Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የሰርጥ አድራሻ: @mirttshefoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 31.87K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 28

2023-02-23 07:25:03 ካንተ ነው!

በደል ነፍስህን ባደማች ወቅት ፣ ሀጢያት ባስነወረህ ሰዓት ፣ ጥፋትህ ባሳሰረህ ወቅት ፣ አምላክህን እንዳስቀየምክ በተሰማህ ጊዜ ይህን እያልክ ተማፀነው ፣ እራስህንም አፅናና ። "ይቅርታ ካንተ ነው ፤ ምህረት ካንተ ነውና ይቅር በለኝ ፣ ማረኝ ፣ በቸር እጆችህ ዳሰኝ ፣ ፈውሰኝ ፣ ነፃም አድርገኝ ። ፈልጌ አልበድልህም ፤ ደስ ብሎኝ አላጠፋም ፤ ከልቤ ክፋትን አላደርግም ፤ የማደርገውን መጥፎ ነገር ስለማወቄም እርግጠኛ አይደለሁም ፤ አውