Get Mystery Box with random crypto!

ብርታቱ ይኖርሃል! ለእራስህ ይቅርታ ማድረግ የውዴታ ግዴታ ቢሆንም ምንያክል እራስህን ይቅር | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ብርታቱ ይኖርሃል!

ለእራስህ ይቅርታ ማድረግ የውዴታ ግዴታ ቢሆንም ምንያክል እራስህን ይቅር እንዳልከው እራስህን ጠይቅ ። በእራስህ አፍረህ ታውቃለህ ፤ በማንነትህ ተሸማቀህ ታውቃለህ ፤ እራስህን ጥለህ ሌላ ሰው በሆንኩ ብለህ ተመኝተሃል ፤ በረከቶችህን ረስተህ በጉድለቶችህ ተሸማቀሃል ፤ እራስህን ለመግለፅ እስክትሸማቀቅ ድረስ አንተነትህን ተጠይፈሐል ፤ የመጣህበትን ቤተሰብ ለመውቀስ ተቻኩለሃል ። እራስህ ላይ ያደረስከው እያንዳንዱ በደል በማንም አስገዳጅነት የተፈፀመ ሳይሆን በእራስህ ፍቃድና ፍላጎት የተከወነ ነው ። እራስህን ጥላው ፣ እራስህን ጣለው ፣ አትንከባከበው ፣ አዋርደው ያለህ ሰው የለም ። በገዛ ፍቃድህ ለእራስህ ባዳ ለመሆን በቅተሃል ፤ የሚጎዱትን ልማዶች በማዳበር ተክነሃል ፤ የማይመጥኑትና የማይወክሉት ስፍራ ተገኝተሃል ። እራስህን ጥለህ ፣ ማንነትህን አርክሰህ ፣ አንተነትህን አሳንሰህ ከእራስህ ውጪ ሌላ ማንም መሆን እንደማትችል ብታውቅም እራስህን ከመበደል ግን ወደኋላ አላልክም ።

አዎ! ጀግናዬ..! ብርታቱ ይኖርሃል ! እራስህን ይቅር ለማለት ፣ ያለፈ ጥፋቱን ለመርሳት ፣ ሙሉ ማንነቱን ለመቀበል ፣ እንከኖቹን ለማጥፋት ፣ የተሻለ ሰው ለማድረግ ፣ ወደፊት ለመምራት ፣ ያለፈ ጠባሳውን ለመሻር በእርግጥም ጥንካሬው ይኖርሃል ፤ ብርታቱን አለህ ። ሰዎችን ብትበድል ይቅርታ መጠየቅህ የግድ ነው ፤ እራስህን ስለመበደለህስ ለእራስህ የዘረጋሀው የይቅርታ እጅ ይኖር ይሆን ? ከሰው ባትስማማ ሽማግሌ ያስማማህ ይሆናል ፤ ክእራስህ ብትጣላ ፣ እራስህን ብትበድልስ ማን ይሆን የሚያስታርቅህ ? ለየትኛውም ጉዞህ ከእራስህ ጋር ያለህ ግንኙነት ፣ ተግባቦትህ ፣ አረዳድህ እጅጉን ወሳኝ ነው ። ከእራስህ ጋር በሚፈጠር አለመግባባት የምትጎዳው አንተ ነህ ፤ ጭንቀትን የምታተርፈው ፣ መረጋጋትን የምታጣው ፣ በበዛ ሃሳብ የምትዋጠው ፣ ትካዜ ውስጥ የምትገባው ፣ በማያባራው ወቀሳ አንገትህን የምትደፋው ፣ የምትሸማቀቀው አንተ ነህ ።

አዎ! ከእራስህ ጋር ሰላም ፍጠር ፣ ከእራስህ ጋር ተስማማ ፤ ለእራስህ ፍቅር ይኑርህ ፤ እራስህን ተረዳው ፤ ከሚጎዳው የትኛውም የሃሳብ ፍጪት ጠብቀው ። እራስህን የበደልከውን ያክል እራስህን መካስ እንደምትችል እወቅ ። ሳታውቀው ላደረስክበት እያንዳንዱ በደል እራስህን ይቅርታ ጠይቅ ፤ እራስህን በእራስህ ለማከም ፣ ውስጥህን ለመመልከት ፣ እውነተኛ ስሜትህን ለማድመጥ በቂ ጊዜ ይኑርህ ። ከውስጣዊ ማንነትትህ ጋር ሰላም ከሌለህ ምንም ብታደርግ ህይወት ትርጉም እንደማትሰጥህ ተረዳ ። ከየትኛውም ጊዜ በላይ ሁልጊዜ ለእራስህ ታስፈልገዋለህ ። ለማንም ለመድረስ እራስህን መውደድ ቀዳሚው እርምጃህ ነውና እንደ ውዴታ ሳይሆን እንደ ግዴታ እራስህን ውደድ፤ እራስህን አክብር ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q