Get Mystery Box with random crypto!

ቅድሚያ ለእራስሽ! ሰዎች ነንና ፍቅር ፣ እንክብካቤና ጥበቃ በቀላሉ የሰዎች ባሪያ ፣ የሰዎች | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ቅድሚያ ለእራስሽ!

ሰዎች ነንና ፍቅር ፣ እንክብካቤና ጥበቃ በቀላሉ የሰዎች ባሪያ ፣ የሰዎች ተመፅዋችና ተደጋፊ ያደርገናል ፤ በፈለጋቸው መጠን ይዘክሩን ዘንድ ይፈቅድላቸዋል ። ከእነርሱ ለምናገኘው ነገር ስንል ያለነርሱ እራሳችንን ማሰብ አንፈልግም ። ሁሌም ነፃነታችን ከእነሱ የመጣ ፣ መሰረታዊውን ሰላማችንን እነርሱ የፈጠሩት ይመስለናል ፣ ያለእነርሱ ደስታችን ባዶ እንደሚሆን ይሰማናል ። እውነታው ግን እነርሱ ሲሔዱ ሁሉን ይዘወት መሔዳቸውና እኛንም ባዶ ማስቀረታቸው ነው ። ከአምላክ በቀር ታማኝ ምርኩዝ የለህም ፤ ከፈጣሪህ ውጪ የእውነተኛ ደስታና እርካታህ ምክንያት አታገኝም ። ያልሽው ስለተደረገልሽ ብቻ ሳይሆን በእራስሽ መንገድ ስለተደረገ ይበልጥ ስሜት ይሰጥሻል ። ምንም ያክል ብትሰበሪ በስተመጨረሻ ለእራስሽ የምትቀሪው አንቺ ብቻ ነሽ ። የሆንሽውን መቀበል መብትሽ ቢሆንም አለመቀበልሽም የእራሱ ጉዳት ይዞብሽ ይመጣል ። ሲቀር የሚቀር ነገር ተከትለሽ ለእራስሽ ባዳ አትሁኚ ።

አዎ! ጀግኒት..! ቅድሚያ ለእራስሽ! የሁሉም ነገር መሰረቷ አንቺ ነሽ ። ማንም ቢመጣ አንቺን ብሎ ነው ፤ ለማንም የምትተርፊው እራስሽን ሆነሽ ነው ፤ ገፅና ቁመናሽ በእራሱ የእውነተኛው ማንነትሽ መገለጫ አይደለም ። የሔደው ቢመለስ አይጠቅምሽም ፤ የተለየሽ ዳግም አብሮሽ ቢሆን እውነተኛውን ደስታ አይሰጥሽም ። ውጫዊውን ነገር ብታስቀድሚ ፣ ለእርሱ የተሻለ ትኩረት ብትሰጪ ለጊዜው ቢያረጋጋሽ እንጂ ዘላቂ መፍትሔ አይሆንሽም ። እራስሽን ስታስቀድሚ የምታዳምጪው ውስጥሽን ነው ፤ የምትኖሪው በእራስሽ መንገድ ለሰዎች በመትረፍ ነው ፤ ደስታሽን ከውስጥ ማንነትሽ ታገኚዋለሽ ። እራሱን የሚጠብቅ ፣ ለእራሱ የሚጠነቀቅ ፣ በቅድሚያ እራሱን ለማዳን የሚጥር ሰው እራሱን ከአደጋ ያነፃል ፤ ለሰዎችም ደህንነት ምክንያት ይሆናል ። ጥበቃሽ ትርጉም ቢሰጥሽ እንኳን የሚያድንሽ ግን ያ በሙሉ እምነት የጠበቅሽው ውጫዊ አካል ሳይሆን ፣ ሙሉ ትኩረትሽን የሳበው ሰውም ሳይሆን በውስጥሽ ያለው መንፈሳዊ እምነትሽ ነው ።

አዎ! ጀግናዬ..! አድካሚውን የህይወት ጉዞህን በስተመጨረሻ በግልፅ የምትጋፈጠው ብቻህን ነው ፤ የደረሱብህን በደሎች የምታክመው ለእራስህ ነው ፤ በገሃድ የተገፋህባቸውን አጀንዳዎች የምትታገለውም ብቻህን ነው ። የውስጥህን ስብራትና ሃዘን ማንም አያውቅም ፤ የሚረዳህም ሰው አይኖርም ። ለቃልህ ታምነህ ብትኖር የምታነግሰው እራስህን ነው ። እራስህን ብታስቀድም ፤ ለእራስህ ብታዝን ፣ እራስህን ብትንከባከብ ከእራስህ በላይ ለሰው መትረፍ ትችላለህ ። በቶሎ የሚሰበርና እራሱን መጠበቅ የማይችል ሰው እንዴትም ለሌላው ጠበቃና ከለላ ሊሆን አይችልም ። እራስህን ማስቀደምህ የጥንካሬህ ምክንያት ናውና ችላ አትበለው ። ከምንም በላይ ለደስታህ ፣ ለእርጋታህ ፣ ለሰላምህ ፣ ለውስጣዊ ሃሴትህ አንተው ዋነኛ ምክንያት ሆነህ ተገኝ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q