Get Mystery Box with random crypto!

#_እውነትን_ከውሸት ትወጂኝ እንደሆን እያልኩ ሳሰላስል ሆኖብኝ ተቸገርኩ ፍቅርሽ የጅብ ችኩል የጅብ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

#_እውነትን_ከውሸት
ትወጂኝ እንደሆን እያልኩ ሳሰላስል
ሆኖብኝ ተቸገርኩ ፍቅርሽ የጅብ ችኩል
የጅብማ ችኩል ቀንድ ይነክሳል አሉኝ
ፍቅር ጣቴን ብሰጥ ነክሰሽ አቆሰልሽኝ
ትቀበዪኝ ብዬ ፍቅር ልቤን ብሰጥ
አልቀበል ብለሽ አንቺን ስለማመጥ
ሰከሬ ወደኩኝ በጭካኔሽ መጠጥ
አደነጋገርሽኝ ግራም አጋባሽኝ
ምን ልበል ጨነቀኝ የማወራው ጠፋኝ
እንደስደተኛ መሄጃ አጣሁኝ
ሀገሬ ውስጥ ሆኜ ሰው ሀገር መሰለኝ
በአይኔስ አያለሁ አሳወርሽው ልቤን
አካሌስ እዚሁ ነው ገደል ከተትኩ ፍቅሬን
ለምን?አትበዪኝ ልቤ ከታወረ በምኔ አያለሁ
ሁሉ ጨልሞብኝ ሰው ያለህ እላለሁ
ሰውም ጨካኝ አይደል ሚደርስልኝ አጣሁ
መስጠት እየቻልሽ ድምቅ ያለ ብርሀን
ጭካኔን ጨክነሽ አጨለምሽው ልቤን
ያንቺስ አጃኢብ ነው እንዲያው ትገርሚያለሽ
እውነተኛ ፍቅሬን ውሸታም ትያለሽ መልሰሽ
እየደባለቅሽ እውነትን ከውሸት ውሸትን ከእውነት
አመቱን ወር አልሽው ወሩን ደግሞ አመት
አሁን ግን ከበደኝ መለመን አልችልም
ሂጂ ሸኝሻለሁ ፍቅር በልመና ፈፅሞ አይሆንም
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q