Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የሰርጥ አድራሻ: @mirttshefoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 31.94K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 27

2023-02-27 04:16:24 የታየህን አሳይ!

አዲስ ንጋት፣ አዲስ ጀምበር፣ አዲስ ብረሃን፣ ልዩ በረከት፣ ልዩ ስጦታ ከአምላክ ውጪ ከሌላ የማይታደል፣ ከማንም የማይሰጥ እጅግ የተዋበ ስጦታ ዛሬ። በግሩም ቀን ግሩም ተግባር ያስፈልገናል። የአምላክን ድንቅ ስራ ማስታውስ፣ በፈጣሪ መልካም ተግባር መደነቅ፣ የእጆቹን ስራዎች ማስታወስ፣ በየመንገዱ የወደቁ ነፍሳትን መርዳት፣ ለወገን መድረስ፣ ወገንን ማሳረፍ፣ ከጎኑ መቆም፣ ከመጣበት መከራ በተቻለን አቅም ለመታደግ መጣር ይጠበቅብናል። አንዳንዴ ተፈጥሮ ትዛባለችና የእኛን የማስተካከል ድርሻ ትፈልጋለች። ሚዛኑን የሳተ ኑሮ መጨረሻው ጥፋት ነውና ሙሉ በሙሉ ሚዛኑን እንዲጠብቅ ማድረግ ባትችል እንኳን ደጋፊውን መደገፍና፣ ከጎን መቆም ትችላለህ። የንጋትህ እዳ አለብህ፣ በሰላም ያየሃት፣ በጤና የደረስክባት ብሩህዋ ዛሬ አደራ ጥላብሃለች። ያለምክንያት ለዛሬ አልደረስክም፣ የዛሬን ብረሃን በሙላት አልተመለከትክም።

አዎ! ጀግናዬ..! የታየህን አሳይ፣ ያለህን አካፍል፤ ብረሃኑን ለሌላውም አብራ፣ የአምላክህ ማመስገኛ ሁን፣ በመፅዋች እጆችህ መፅውት፣ የተራቡ ወገኖችህን፣ የተጠሙ ነፍሳትን ከልብህ አስባቸው፣ በቻልከው ድረስላቸው። ሰው መሆን ፈተና ነው፤ በተለይ የተቸገሩ ነፍሳትን እያዩ ዝም ማለት ሰውነትም አይደለም። ምንም ማድረግ ባትችል ከሁሉ የሚበልጥ ፀሎትና ተማፅኖን በጉያህ ይዘሃል። የፀሎት መፅሐፍህን አንሳ፣ ስለተቸገሩ ነፍሳት ፀልይ፣ ስለደከሙ እናት አባቶች ተማፅኖህን አቅርብ፣ ለሚሰቃዩት እንስሳት ቃልህን አውጣ። አዛኝ ልብ በመከራው ጊዜ እረፍት የለውም፤ በሰቆቃው ሰዓት ሰላም አይሰማውም፤ በእርዛቱ ሰዓት ሳቅ ጫወታ አያምረውም። አስተዋይ ነውና የወገኑ ህመም ያመዋል፤ ስቃዩ ይደርሰዋል፤ ችግሩን ይጋራዋል።

