Get Mystery Box with random crypto!

አላበቃም! አዎ! ልዩነትህን ስላላሳየክ፣ ማንነትህን ስላላስመሰከርክ፣ ስላላሸነፍክ፣ ያሰብክበት ቦ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

አላበቃም!

አዎ! ልዩነትህን ስላላሳየክ፣ ማንነትህን ስላላስመሰከርክ፣ ስላላሸነፍክ፣ ያሰብክበት ቦታ ስላልደረስክ፤ የተመኘሀውን ህይወት በእጅህ ስላላስገባህ፤ የህይወት ትግልህን በድል ስላላጠናቀክ አላበቃም፤ ትግልህ በፍፁም አልተጠናቀቅም፤ አልጨረስክም። አንዳች የሚቀርህ ነገር እጅህ ላይ አለ፤ ገና ትልቅ ጀብድ ይጠብቅሃል፤ የተለየ አስደሳች ህይወት ከፊትህ አለ፤ ምንም ያልተነካ ወኔና ጉልበት ውስጥህ አለ። ብዙ የጀመርካቸው ጉዳዮች አንዳሉህ አትርሳ፤ እነርሱ ሳይጠናቀቁ ደግሞ ወዴትም አትሔድም። ጅምሮህን ተመልከት፤ ሃሳቦችህን አስተውል፤ በውስጥህ የሚመላለሱትን አስደናቂ እይታዎች አጢናቸው። ማድረግ ከብዶህ አይደለም፤ ወኔውንም አጥተህ አይደለም፤ ሳትችል ቀርተህም አይደለም፤ ከፍፃሜው የደረስክ ወይም የሚፈልገው ጥረት ከፍተኛ መስሎህ ይሆናል። ነገር ግን ያልጨረስከው ነገር ሁሌም ጅምር ሆኖ ይቀራልና ውጤት አይኖረውም፤ የድካምህን አይከፍልህም፣ ወጪህንም አይመልስም።

አዎ! ጀግናዬ..! አላበቃም! ከዳር ሳትደርስ በፍፁም አይገባደድም፤ የመጨረሻውን ሪቫን ሳትበጥስ የሚቋጭ ነገር አይኖርም፤ መጨረሻውን ሳታውቅ የምትዘጋው አጀንዳ የለም። የታየህን ከፍታ የምትቆናጠጠው ጉዞህን ስትፈፅም ብቻ ነው። የነገሮች መጨረሻ ሲያምር ደስ ያሰኛል፤ ከጉዞህ ባልተናነሰ ፍፃሜህም የተለየውን አስደናቂ ደስታ እንደሚያጎናፅፍህ አትጠራጠር። የጀመርከውን ጨርስ፤ አቅምህን አጎልብት፤ በእራሰ መተማመንህን አዳብር፤ ለተሻለ ተግባር እራስህን አዘጋጅ፤ ከአሸናፊነት ጋር ተሳሰር፤ ድልን የምታሳድድ፣ ግብህን የምትመታ፣ ህልምህን እውን የምታደርግ ብርቱ ሰው ሁን። የትኛውም ተግባርህ በሰው ፊት በኩራት የሚያቆምህ፣ አንገትህን ቀና የሚደርግህ፣ የልብ ልብ የሚሰጥህ ስለጀመርከው ሳይሆን አከናውነህ ስለ ጨረስከው ነው።

አዎ! ጅማሬው ከብዶሃል፤ ጫናዎቹ አዝለውሃል፤ ብዙዎች ግራ አጋብተውሃል፤ አፌዘውብሃል፤ ተሳልቀውብሃል፤ ተጫውተውብሃል። ነገር ግን ጉዞህ በዚ አያበቃም፤ እንዲሁ እንደቀላል አይቋጭም፤ በጅምርም አይቀርም። ከውጫዊው ጫና እኩል የሚሞግትህ ውስጣዊ ድምፅ አለ። "ለዚህማ እጅ አትስጥ፤ መጨረሻውን ተመልከት፤ ድልህን አክብር፤ ለዚህማ አታንስም" የሚልህ የእውነተኛ ማንነትህ መገለጫ ድምፅ አለ። ለእርሱ ጆሮ ከመስጠት አትቦዝን፤ ማንም ከሚያውቅህ በላይ እርሱ ያውቅሃል፤ ፍላጎትህ ይገባዋል፤ ምርጫህን ይረዳል። እስክታሸንፍ መፋለምህን እንዳታቆም፤ የናቁህን እስክታሳፍር መልፋትህን እንዳታቆም፤ ያጣሀውን እስክታገኝ፤ ምኞትህን እስክታሳካ፤ ከእራስህ በላይ ለሰዎች መትረፍ እስክትችል፤ ቤተሰቦችህ እስኪኮሩብህ፣ ማንነትህን እስክታሳይ በፍፁም እንዳተበገር፤ በጭራሽ እጅ እንዳትሰጥ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q