Get Mystery Box with random crypto!

አትታወክ! ያንተ መንገድ የተለየ እንደሆነ አስተውል ፤ እውቀትህ ፣ ተነሳሽነትህ ፣ ወኔህ ፣ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

አትታወክ!

ያንተ መንገድ የተለየ እንደሆነ አስተውል ፤ እውቀትህ ፣ ተነሳሽነትህ ፣ ወኔህ ፣ ጅማሬህ በሙሉ የተለየ ነው ። ማንም ጀረብናውን የማታውቀው ሰው በሚጓዘው ጉዞ እራስህን እያስተያየህ አትረበሽ ፤ ማንነቱን ከማታውቀው ሰው አንፃር እራስህን እየቃኘህ የበታችነት ስሜት አይሰማህ ። ምንም ብታደረግ ያንተ ከማንኛውም ሰው አደራረግና አፈፃፀም ይለያል ። ያንተን ጥበብ ማንም የለውም ፤ የሌላውን ጥበብም አንተ የለህም ። አንተ አንተ ነህ ፣ ያለህ ነገር በሙሉ አንተነትህን ማሳያ ነው ። ማንም ካንተ በተሻለ ሊሰራ ይችላል ፣ በልጦህ ሊገኝ ይችላል ፣ የተሻለ ውጤትም ሊያስመዘግብ ይችልላል ። ያንተ ጉዳይ ግን እርሱ አይደለም ። ጉዳይህ አንተና አንተ ብቻ ነህ ። ከንፅፅር የወጣህ እለት ህይወትህ ትክክለኛውን አቅጣጫ ይይዛል ።

አዎ! ጀግናዬ..! አትታወክ! በምታየው የሰዎች ስኬት አትረበሽ ፣ በሚሰማህ የበታችነት ስሜት አትጨነቅ ። ለየትኛውም የህይወትህ መታወክ ምክንያቱ ውደድር ከሆነ አስወግደው ። ምንም ስራ ስራህ ሁሌም ኩራትህ ሊሆን ይገባል ። ውድድር ዋነኛው የውድቀትህ ምክንያት ነውና የሌሎችን ተሽሎ መገኘት አቁም ። ሰዎችን ስታይ እራስህን ታጣለህ ፤ ሰዎችን ስትመለከት ማንነትህን ታሳንሳለህ ፤ በሰዎች ስራ እራስህን ስትለካ የእራስህን አለምና አላማ ታጣለህ ። ያደረከውን አድርገሃልና እራስህ ላይ ህፀፅ በማውጣት አትጠመድ ፤ እራስህን በማሳነስ አንሰህ አትገኝ ። ማንም ሰው የእራሱ ሩጫ አለበት ፣ ትኩረትህን የእራስህ የግል ሩጫ ላይ አድርግ ። ማንንም ባትበልጥ ፣ ከማንም ባትሻል ከትናንትናው ማንነትህ ተሽለህ ከተገኘህ ከዚህ የሚልቅ ስኬት ሊኖርህ አይችልም ።

አዎ! እድገትን ከፈለክ በሰዎች ስኬት ተደሰት ፤ ለውጥን ከተመኘህ የእራስህን አመጣጥ አስተውል ። እውነተኛው ማንነትህ ከሰዎች ጋር በምታደርገው ውድድር ውስጥ ሳይሆን ከእራስህ ጋር በምታደርገው ውድድር ነው ። እራስህን ታውቃለህ ፣ እራስህን ማወቅህ በየጊዜው እያሻሻለህ የሚቀጥል ምርጡ ሃይልህ ነው ። እያንዳንዳዷን ለውጥህን አስተውል ፤ ትንሿን ስኬትህን አክብር ፤ ለትንሿ አፈፃፀምህ ቦታ ይኑርህ ፤ የእራስህ ብርታትና ጥንካሬ ከመሆን አትቦዝን ። ብዙዎችን ትመለከታለህ ነገር ግን ልኬትህ የእነርሱ ከፍታና ስኬት አይደለም ። የምታደርገውን ታውቃለህ ፣ እውቀትህም አንተንና አንተን የማሻሻል ፣ የማሳደግና ወደ ላቀው ከፍታ የማሸጋገር ሃይል አለው ። የተሻለው ይገባሃልና ከሰዎች ጋር መወዳደሩን አቁም ፤ ልኬትህ የእራስህ እይታ ነውና በማንም ከፍታ አትታወክ ። የእራስህን ከፍታ ገንባ ፤ የእራስህን ግብ በእራስህ መንገድ ምታ ። የሚረብሽህን አላስፈላጊ ፉክክር አስወግድ ፤ ማሳካት የምትፈለገውን ነገር እንደእራስህ ሆነህ አሳካ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q