አዎ! ምናልባትም ካለህ መቁረስ ላይጠበቅብህ ይችላል፣ ህመማቸው ከተሰማህ፣ ችግራቸውን ከተጋራህ ግን ትልቁ አበርክቶትህ ይሆናል። ለወገን በማሰብ ውስጥ የሰውነት ደስታ አለ፤ ሰውን በመርዳት ውስጥ ጥልቁ ሰው የመሆን ባህሪ ይታያል። ማንም ለእራሱ እንደፈለገው በልቶ ጠጥቶ ማደር ላይከብደው ይችላል፣ ነገር ግን ሰው የመሆናችን አላማ ለእራስ ጉርሳችን ብቻ እንድንኖር አይደለም። ከእራስህ በላይ እጅህን ለሚጠብቁ፣ ምፁዋትህን ለሚናፍቁ ነፍሳት መድረስ እንዳለብህ አስብ። ተመችቶህም እያማረርክ፣ ሳይመችህም እያማረርክ ህይወትን መግፋት አትችልም። የፈጠሪህን መቅድም፣ የአምላክን መልካም ፍቃድ ጠይቅ። ጠንክረህ አጠንክራቸው፤ ጎብዘህ አጎብዛቸው፣ ሰርተህ አሰራቸው። የመጣህበትን የህይወት አላማ አሳካ። እንዲሁ ከንፈር መጠህ፣ አዝነህ፣ አንገትህን ደፍተህ ዝም የምትል እንዳልሆንክ አስተውል። አቅሙ አለህ፣ ብርታቱ አለህ፣ በበረከቱ ተሞልተሃልና ወገንህን ለመርዳት፣ ለመታደግ እንዲሁ የአምላክህን ፍፁም በረከት ለመቀበል ወደኋላ አትበል።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
679 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  01:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 06:35:53
#_እውነትን_ከውሸት
ትወጂኝ እንደሆን እያልኩ ሳሰላስል
ሆኖብኝ ተቸገርኩ ፍቅርሽ የጅብ ችኩል
የጅብማ ችኩል ቀንድ ይነክሳል አሉኝ
ፍቅር ጣቴን ብሰጥ ነክሰሽ አቆሰልሽኝ
ትቀበዪኝ ብዬ ፍቅር ልቤን ብሰጥ
አልቀበል ብለሽ አንቺን ስለማመጥ
ሰከሬ ወደኩኝ በጭካኔሽ መጠጥ
አደነጋገርሽኝ ግራም አጋባሽኝ
ምን ልበል ጨነቀኝ የማወራው ጠፋኝ
እንደስደተኛ መሄጃ አጣሁኝ
ሀገሬ ውስጥ ሆኜ ሰው ሀገር መሰለኝ
በአይኔስ አያለሁ አሳወርሽው ልቤን
አካሌስ እዚሁ ነው ገደል ከተትኩ ፍቅሬን
ለምን?አትበዪኝ ልቤ ከታወረ በምኔ አያለሁ
ሁሉ ጨልሞብኝ ሰው ያለህ እላለሁ
ሰውም ጨካኝ አይደል ሚደርስልኝ አጣሁ
መስጠት እየቻልሽ ድምቅ ያለ ብርሀን
ጭካኔን ጨክነሽ አጨለምሽው ልቤን
ያንቺስ አጃኢብ ነው እንዲያው ትገርሚያለሽ
እውነተኛ ፍቅሬን ውሸታም ትያለሽ መልሰሽ
እየደባለቅሽ እውነትን ከውሸት ውሸትን ከእውነት
አመቱን ወር አልሽው ወሩን ደግሞ አመት
አሁን ግን ከበደኝ መለመን አልችልም
ሂጂ ሸኝሻለሁ ፍቅር በልመና ፈፅሞ አይሆንም
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.6K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 22:13:18 አላበቃም!

አዎ! ልዩነትህን ስላላሳየክ፣ ማንነትህን ስላላስመሰከርክ፣ ስላላሸነፍክ፣ ያሰብክበት ቦታ ስላልደረስክ፤ የተመኘሀውን ህይወት በእጅህ ስላላስገባህ፤ የህይወት ትግልህን በድል ስላላጠናቀክ አላበቃም፤ ትግልህ በፍፁም አልተጠናቀቅም፤ አልጨረስክም። አንዳች የሚቀርህ ነገር እጅህ ላይ አለ፤ ገና ትልቅ ጀብድ ይጠብቅሃል፤ የተለየ አስደሳች ህይወት ከፊትህ አለ፤ ምንም ያልተነካ ወኔና ጉልበት ውስጥህ አለ። ብዙ የጀመርካቸው ጉዳዮች አንዳሉህ አትርሳ፤ እነርሱ ሳይጠናቀቁ ደግሞ ወዴትም አትሔድም። ጅምሮህን ተመልከት፤ ሃሳቦችህን አስተውል፤ በውስጥህ የሚመላለሱትን አስደናቂ እይታዎች አጢናቸው። ማድረግ ከብዶህ አይደለም፤ ወኔውንም አጥተህ አይደለም፤ ሳትችል ቀርተህም አይደለም፤ ከፍፃሜው የደረስክ ወይም የሚፈልገው ጥረት ከፍተኛ መስሎህ ይሆናል። ነገር ግን ያልጨረስከው ነገር ሁሌም ጅምር ሆኖ ይቀራልና ውጤት አይኖረውም፤ የድካምህን አይከፍልህም፣ ወጪህንም አይመልስም።

አዎ! ጀግናዬ..! አላበቃም! ከዳር ሳትደርስ በፍፁም አይገባደድም፤ የመጨረሻውን ሪቫን ሳትበጥስ የሚቋጭ ነገር አይኖርም፤ መጨረሻውን ሳታውቅ የምትዘጋው አጀንዳ የለም። የታየህን ከፍታ የምትቆናጠጠው ጉዞህን ስትፈፅም ብቻ ነው። የነገሮች መጨረሻ ሲያምር ደስ ያሰኛል፤ ከጉዞህ ባልተናነሰ ፍፃሜህም የተለየውን አስደናቂ ደስታ እንደሚያጎናፅፍህ አትጠራጠር። የጀመርከውን ጨርስ፤ አቅምህን አጎልብት፤ በእራሰ መተማመንህን አዳብር፤ ለተሻለ ተግባር እራስህን አዘጋጅ፤ ከአሸናፊነት ጋር ተሳሰር፤ ድልን የምታሳድድ፣ ግብህን የምትመታ፣ ህልምህን እውን የምታደርግ ብርቱ ሰው ሁን። የትኛውም ተግባርህ በሰው ፊት በኩራት የሚያቆምህ፣ አንገትህን ቀና የሚደርግህ፣ የልብ ልብ የሚሰጥህ ስለጀመርከው ሳይሆን አከናውነህ ስለ ጨረስከው ነው።

