄ ይኸውላቹ እነሆ....

VPN (virtual private network) ማለት የግላችሁን ኔትዎርክ ግንኙነት መፍጠሪያ ማለት ነው ። ይህም ማለት ለምሳሌ ኔትዎርክ አጠቃቀማች ልክ እንደ ውሃ ነው ። ቤታችን ውስጥ ቧንቧ አለ ። በዛ ቧንቧ የሚላክ ውሃ ደግሞ ባስፈለግን ሰአት እየከፈትን እንጠቀማለን ማለት ነው ። ታድያ ውሃውን መቅጃ ወይ ባሊ ወይ ጆግ ነገር ያስፈልገናል ።

ይህም ቧንቧው ኔቶዎርክ ነው ። የሁላችንም ሲምካርድ ኔትዎርክ አለው ። ውሃው ደግሞ ግንኙነቱ ነው በኔትዎርኩ የድምፅ( ስልክ መደዋወል) ፣ የፅሁፍ አገልግሎት (ሚሴጅ) ፣ የኢንተርኔት አገልግሎት እንጠቀምበታለን ። ይህ ማለትም በቧንቧው ውሃ ብቻ ሳይሆንም ወተትም ቢለቀቅ ወተቱ ይደርሰናል ማለት ነው ። አሁን ቴሌ ቧንቧውንም ውሃውንም ሰጥቶን የከለከለን ባሊውን ነው VPN ማብራት ማለት የራስህ ባሊ ትተህ በኪራይ ባሊ ውሃ እንደመቅዳት ነው ። ይሄ ደሞ የውሃ ክፍያ ብቻ ሳይሆን የባሊ ኪራይም ዋጋ ስለሚጨመርብህ ትጋጣለህ ።

አሁን በየስልኮቻችን የጫንነው VPN ጥቅሙ ይህ ነው ። ሎኬሽንህን አሜሪካ ስታደርግ በአሜሪካ ባሊ ኢትዮጲያ በዘረጋችልህ ቧንቧ ውሃ እንደመቅዳት ነው ። ይህም በዛ ላይ Background data እንድንጠቀም ስለማያስችለን ለከፍተኛ ወጪ ይዳርገናል ሌሎች መተግበሪያዎችን (application) እንዲነሱ በማድረግ ።

ይህን ያህል የVPN ጥቅምና አሰራር ከተነጋገርን ወደ መፍትሄው እንሂድ ። የስልካችን Setting በመግባት ካሉት ዝርዝሮች ውስጥ More connection setting የተሰኘውን በመጫን ወደ ውስጥ እንዘልቃለን ። ከዛም VPN የተሰኘውን በመንካት ቀጥሎም የመደመር ምልክት ወይንም Add VPN ሚለውን በመጫን ወደ ቀጣዩ እንሻገራለን ። Name የሚለው ጋር "Geez VPN" ብለን እንፅፋለን ። ግእዝ ቪፒኤን ካልን በውሃላ ከስር Type የሚለውን ተጭነን L2TP/IPSEC የሚለውን እንመርጣለን።

ቀጥሎ ከሚመጡት ባዶቦታዎች server adress የሚለው ቦታ ላይ public-vpn-209.opengw.netይህን እንፅፋለን ። ቀጥሎ Show advance option የሚለው ላይ የራይት ምልክት በማድረግ
Ip sec pre shared key vpn

ቀጥሎም DNS server 0.0.0.0 ከሞላን በውሃላ SAVE እንለዋለን ። በነገራችን ላይ DNS ማለት Domain Name Service ማለት ነው ሲበተን ። አሁን የራሳችንን VPN ከፍተናል ። በመቀጠል ምናደርገው ዳታ አብርተን connect ማድረግ ብቻ ነው ። Connect ስናደርገው ታድያ Username እና password ይጠይቀናል ሁለቱም ጋር vpn ብላችሁ ሙሉ ። Background ዳታቹንም አብርታቹ በፊት ከሚበላቹ በቀነሰ ዋጋ ተመሳሳይ ፍጆታ መጠቀም ትችላላችሁ መልካም ውሎ
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.0K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  03:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 06:13:13 ተከፍሎሃል!

