Get Mystery Box with random crypto!

ላንተ ታይቶሃል! እንደ እብድ ቢመለከቱህ ፤ ጣታቸውን ቢቀስሩብህ ፣ ቢስቁብህ ፣ ቢሳለቁብህ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ላንተ ታይቶሃል!

እንደ እብድ ቢመለከቱህ ፤ ጣታቸውን ቢቀስሩብህ ፣ ቢስቁብህ ፣ ቢሳለቁብህ ጉዳያቸው ካንተ ጋር ሳይሆን ከእውነተኛው ችሎታህና ህልምህ ጋር ነው ። ያሰኛቸውን ሊሉህና ሊያደርጉበህ ይችላሉ በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ያንተን ህልም እውን ሊያደርጉልህ አለመቻላቸው ነው ። መንገድህ ሁሉን ያካተተ ነው ፤ ውዴታንና ግዴታን ፣ ፍቅርና ጥላቻን ፣ መወደድንና መገፋትን ሁሉን በአንድ አዋህዶ የያዘ ነው ። አንዳንዶች ምን እንደምታደርግም አይገባቸውም ፣ ኬት እንደመጣህ አያውቁም ፣ ወዴት እንደምትጓዝ አይረዱም ፣ በምን እንደምትመራ አይገባቸውም ። ከእነርሱ ቃላትና መጥፎ እይታ በላይ የሚነዳህ ውስጣዊ ስሜት እንዳለ አያውቁም ፤ እርሱን ትተህ ተነጥለሀው መኖር እንደማትችል አያውቁም ። አላማ ያለው ሰው ያለምንም አስረጂና ማብራሪያ ከድርጊትህና ከንግግርህ ይረዳል ፤ ፍላጎትህን ከፊትህ ያነባል ። እንዲሁ በስሜት ትግባባላቹ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሲሆን ፣ ሲሳካ ፣ ከዳር ሲደርስ ላንተ ታይቶሃል ፤ አንተ በሚገባ ታውቀዋለህ ፤ የምታደርገው በደምብ ገብቶሃል ፤ መንገድህን ጠንቅቀህ ታውቀዋለህ ። ለምን ከጓደኞችህ ተነጠልክ ? ለምን አነጋገርህን ቀየርክ ? ለምን ውሎህን አስተካከልክ ? ለምን የምታነባቸውን መፅሐፍት ፣ የምትመለከታቸውን ፖሮግራሞች ፣ የምትከታተላቸውን ስልጠናዎች በጥንቃቄ መረጥክ ? በእርግጥም ከጀርባህ ትክክለኛና እውነተኛ ፍላጎት ስላለህ ነው ። ህልምህ ምንም ስለተባልክ የሚቆም አይደለም ፤ ምንም ስለደረሰብህ የሚገታ አይደለም ፤ ምንም ያክል ጊዜ ስለወደክ የሚቋረጥ አይደለም ፤ በማንም ስለተተቸህ ወደኋላ የሚመለስ አይደለም ። በእራስህ ህልምና ራዕይ ዙሪያ ካንተ በላይ እውቀትም ሆነ ግንዛቤው ያለው ሰው የለም ፤ ሊረዳህም የሚችል ሰው አይገኝም ። ሰዎች ቢረዱህም ባይረዱህም በእርግጥም ህልመኛ ከሆንክ ማንም እንዴትም ህልምህን ከመኖር ሊያስቆምህ አይችልም ። አዋቂ ያስተውላል ፣ ጠቢብ ባስተዋለው ልክ ሊረዳህና ሊያበረታታህ ይሞክራል ።

አዎ! የሰዎችን ስራ በመደጋገም የተጠመድ ፣ አንድም የእራሴ የሚለው ነገር የሌለው ፣ እንዴትም ለውጥ ያላስመዘገበ ሰው እንዲናገርህና ቅስምህን እንዲሰብር አትፍቀድ ። ለደካማ ሰው እራስህን አሳልፈህ አትስጥ ፤ ተግባር ላይ ለሌለ ቃላት ላይ ለሚበረታ ፣ ማበረታት ለማይችል ፣ ነገሮችን ሁሉ በአንድ አቅጣጫ ለሚመለከት ሰው ፊት አታሳይ ። የምታውቀውን ታውቃለህ ፤ የምታደርገውንም እንዲሁ ታውቃለህ ። ነገር ግን እውቀትህ ለእራስህ ነው ። የፈለከው ሁሉ በፈለከው መጠን አይረዳህም ፤ አያውቅልህም ። ዙሪያህን አስተውል የህልምህን ወኔ በሚቀሙህ ሰዎች ተከበሃልን ? ቀላል ያልከውን ጉዳይ ሲያካብዱ ትመለከታለህን ? አቅምህን በእራሳቸው አቅም አየለኩት ተቸግረሃልን ? በፍፁም አቅልለህ እንዳትመለከተው ።

አዎ! እራስህን በምትመለከትበት ልክ ባይመለከቱህም ሊረዱህ እንደሚገባ ግን አስብ ። ምርጫህ ምርጫቸው ባይሆንም ማክበር ግን ግዴታቸው ነው ። የሚያስፈልግህ የምትኖረውን ህይወት የሚመርጥልህ ፣ እያንዳንዱ እርምጃህ ላይ አሉታዊ አስተያየት የሚሰጥህ ፣ ወደኋላ የሚጎትተህ ሰው ሳይሆን ምርጫህን እንደምርጫህ ፣ ፍላጎትህን እንደተለየ ፍላጎት የሚያከብርልህና ማበረታታት ባይችል እንኳን እራስህን እንድትሆነ የሚተውህ ሰው ነው ። የታየህን ከማደረግ አትመለስ ፤ ያለምከውን ከማሳካት ወደኋላ አትበል ፤ አስቀድምህ ያለቀውን ተመልክተሃልና ትግበራው እንደማይከብድህ አስብ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q