አዎ! ጅማሬው ከብዶሃል፤ ጫናዎቹ አዝለውሃል፤ ብዙዎች ግራ አጋብተውሃል፤ አፌዘውብሃል፤ ተሳልቀውብሃል፤ ተጫውተውብሃል። ነገር ግን ጉዞህ በዚ አያበቃም፤ እንዲሁ እንደቀላል አይቋጭም፤ በጅምርም አይቀርም። ከውጫዊው ጫና እኩል የሚሞግትህ ውስጣዊ ድምፅ አለ። "ለዚህማ እጅ አትስጥ፤ መጨረሻውን ተመልከት፤ ድልህን አክብር፤ ለዚህማ አታንስም" የሚልህ የእውነተኛ ማንነትህ መገለጫ ድምፅ አለ። ለእርሱ ጆሮ ከመስጠት አትቦዝን፤ ማንም ከሚያውቅህ በላይ እርሱ ያውቅሃል፤ ፍላጎትህ ይገባዋል፤ ምርጫህን ይረዳል። እስክታሸንፍ መፋለምህን እንዳታቆም፤ የናቁህን እስክታሳፍር መልፋትህን እንዳታቆም፤ ያጣሀውን እስክታገኝ፤ ምኞትህን እስክታሳካ፤ ከእራስህ በላይ ለሰዎች መትረፍ እስክትችል፤ ቤተሰቦችህ እስኪኮሩብህ፣ ማንነትህን እስክታሳይ በፍፁም እንዳተበገር፤ በጭራሽ እጅ እንዳትሰጥ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
981 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 22:12:53 በምርጫህ ተቀየር!

ምርጫን መኖርና የተመረጠልንን መኖር ትልቅ ልዩነት አለው። ውስጣዊ ምኞታችንን ከእኛ በላይ የሚያውቅ በሌለበት ዓለም አንዳንዴ ነገሮች ከምርጫችን ውጪ በተለየ መንገድ ህይወታችንን እንድንኖር ያደርጉናል። አንተስ የትኛውን እየኖርክ ነው? ህልምህን፣ ረዕይህን፣ ግብህን ወይስ ፍረሃትና ስጋትህን? በምን ውስጥ እየተመላለስክ ነው? በጭንቀት ወይስ በነፃነት ውስጥ? ምን ይዘህ ምን ለቀሃል? ፍቅርን ይዘህ ጥላቻን ለቀሃልን? ሰላምን ይዘህ አለመረጋጋትን ለቀሃልን? ደግነትን ይዘህ ክፋትን አስወግደሃልን? የተመረጡ መልካም በሀሪያት ይቆጣጠሩህና ይገልፁህ ዘንድ ፍቀድላቸው። ከፍረሃትህ በተሻለ ድፍረትህ ይግለፅህ፤ ከጭንቀትህ በላይ በነፃነትህ ታወቅ፤ ከክፋት በተሻለ ደግነትህ ይጎልብት። ምርጫህ እንዲያስከብርህ፣ እንዲያሳድግህ፣ እንዲያነሳህና እንዲያበለፅግህ አድርግ።

አዎ! ጀግናዬ..! በምርጫህ ተቀየር! ማንም ምንም እስኪልህ፣ እስኪጎተጉትህ፣ እስኪጨቀጭቅህ አትጠብቅ፤ እራስህ ፈልገህ መርጠህ፣ ወደህ፣ ፈቅደህ በምርጫህ ተቀየር፤ በፍላጎትህ ፍረሃትህን ስበር። የመረጥከውን እንዳትኖር የሚያግድህ አንድ ነገር ቢኖር እርሱም እራስህ ነህ፤ ፍረሃትህ ነው፤ ይሉኝታህ ነው፤ የበታችነትህ ነው፤ ለእራስህ የምትሰጠው ያልተገባ ስፍራ ነው። ህይወትህን የማቅለልም የማክበድም መብቱ አለህ። ዘወትር በቀላልና አደጋ በሌለው መንገድ እየተጓዝክ ቀላል ህይወት ልትኖር አትችልም። ለጊዜው የቀለለህና ከጫና ውጪ የተከነልህ ተግባር ለከባዱ ሁነት ብቁ አያደርግህም። ቀላሎቹ ተግባሮችህ አንተንም ቀላል ያደርጉሃል። ከባዱ ምርጫህና በድፍረት የተሞላው ተግባርህ ግን ቀላሉን ህይወት ያጎናፅፍሃል። ዛሬ ችግርህን ካልቀረፍክ ነገም ችግርህ ይቀጥላል። ዛሬ ከባዱን ተግባር ካልሞከርክ፣ ፍረሃትህን ካልተጋፈጥክ፣ ፍላጎትህን ካልኖርክ ነገ ክብደቱ በእጥፍ ጨምሮ፣ ፍረሃትህም አይነቱን ቀይሮ ይጠብቅሃል።

አዎ! ምርጫህ እንጂ ፍላጎትህ ብቻውን የትም አያደርስህም፤ ምኞትና አምሮትህ ብቻውን ለምንም አያበቃህም። ፍላጎትህን እውን ለማድረግ፣ ህልምህን ለመኖር፣ ራዕይህን ከዳር ለማድረስ በትክክለኛው መንገድ ማለፍ ይጠበቅብሃል። አደጋ የበዛበት ህይወት መምረጥህ ቢያጠነክርህ እንጂ አይጎዳህም፤ ፍረሃትህን ተሻግረህ ማለፍህ ለተሻለ ስፍራ ቢያበቃህ እንጂ አንተነትህን አያውከውም። እውነት ነው፣ ስለሞከርክ ትወድቃለህ፣ ከባዱን ስለመረጥክ ለአደጋ ትጋለጣለህ፣ ባልተለመደው ስለተጓዝክ አይን ትስባለህ ነገር ግን ለለውጥህ፣ ለእድገትህና ለህልምህ በጥቂቱ መክፈል ያለብህ ይህ ነው። የወደድከው ብቻ የተሻልክ አያደርግህም፤ ቀላሉ ብቻ ብቁና ብርቱ አያደርግህም። ያማረ የሰውነት አቋም ከፈለክ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅብሃል። ፍላጎትህን በትክክለኛ ምርጫ ደግፈው፤ ህልምህንም በማይናወጡ ውሳኔዎችህ አጎልብተው።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
947 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 04:33:35 ላንተ ታይቶሃል!

እንደ እብድ ቢመለከቱህ ፤ ጣታቸውን ቢቀስሩብህ ፣ ቢስቁብህ ፣ ቢሳለቁብህ ጉዳያቸው ካንተ ጋር ሳይሆን ከእውነተኛው ችሎታህና ህልምህ ጋር ነው ። ያሰኛቸውን ሊሉህና ሊያደርጉበህ ይችላሉ በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ያንተን ህልም እውን ሊያደርጉልህ አለመቻላቸው ነው ። መንገድህ ሁሉን ያካተተ ነው ፤ ውዴታንና ግዴታን ፣ ፍቅርና ጥላቻን ፣ መወደድንና መገፋትን ሁሉን በአንድ አዋህዶ የያዘ ነው ። አንዳንዶች ምን እንደምታደርግም አይገባቸውም ፣ ኬት እንደመጣህ አያውቁም ፣ ወዴት እንደምትጓዝ አይረዱም ፣ በምን እንደምትመራ አይገባቸውም ። ከእነርሱ ቃላትና መጥፎ እይታ በላይ የሚነዳህ ውስጣዊ ስሜት እንዳለ አያውቁም ፤ እርሱን ትተህ ተነጥለሀው መኖር እንደማትችል አያውቁም ። አላማ ያለው ሰው ያለምንም አስረጂና ማብራሪያ ከድርጊትህና ከንግግርህ ይረዳል ፤ ፍላጎትህን ከፊትህ ያነባል ። እንዲሁ በስሜት ትግባባላቹ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሲሆን ፣ ሲሳካ ፣ ከዳር ሲደርስ ላንተ ታይቶሃል ፤ አንተ በሚገባ ታውቀዋለህ ፤ የምታደርገው በደምብ ገብቶሃል ፤ መንገድህን ጠንቅቀህ ታውቀዋለህ ። ለምን ከጓደኞችህ ተነጠልክ ? ለምን አነጋገርህን ቀየርክ ? ለምን ውሎህን አስተካከልክ ? ለምን የምታነባቸውን መፅሐፍት ፣ የምትመለከታቸውን ፖሮግራሞች ፣ የምትከታተላቸውን ስልጠናዎች በጥንቃቄ መረጥክ ? በእርግጥም ከጀርባህ ትክክለኛና እውነተኛ ፍላጎት ስላለህ ነው ። ህልምህ ምንም ስለተባልክ የሚቆም አይደለም ፤ ምንም ስለደረሰብህ የሚገታ አይደለም ፤ ምንም ያክል ጊዜ ስለወደክ የሚቋረጥ አይደለም ፤ በማንም ስለተተቸህ ወደኋላ የሚመለስ አይደለም ። በእራስህ ህልምና ራዕይ ዙሪያ ካንተ በላይ እውቀትም ሆነ ግንዛቤው ያለው ሰው የለም ፤ ሊረዳህም የሚችል ሰው አይገኝም ። ሰዎች ቢረዱህም ባይረዱህም በእርግጥም ህልመኛ ከሆንክ ማንም እንዴትም ህልምህን ከመኖር ሊያስቆምህ አይችልም ። አዋቂ ያስተውላል ፣ ጠቢብ ባስተዋለው ልክ ሊረዳህና ሊያበረታታህ ይሞክራል ።

አዎ! የሰዎችን ስራ በመደጋገም የተጠመድ ፣ አንድም የእራሴ የሚለው ነገር የሌለው ፣ እንዴትም ለውጥ ያላስመዘገበ ሰው እንዲናገርህና ቅስምህን እንዲሰብር አትፍቀድ ። ለደካማ ሰው እራስህን አሳልፈህ አትስጥ ፤ ተግባር ላይ ለሌለ ቃላት ላይ ለሚበረታ ፣ ማበረታት ለማይችል ፣ ነገሮችን ሁሉ በአንድ አቅጣጫ ለሚመለከት ሰው ፊት አታሳይ ። የምታውቀውን ታውቃለህ ፤ የምታደርገውንም እንዲሁ ታውቃለህ ። ነገር ግን እውቀትህ ለእራስህ ነው ። የፈለከው ሁሉ በፈለከው መጠን አይረዳህም ፤ አያውቅልህም ። ዙሪያህን አስተውል የህልምህን ወኔ በሚቀሙህ ሰዎች ተከበሃልን ? ቀላል ያልከውን ጉዳይ ሲያካብዱ ትመለከታለህን ? አቅምህን በእራሳቸው አቅም አየለኩት ተቸግረሃልን ? በፍፁም አቅልለህ እንዳትመለከተው ።

አዎ! እራስህን በምትመለከትበት ልክ ባይመለከቱህም ሊረዱህ እንደሚገባ ግን አስብ ። ምርጫህ ምርጫቸው ባይሆንም ማክበር ግን ግዴታቸው ነው ። የሚያስፈልግህ የምትኖረውን ህይወት የሚመርጥልህ ፣ እያንዳንዱ እርምጃህ ላይ አሉታዊ አስተያየት የሚሰጥህ ፣ ወደኋላ የሚጎትተህ ሰው ሳይሆን ምርጫህን እንደምርጫህ ፣ ፍላጎትህን እንደተለየ ፍላጎት የሚያከብርልህና ማበረታታት ባይችል እንኳን እራስህን እንድትሆነ የሚተውህ ሰው ነው ። የታየህን ከማደረግ አትመለስ ፤ ያለምከውን ከማሳካት ወደኋላ አትበል ፤ አስቀድምህ ያለቀውን ተመልክተሃልና ትግበራው እንደማይከብድህ አስብ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.0K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  01:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 04:31:09 ያለህበት ላይ አተኩር!

ሁሉንም ደረጃ ለመውጣት እያንዳንዱን መመልከት አይጠበቅብህም ። ጀማሬው ላይ ከሆንክ ሙሉ ትኩረትህን ጅማሬው ላይ አድርግ ፤ መሐል ከደረስክም እንዲሁ ትኩረትህን መሐል ላይ አድርግ ። ስላለህበት ደረጃ በቂ እውቀት ካለህ ስለመጪው ባለማወቅህ አትጨነቅ ። ብርታትህ የዛሬ እርምጃህ እንጂ የወደፊትህ አይደለም ፤ አሁን ያለህበትን ሁኔታ ሳታልፍ ፣ የደረሰብህን መከራ ሳትወጣ ገና ያልተከሰተው ጋር መድረስ አትችልም ። ሁሉም ነገር የየራሱ ቅድመተከተል አለው ፤ የእራሱ ደረጃ አለው ፤ ውጣውረድ አለው ። መደበኛ ትምህርትህን በአግባቡ ሳታጠናቅቅ ለየትኛውም ክፍተኛ መዓረግ ልትበቃ አትችልም ። ደረጃ አንድን ሳትሻገር እንዴትም ደረጃ ሁለት ጋር አትደርስም ። የፊደል ገበታ እንኳን የእራሱ ቅድመተከተል አለው ።

