2023-02-03 03:46:55
ክፍያ አለው! ጥሩ ነገር ክፍያ አለው፣ ዋጋ ያስወጣል ፣ ጥረትን ይጠይቃል ፣ መሰጠትን ይፈልጋል ። መጥፎ ተግባርም እንዲሁ ዋጋ ያስወጣል፣ እጅን ያሳጥራል ፣ አቅምን ያሳንሳል ፤ ስሜትን ይገድላል ። እምነት ኖሮህ ማድረግ የምትችለው ነገር በበጎ ተግባርህ የኋሊት ምላሽ በመተማመን ነው ። የትኛውንም ክፋትን የሚዘራ ሃሳብ ብታመነጭ ጉዳቱና ክፍያው አሁን ባይሆንም በጊዜው በእጥፍ ይከፍልሃል ። መሆን የምትችለው ብዙ መልካም ነገር እያለ ሸፍጥና ደባን ብትመርጥም ዋጋው አንድም ከአምላክህ ሌላም ከሰው ይሰጥሃል ። መጥፎና ጨካኝ ለመሆን እራስህን መካድ እንዳለብህ ልትገነዘብ ይገባል ። ተፈጥሮዋዊው ሰውነትህ የመልካም ፍሬ ዘር እንጂ የጥፋትና የተንኮል ምንጭ አይደለም ። ህይወትን ቀለል ማድረግ ከፈለክ ጥሩ ፣ አዛኝና ሰዎችን የሚረዳ ፣ የሚረዳ ሰው መሆን በቂህ ነው ። አዕምሮህ ሲያርፍ ፣ ውስጥህ ሰላም ሲሰማው ፣ ማንነትህ ሲነፃ ፣ ንፁ አየር ስትተነፍስ ፣ ከአምላክ ጋር ስትግባባ ፣ ከባቢህን በበጎ ተግባርህ ስታንፅ የሚሰማህን ልዩ ስሜት አዳምጥ ። ስሜቱንና ዋጋውን ብታመዛዝን የምታገኘው የተለየ ስሜት ከወጪህ በእጅጉ ይበልጣል ።
አዎ! ጀግናዬ..!
ክፍያ አለው! መልካም መሆን ክፉ መሆን፣ ህግን ማፅናት ህግን ማፍረስ ፣ ሰውን መርዳት ሰውን መጉዳት ፣ እራስን መበደል እራስን ነፃ ማውጣት ፣ በታሪክ መታሰር ታሪክ መስራት እያንዳንዱ ተመጣጣኝ ዋጋ ያስከፍላል ። ጠቃሚው ግን መልካምነት እንደሆነ ግልፅ ነው ። ታሪክ የሆነ ተግባር ሁሌም ታሪክነቱ ፣ ትርክትነቱ ይቀጥላል ። የትም ሃገር፣ የትም ቦታ ፣ በማንም ሰው ህይወት ውስጥ መጥፎ ታሪኮች ነበሩ ፣ ብዙ ሰዎችም ጠፍተውበታል ፣ ተሰቃይተውበታል ፣ ዋጋ ከፍለውበታል ። ነገር ግን ባለፈው ጥፋትና በደል ውስጥ እራስን ወስኖ ማስቀመጥ ፣ የእራስን የተለየ ታሪክ ለመስራት አለመታገል ፣ በምትኩ በትናት ጥፋት ላይ ዛሬም የተለየ ጥፋትና ክፋትን ለመፈፀም መቻኮል ከሚዛናዊው ሰውኛ ባህሪ የወጣ ነው ።
አዎ! መጥፎውን ታሪክ በመልካም ታሪክ መቀልበስ ባትችል ፣ ክፉውን ተግባር በጥሩ ስራ መሻር ባትችል እንኳን ደጋግመህ መጥፎውንና ክፉውን ታሪክ ማንሳት አቁም ። አቅም እንደሌለው ፣ ደካማ እንደሆነ የእራሱን ታሪክ መፃፍ እንደማይችል ልፍስፍስ ትውልድ ትናንት ለሆነው ክስተት ዛሬ የማይገባ ዋጋ ለመክፈል አትቻኮል ። ሰው ሆነህ መፈጠርህ ተዓምር እንድትሰራ እንጂ ተዓምረኛውን ሰው ያለጥፋቱ እንድትበድለውና እንድትኮንነው አይደለም ። በምክንያትም ቢሆን መጥፎ ቂመኛ ሰው ከሆንክ ለመሱዓትነት የምታቀርበው ውዱን የገዛ ህይወትህን ነው ። ከሚመርዘው የጥላቻና የተበዳይነት ስሜት ውጣ ፤ ከበደል በተሻል ብዙ ድንቅ ተግባራትን መፈፀም እንደምትችል አስተውል ። ዋጋቸው ተመጣጣኝ ከሆነ ለሚያተርፍልህ መልካምነትና በጎነት የሚገባውን መሱዓትነት ክፈል ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.6K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited 00:46