Get Mystery Box with random crypto!

በምርጫህ ተቀየር! ምርጫን መኖርና የተመረጠልንን መኖር ትልቅ ልዩነት አለው። ውስጣዊ ምኞታችንን | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

በምርጫህ ተቀየር!

ምርጫን መኖርና የተመረጠልንን መኖር ትልቅ ልዩነት አለው። ውስጣዊ ምኞታችንን ከእኛ በላይ የሚያውቅ በሌለበት ዓለም አንዳንዴ ነገሮች ከምርጫችን ውጪ በተለየ መንገድ ህይወታችንን እንድንኖር ያደርጉናል። አንተስ የትኛውን እየኖርክ ነው? ህልምህን፣ ረዕይህን፣ ግብህን ወይስ ፍረሃትና ስጋትህን? በምን ውስጥ እየተመላለስክ ነው? በጭንቀት ወይስ በነፃነት ውስጥ? ምን ይዘህ ምን ለቀሃል? ፍቅርን ይዘህ ጥላቻን ለቀሃልን? ሰላምን ይዘህ አለመረጋጋትን ለቀሃልን? ደግነትን ይዘህ ክፋትን አስወግደሃልን? የተመረጡ መልካም በሀሪያት ይቆጣጠሩህና ይገልፁህ ዘንድ ፍቀድላቸው። ከፍረሃትህ በተሻለ ድፍረትህ ይግለፅህ፤ ከጭንቀትህ በላይ በነፃነትህ ታወቅ፤ ከክፋት በተሻለ ደግነትህ ይጎልብት። ምርጫህ እንዲያስከብርህ፣ እንዲያሳድግህ፣ እንዲያነሳህና እንዲያበለፅግህ አድርግ።

አዎ! ጀግናዬ..! በምርጫህ ተቀየር! ማንም ምንም እስኪልህ፣ እስኪጎተጉትህ፣ እስኪጨቀጭቅህ አትጠብቅ፤ እራስህ ፈልገህ መርጠህ፣ ወደህ፣ ፈቅደህ በምርጫህ ተቀየር፤ በፍላጎትህ ፍረሃትህን ስበር። የመረጥከውን እንዳትኖር የሚያግድህ አንድ ነገር ቢኖር እርሱም እራስህ ነህ፤ ፍረሃትህ ነው፤ ይሉኝታህ ነው፤ የበታችነትህ ነው፤ ለእራስህ የምትሰጠው ያልተገባ ስፍራ ነው። ህይወትህን የማቅለልም የማክበድም መብቱ አለህ። ዘወትር በቀላልና አደጋ በሌለው መንገድ እየተጓዝክ ቀላል ህይወት ልትኖር አትችልም። ለጊዜው የቀለለህና ከጫና ውጪ የተከነልህ ተግባር ለከባዱ ሁነት ብቁ አያደርግህም። ቀላሎቹ ተግባሮችህ አንተንም ቀላል ያደርጉሃል። ከባዱ ምርጫህና በድፍረት የተሞላው ተግባርህ ግን ቀላሉን ህይወት ያጎናፅፍሃል። ዛሬ ችግርህን ካልቀረፍክ ነገም ችግርህ ይቀጥላል። ዛሬ ከባዱን ተግባር ካልሞከርክ፣ ፍረሃትህን ካልተጋፈጥክ፣ ፍላጎትህን ካልኖርክ ነገ ክብደቱ በእጥፍ ጨምሮ፣ ፍረሃትህም አይነቱን ቀይሮ ይጠብቅሃል።

አዎ! ምርጫህ እንጂ ፍላጎትህ ብቻውን የትም አያደርስህም፤ ምኞትና አምሮትህ ብቻውን ለምንም አያበቃህም። ፍላጎትህን እውን ለማድረግ፣ ህልምህን ለመኖር፣ ራዕይህን ከዳር ለማድረስ በትክክለኛው መንገድ ማለፍ ይጠበቅብሃል። አደጋ የበዛበት ህይወት መምረጥህ ቢያጠነክርህ እንጂ አይጎዳህም፤ ፍረሃትህን ተሻግረህ ማለፍህ ለተሻለ ስፍራ ቢያበቃህ እንጂ አንተነትህን አያውከውም። እውነት ነው፣ ስለሞከርክ ትወድቃለህ፣ ከባዱን ስለመረጥክ ለአደጋ ትጋለጣለህ፣ ባልተለመደው ስለተጓዝክ አይን ትስባለህ ነገር ግን ለለውጥህ፣ ለእድገትህና ለህልምህ በጥቂቱ መክፈል ያለብህ ይህ ነው። የወደድከው ብቻ የተሻልክ አያደርግህም፤ ቀላሉ ብቻ ብቁና ብርቱ አያደርግህም። ያማረ የሰውነት አቋም ከፈለክ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅብሃል። ፍላጎትህን በትክክለኛ ምርጫ ደግፈው፤ ህልምህንም በማይናወጡ ውሳኔዎችህ አጎልብተው።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q