አዎ! ጀግናዬ..! ያለህበት ላይ አተኩር! ስለቆምክበት አስብ ፤ ሰለደረስክበት በሚገባ እወቅ ፤ ያለህበትን ጠንቅቀህ ተረዳ ። ያለፈው አልፏል መጪውም በጊዜው ይመጣል ። ወደፊት የሚሆንን ነገር ልታውቅ ትችላለህ እውቀትህ ግን የዛሬውን ደረጃ ሳትሻገር እንድታልፍ አያደርግህም። ነገን በመደገፍ የዛሬው ድጋፍህን እንዳትጥል ። ነገሮች ተያያዦች ናቸው ፤ ከፍታው ጋር ለመድረስ በዝቅታው ውስጥ ማለፍ ይኖርብሃል ። ምንምእንኳን በስተመጨረሻ እንደሚሳካ ብታውቅም ከእርሱ በፊት የሚቀድመውን ግን የመፈፀም ግዴታ አለብህ ። ብርቱ ብርታቱ የሚለካው በአንድ ደረጃ ሳይሆን እንደየሁኔታው በሚሻገራቸው ከባድና ቀላል ውጣውረዶች ነው ። ዛሬ ባለህበት ስራ አትለካም ፤ በዛሬው ገቢህ አትመዘንም ነገር ግን ለተሻለው ስራ ለመብቃትና ከዛሬ የላቀ ገቢ ለማግኘት ለጊዜውም ቢሆን በዚህ መንገድ ማለፍ ይጠበቅብሃል ።

አዎ! ጊዜያዊ ሃላፊነትን መወጣት ለትልቅ ደረጃ ያበቃል ፤ አስፈላጊ የተባሉ ደረጃዎችን እየተሻገሩ መጓዝ ብቃትን ይጨምራል ፤ በሒደት ውስጥ ማለፍ የተሻለ ማንነትን ይገነባል ። ዛሬ አንድ ያልከው ትንሽ እርምጃህ ሲደጋገም ውጤቱ እያማረ ይመጣል ። ዋናው ጉዳይ የቀጣዩ እርምጃህ ክብደትና ቅለት ሳይሆን የዛሬው እርምጃህ በአግባቡ መታለፍ ነው ። ከመዳረሻህ የሚያደርስህ በጥቂት የጀመረው እንቅስቃሴህና ያልተቋረጠው ጥረትህ ነው ። በየትኛውም የህይወት ጉዞ ምናልባትም ልታውቅ የምትችለው በመሃል ያለውን ውጣውረድ ሳይሆን ያለህበትን ሁኔታ ነው ፤ እንዲሁም በጥቂቱ መጪውን ብትገምት ነው ፤ መሃሉ ግን ላንተም ሆነ ለተመልካች አይነገርም ፤ ግልፅም አይደለም ። መጪውን ትተህ በጊዜው የሚጠበቅብህን በአግባቡ ተወጣ ። ትኩረትህ የማያሳድገው ነገር የለምና ያለህበት ላይ በማተኮር በቅድሚያ እርሱን አሳድግ ፤ እርሱን ተሻገር ፤ በእርሱ መንገድ ያሰብከውን እውን አድርግ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
914 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  01:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 06:24:40
ይህቺን አስታወሳችኋት ያንን ሁሉ መከራና ስቃይ አሳልፋ ለዚህ ትልቅ ደረጃ ደርሳለች ። ለዚህ ነው ቶሎ ብላችሁ ተስፋ አትቁረጡ ምንለው ። ለማንኛውም የቲክቶክ አካውንቷንም ይኸው ብለናል ሁሉንም ነገር ከራሷ አንደበት ስሙላት https://www.tiktok.com/@lomi_birtukan?_t=8a8MpdLjLrK&_r=1
3.4K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 03:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 05:17:34
#_10ሩ_የመጥፎ_ሰዎች_ምልክቶች
1 አሉታዊነትን ያበዛሉ ያስፋፋሉ
2 የሰውን ስህተትን ከማረም ይልቅ ትችት ማብዛት ይወዳሉ ።
3 ምቀኞች ናቸው የሰው ስኬት እንቅልፍ ይነሳቸዋል ።
4 የሰው ልጅ ሰላም እነሱን ሠላም ያሳጣቸዋል ።
5 ሰውን እየጎዱ እራሳቸውን እንደ ተጎጂ ይቆጥራሉ ።
6 ስለራሳቸው እንጂ ስለሰው ግድ የላቸውም ።
7 ለመለውጥ ፍላጎት የላቸውም የሰው ልጅ ለውጥ ጥረት ላይ እንቅፋት ይሆናሉ ።
8 ማንኛውንም ስህተት ሲሰሩ ስህተታቸውን አይቀበሉም ይክዳሉ ።
9 ሁሌም የሰው ልጅ ስም በማጥፋት ይጠመዳሉ ሲሳካላቸው ደሞ ይረካሉ ።
10 ከውሃላ ሴራና ተንኮል እየሸረቡ በፊትለፊት ጥሩ ለመሆን ያስመስላሉ ።

ከእንደዚህ አይነት ሰዎች ፈጣሪ ይጠብቃቹ አቦ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
29 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 05:11:48 ቅድሚያ ለእራስሽ!

ሰዎች ነንና ፍቅር ፣ እንክብካቤና ጥበቃ በቀላሉ የሰዎች ባሪያ ፣ የሰዎች ተመፅዋችና ተደጋፊ ያደርገናል ፤ በፈለጋቸው መጠን ይዘክሩን ዘንድ ይፈቅድላቸዋል ። ከእነርሱ ለምናገኘው ነገር ስንል ያለነርሱ እራሳችንን ማሰብ አንፈልግም ። ሁሌም ነፃነታችን ከእነሱ የመጣ ፣ መሰረታዊውን ሰላማችንን እነርሱ የፈጠሩት ይመስለናል ፣ ያለእነርሱ ደስታችን ባዶ እንደሚሆን ይሰማናል ። እውነታው ግን እነርሱ ሲሔዱ ሁሉን ይዘወት መሔዳቸውና እኛንም ባዶ ማስቀረታቸው ነው ። ከአምላክ በቀር ታማኝ ምርኩዝ የለህም ፤ ከፈጣሪህ ውጪ የእውነተኛ ደስታና እርካታህ ምክንያት አታገኝም ። ያልሽው ስለተደረገልሽ ብቻ ሳይሆን በእራስሽ መንገድ ስለተደረገ ይበልጥ ስሜት ይሰጥሻል ። ምንም ያክል ብትሰበሪ በስተመጨረሻ ለእራስሽ የምትቀሪው አንቺ ብቻ ነሽ ። የሆንሽውን መቀበል መብትሽ ቢሆንም አለመቀበልሽም የእራሱ ጉዳት ይዞብሽ ይመጣል ። ሲቀር የሚቀር ነገር ተከትለሽ ለእራስሽ ባዳ አትሁኚ ።

አዎ! ጀግኒት..! ቅድሚያ ለእራስሽ! የሁሉም ነገር መሰረቷ አንቺ ነሽ ። ማንም ቢመጣ አንቺን ብሎ ነው ፤ ለማንም የምትተርፊው እራስሽን ሆነሽ ነው ፤ ገፅና ቁመናሽ በእራሱ የእውነተኛው ማንነትሽ መገለጫ አይደለም ። የሔደው ቢመለስ አይጠቅምሽም ፤ የተለየሽ ዳግም አብሮሽ ቢሆን እውነተኛውን ደስታ አይሰጥሽም ። ውጫዊውን ነገር ብታስቀድሚ ፣ ለእርሱ የተሻለ ትኩረት ብትሰጪ ለጊዜው ቢያረጋጋሽ እንጂ ዘላቂ መፍትሔ አይሆንሽም ። እራስሽን ስታስቀድሚ የምታዳምጪው ውስጥሽን ነው ፤ የምትኖሪው በእራስሽ መንገድ ለሰዎች በመትረፍ ነው ፤ ደስታሽን ከውስጥ ማንነትሽ ታገኚዋለሽ ። እራሱን የሚጠብቅ ፣ ለእራሱ የሚጠነቀቅ ፣ በቅድሚያ እራሱን ለማዳን የሚጥር ሰው እራሱን ከአደጋ ያነፃል ፤ ለሰዎችም ደህንነት ምክንያት ይሆናል ። ጥበቃሽ ትርጉም ቢሰጥሽ እንኳን የሚያድንሽ ግን ያ በሙሉ እምነት የጠበቅሽው ውጫዊ አካል ሳይሆን ፣ ሙሉ ትኩረትሽን የሳበው ሰውም ሳይሆን በውስጥሽ ያለው መንፈሳዊ እምነትሽ ነው ።

አዎ! ጀግናዬ..! አድካሚውን የህይወት ጉዞህን በስተመጨረሻ በግልፅ የምትጋፈጠው ብቻህን ነው ፤ የደረሱብህን በደሎች የምታክመው ለእራስህ ነው ፤ በገሃድ የተገፋህባቸውን አጀንዳዎች የምትታገለውም ብቻህን ነው ። የውስጥህን ስብራትና ሃዘን ማንም አያውቅም ፤ የሚረዳህም ሰው አይኖርም ። ለቃልህ ታምነህ ብትኖር የምታነግሰው እራስህን ነው ። እራስህን ብታስቀድም ፤ ለእራስህ ብታዝን ፣ እራስህን ብትንከባከብ ከእራስህ በላይ ለሰው መትረፍ ትችላለህ ። በቶሎ የሚሰበርና እራሱን መጠበቅ የማይችል ሰው እንዴትም ለሌላው ጠበቃና ከለላ ሊሆን አይችልም ። እራስህን ማስቀደምህ የጥንካሬህ ምክንያት ናውና ችላ አትበለው ። ከምንም በላይ ለደስታህ ፣ ለእርጋታህ ፣ ለሰላምህ ፣ ለውስጣዊ ሃሴትህ አንተው ዋነኛ ምክንያት ሆነህ ተገኝ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
43 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 05:10:00 አትታወክ!

