Get Mystery Box with random crypto!

#እየነገርኩሽ_ነው #ለአንዳንድ_ሴቶች ፎቶ ፖስተሽ ኮሜንት ላይ #ቆንጆ ስላልተባልሽ አ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

#እየነገርኩሽ_ነው
#ለአንዳንድ_ሴቶች
ፎቶ ፖስተሽ ኮሜንት ላይ #ቆንጆ ስላልተባልሽ አልያም የምጠብቂውን ያክል #ላይክ ስላላገኘሽ ቁንጅናሽን የምትጠራጠሪ ከሆነ ሁነኛ ዘመድ ፈልጊና ፀበል ይውሰዱሽ አየሽ ማናችንም እኮ ቆንጆ መባልን አንጠላም ቁምነገሩ ግን በሰው ጭብጨባና ኮሜንት ከፍና ዝቅ የሚል ማንነት ሊኖረን አይገባም

ለምሳሌ እኔ አስተማሪ ፅሁፍ ፖስት ሳደርግ አስተያየተ ቢሰጠኝ ፣ ሼር ቢደረግና ለሌሎች ተደራሽ ቢሆን ደስ ይለኛል ነገር ግን እንደዛ አልተደረገልኝምና ፅሁፌ የማይረባ ነው ብዬ ከመፃፍ አልቦዝንም ምክኒያቱም ቢያንስ የአንድን ሰው ስሜት እንኳ መግለፅ እንደሚችል ሳልፖስተው በፊት ቀድሜ አውቀዋለሁና

እናም እልሻለሁ የምትጓዥበት መንገድ ወደ ጥሩ አልያም ወደ መጥፎ የሚመራው አንቺን እንጂ ተመልካችን አይደለም ፣ የምትለብሽው ልብስ የሚሞቀውም ሆነ የሚበርደው አንችኑ እንጂ የሚያይሽን አይደለም ፣ የምትበይው ምግብ የሚጣፍጠው ወይ የሚመረው አንቺን እንጂ ሌላውን አይደለም ልክ እንደዛ ሁሉ የመልክሽም ማማርና ማስጠላት አንቺ ለራስሽ ካለሽ አመለካከትና እሳቤ እንጂ በፌስቡክ መንደር እድርተኞች ኮሜንትና ላይክ አይደለም እናም አንድን ነገር ለታይታ ማድረግ ሞኞች የፈለሰፉት የመከበር ሙከራ መሆኑን ተረድተሽ በቀጥተኛው መንገድ ለመጓዝ ሞክሪ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q