በመልፋትህ የእጅህን አግኝተሃል፤ በመትጋትህ የሚገባህ ተሰጥቶሃል፤ በመድከምህ ተመጣጣኙ ሽልማት ተበርክቶልሃል። ቀልድና ቁብ ነገር የእራሳቸው የግል ዋጋ አላቸው። በህይወትህ እየቀለድክ ለቁብ ነገር አትበቃም። ትልቅ ነገር ከተመኘህ የትልቅነትን ባህሪ መላበስ ይኖርብሃል። ሁሌም ነገሮች እንደጠበከው አይሆኑም። አንዱን ስትለው አንዱ ይጎድላል፤ አንዱን ስትሞላው አንዱ ያፈሳል። ሁሉንም በአንዴ ማሰተካከል እንደምትችል ቢሰማህም ስላላስተካከልከው ብቻ ጉዞህን ማቆም የለብህም። ምንም ጊዜ የማታጣው ከባድ የህይወት አጋጣሚ ይኖራል። ትፈተናለህ ካለፍክ ትቀጥላለህ፣ ካላለፍክ ፈተናህ አይነቱን እየቀየረ፣ ይዘቱን እያሻሻለ ይቀጥላል። ያለምክንያት፣ ያለ ምንም ዋጋ የምትጎናፀፈው ድልና የምታጠልቀው የአሸናፊነት ካባ የለም። ከባዱን ጊዜ ካልተቋቋምክ የህይወት አቅጣጫህ መንገድ ይስታል፤ ካሰብከው መንገድ ይወጣል፤ ያልጠበከው ስፍራ እራስህን ታገኘዋለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ተከፍሎሃል! በትዕግስትህ ምክንያት የበለሷን ፍሬ በልተሃል፤ እንደ ፅናትህ ለተሻለ ደረጃ በቅተሃል፤ በልፋትህ ልክ ከፍ ብለሃል፤ እንደ ድካምህ አቅምህን አጎልብተህ ተገኝተሃል። እያንዳንዱ በህይወት አቅጣጫህ የምታገኘው ሽንፈትም ሆነ አሸናፊነት፣ ታናሽነትም ሆነ ታላቅነት፣ ክብርም ሆነ ውርድ የስራህ ውጤት ነው። ለእራስህ ጊዜ ከሰጠህ፣ እራስህን ካከበርክ፣ ከተንከባከብክ፣ ለእራስህ ጠበቃ መሆን ከቻልክ የማያከብርህ፣ የማይሰማህ፣ የማይደግፍህ ሰው አይኖርም። አምነህበት ከልብህ ለእራስህ የምታደርገው ነገር በመጨረሻ ለሚገባህ ውጤት ያበቃሃል። ተነሳሽነት ሁሌም ላይኖር ይችላል፣ ሁሌም ብርታት ላይሰማህ ይችላል ነገር ግን ስሜትህን አሸንፈህ የጀመርከውን ስለጨረስክ፣ ያቀድከውን ስለፈፀምክ ለእራስህ የላቀ ክብርና ቦታ ይኖርሃል።

አዎ! ቀላል መንገድ አልጀመርክምና መበርታት ይኖርብሃል፤ ጉዞህ የተመቻቸ አይሆንምና ለመሰናክሎቹም እራስህን ማዘጋጀት ይጠበቅብሃል። ብልህና ብርቱ ሰው ስራውን በሙሉ የሚጀምረው ከጨረሻው ነው። በምናቡ እያንዳንዱን ነገር አከናውኖ እንደጨረሰ ያምናል፤ መሬት ላይ የሚያወርደው በተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት እንደሆነ ያውቃል። በውስጥህ ጨርሰህ የምትጀምረው ተግባር ምን እንደሚያስወጣህና በምላሹ ምን እንደሚከፍልህ አስቀድመህ ታውቃለህ። እውቀትህም ተጨባጭ የሚሆነው ወጪውን አውጥተህ ክፍያህን በእውን ስትቀበል ነው። ስሜትህን በማባበል ከሚገባህ የህይወት ደረጃ በታች አትኑር፤ ለእራስህ በቂ ሆነህ ሳለ በጥበቃ እድሜህን አትጨርስ። ካለህበት ሁኔታ የተሻለ ስፍራ ይገባሃልና እንደ ችሎታህ ጥረትህን ቀጥል።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.0K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  03:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 07:17:08 ማን አለ?

ክብርን አትንፈጉት ክቡር ነውና ፤ ምስጋናን አትንሱት ምስጉን ነውና ፤ መኖሩን አትጠራጠሩ ሁሌም በውስጣችሁ ነውና ፤ በፍርዱ አትከፉ ሁሌም ፍፁም ነውና ፤ በመዘግየቱ አትቆጡ የሚቀድመው አይኖርምና ። አምላክ ሁሌም አለ ፤ ዘወትርም ከእኛ ጋር ነው ። ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ ነው ። በምላሹ የማይሳሳት ፣ በፍርዱ የማያጎድል ፣ በአሰራሩ እንከን የማይገኝበት ፣ ሁሉን በአግባብ ፣ በስረዓት ፣ በጊዜው መከወን የሚያውቅበት እንደፈጣሪ ማን አለ ? እንደ ቸር አምላክ ማን አለ ? እምነትህ በእጥፍ ሲከፍልህ ተመልክተሃል ፤ ፀሎትህ ምላሽ ሲያሰጥህ አይተሃል ፤ የእንባህን ዋጋ አግኝተሃል ፤ የለቅሶህን መጨረሻ ተመልክተሃል ። ፅናት ብርቱ ሀይልህ ነው ፤ ትዕግስት ድንቅ መሳሪያህ ነው ። ከአምላክህ ብዙ ተማር ፤ ከስራው እውቀትን በጥበብ ቅሰም ፤ በምንም ሁኔታ ውስጥ ለምስጋና ፣ ለውዳሴ ፣ ለአድናቆት አትስነፍ ። የነገሮችን ሁሉ መጨረሻ የሚያሳምር ድንቅ አባት እንዳለህ አስተውል ።

አዎ! ጀግናዬ..! እንደ እርሱ ማን አለ ? ልጆቹን ዘወትር የሚጠብቅ ፣ በምክንያት የሚሰበስባቸው ፣ ወደ ቤቱ የሚጠራቸው ፣ አንድነትን የሚያስተምራቸው ፣ ፍቅሩን የሚያሳያቸው ፣ መግቦቱን የሚቸራቸው፣ እምነታቸውን የሚያዳብርላቸው ፣ በፍቅሩ የሚማርካቸው በእርግጥም እንደ ቸሩ አምላክ ፣ እንደ ደጉ ጌታ ማን አለ ? ማንስ ይገኛል ? ማንም አይኖርም ። ማግሮመረማችን ሰምቶ ዝም አለ ፤ በአመፃችን ልክ ጠልፎ አልጣለንም ፤ እንደ እምነታችን ጉድለት ብዙ አልፈተነንም ፤ ከቤቱ እንደ መራቃችን ፣ ህጉን እንደመሻራችን ፣ ከትዕዛዛቱ እንደመውጣታችን አልፈረደብንም ። ልታመሰግነው ብትወድ ስለ ጥበቃው ታመሰግነዋለህ ፤ ስለ ትዕገስቱ ደጁን ትጠናለህ ፤ ስለ ርህራሔው በቤቱ ትፀናለህ ። ሳይዘገይ መልስ የሚሰጥ ፣ ከአንተ በላይ የሚያስብልህ ግሩም አባት አለህና በፍፁም በእርሱ ተስፋ አትቁረጥ ።

አዎ! የነገሮች መከሰት ፣ የሁኔታዎች ማማርና መበላሸት ፣ የእያንዳንዱ ተግባራት አጥፊና አልሚ መሆን በምክንያት ነውና ሃዘንህንም ሆነ ደስታህን በልክ በመጠን አድርገው ። ማን ሊታደግህ እንደሚችል አይተሃል ፤ ማን ከጎንህ እንደሚቆም ተመልክተሃል ። አምላክ ሁሌም ከንፁህ ልቦናና ከቀና አስተሳሰብ ጋር ነው ። መልካምነትህ ፣ የዋህነትህ ፣ ቅንነትህ ፣ ደግ አሳቢነትህ ፣ የማይናወጠው እምነትህ የአሸናፊነትህ ምስጢር ነው ፤ የድል አድራጊነትህ መሰረት ነው ። በየትኛውም ምድራዊ ሃይል የማይናወጥ ፣ የማይሸበር ፣ የማይታወክ እምነት ስላለህ ልትኮራ ይገባል ። ማመን ስትጀመር እውነተኛ ማንነትህን ተመለከታለህ ፤ በፅናትህ ልክ ያሰብክበትን ነገር ታሳካለህ ። በየትኛውም የህይወትህ ዘርፍ የፈለከው እንዲሆን፣ ያለምከው እንዲሳካ ፣ የተበላሸው እንዲቃና ፅኑ እምነት ይኑርህ ፤ የአምላክህን ስራ በትዕግስት ተጠባበቅ ። ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን!
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.6K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 07:14:28 ያልተማረ አያልፍም!

“ችግሮች ሊያስተምሯችሁ ወደ ሕይወታችሁ የመጡበትን ትምህርት እስክትማሩና እስኪገባችሁ ድረስ ችግሮቹ ከሕይወታችሁ አይሄዱም” እየደጋገማችሁ የምትጎዱበትንና ተስፋ የምትቆርጡበትን የሕይወት ችግርና ፈተና አስቡት እስቲ ፡፡ ይህ ችግር እየደጋገመ ብቅ የሚለው ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ችግሮች ተከስተው ከእነዚያ ሁኔታዎች ማግኘት የሚገባችሁን ትምህርት በመማር ስላላለፋችሁ ነው ፡፡

የሚያጋጥሟችሁ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የሚያደርጉላችሁ ትልቁ ውለታ እስከወዲያኛው የምትጠቀሙበትን ትምህርት አግኝታችሁ የማለፋችሁ ጉዳይ ነው ፡፡ በሌላ አገላልጽ ፣ ትምህርት አግኝታችሁ ያለፋችሁበት ችግር የሚሰብራችሁና ተስፋ የሚያስቆርጣችሁ ችግር ሳይሆን የሚያጠነክራችሁና ወደፊት እንድትራመዱ የሚያደርጋችሁ ችግር ነው ፡፡ ከችግራችሁ ተገቢውን ትምህርት ያለማግኘታችሁ ምልክቶች ፡- ተመሳሳይ ችግር ውስጥ እየደጋገሙ መገኘት ፤ በተመሳሳይ ችግር ከዚህ በፊት በተጎዳንበት መልክ ወይም ከዚያ በበለጠ ሁኔታ መጎዳት ፤ እንደገና እንዳንጎዳ በሚል ፍርሃት ተመሳሳይ ነገር አለመሞከር ፤ ለደረሰብን ችግር ሰውን መውቀስና ሃላፊነትን አለመውሰድ ።

ከችግሮቻችሁ ተገቢውን ትምህርት እስካገኛችሁ ድረስ ወደሚቀጥለው የእድገት ደረጃ ማለፋችሁ አይቀርምና በርቱ!
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.4K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 04:49:18 ጥርስን መንቀል እንደተነቃነቀ ነው አለች አያቴ
1.5K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  01:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