ያንተ መንገድ የተለየ እንደሆነ አስተውል ፤ እውቀትህ ፣ ተነሳሽነትህ ፣ ወኔህ ፣ ጅማሬህ በሙሉ የተለየ ነው ። ማንም ጀረብናውን የማታውቀው ሰው በሚጓዘው ጉዞ እራስህን እያስተያየህ አትረበሽ ፤ ማንነቱን ከማታውቀው ሰው አንፃር እራስህን እየቃኘህ የበታችነት ስሜት አይሰማህ ። ምንም ብታደረግ ያንተ ከማንኛውም ሰው አደራረግና አፈፃፀም ይለያል ። ያንተን ጥበብ ማንም የለውም ፤ የሌላውን ጥበብም አንተ የለህም ። አንተ አንተ ነህ ፣ ያለህ ነገር በሙሉ አንተነትህን ማሳያ ነው ። ማንም ካንተ በተሻለ ሊሰራ ይችላል ፣ በልጦህ ሊገኝ ይችላል ፣ የተሻለ ውጤትም ሊያስመዘግብ ይችልላል ። ያንተ ጉዳይ ግን እርሱ አይደለም ። ጉዳይህ አንተና አንተ ብቻ ነህ ። ከንፅፅር የወጣህ እለት ህይወትህ ትክክለኛውን አቅጣጫ ይይዛል ።

አዎ! ጀግናዬ..! አትታወክ! በምታየው የሰዎች ስኬት አትረበሽ ፣ በሚሰማህ የበታችነት ስሜት አትጨነቅ ። ለየትኛውም የህይወትህ መታወክ ምክንያቱ ውደድር ከሆነ አስወግደው ። ምንም ስራ ስራህ ሁሌም ኩራትህ ሊሆን ይገባል ። ውድድር ዋነኛው የውድቀትህ ምክንያት ነውና የሌሎችን ተሽሎ መገኘት አቁም ። ሰዎችን ስታይ እራስህን ታጣለህ ፤ ሰዎችን ስትመለከት ማንነትህን ታሳንሳለህ ፤ በሰዎች ስራ እራስህን ስትለካ የእራስህን አለምና አላማ ታጣለህ ። ያደረከውን አድርገሃልና እራስህ ላይ ህፀፅ በማውጣት አትጠመድ ፤ እራስህን በማሳነስ አንሰህ አትገኝ ። ማንም ሰው የእራሱ ሩጫ አለበት ፣ ትኩረትህን የእራስህ የግል ሩጫ ላይ አድርግ ። ማንንም ባትበልጥ ፣ ከማንም ባትሻል ከትናንትናው ማንነትህ ተሽለህ ከተገኘህ ከዚህ የሚልቅ ስኬት ሊኖርህ አይችልም ።

አዎ! እድገትን ከፈለክ በሰዎች ስኬት ተደሰት ፤ ለውጥን ከተመኘህ የእራስህን አመጣጥ አስተውል ። እውነተኛው ማንነትህ ከሰዎች ጋር በምታደርገው ውድድር ውስጥ ሳይሆን ከእራስህ ጋር በምታደርገው ውድድር ነው ። እራስህን ታውቃለህ ፣ እራስህን ማወቅህ በየጊዜው እያሻሻለህ የሚቀጥል ምርጡ ሃይልህ ነው ። እያንዳንዳዷን ለውጥህን አስተውል ፤ ትንሿን ስኬትህን አክብር ፤ ለትንሿ አፈፃፀምህ ቦታ ይኑርህ ፤ የእራስህ ብርታትና ጥንካሬ ከመሆን አትቦዝን ። ብዙዎችን ትመለከታለህ ነገር ግን ልኬትህ የእነርሱ ከፍታና ስኬት አይደለም ። የምታደርገውን ታውቃለህ ፣ እውቀትህም አንተንና አንተን የማሻሻል ፣ የማሳደግና ወደ ላቀው ከፍታ የማሸጋገር ሃይል አለው ። የተሻለው ይገባሃልና ከሰዎች ጋር መወዳደሩን አቁም ፤ ልኬትህ የእራስህ እይታ ነውና በማንም ከፍታ አትታወክ ። የእራስህን ከፍታ ገንባ ፤ የእራስህን ግብ በእራስህ መንገድ ምታ ። የሚረብሽህን አላስፈላጊ ፉክክር አስወግድ ፤ ማሳካት የምትፈለገውን ነገር እንደእራስህ ሆነህ አሳካ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
45 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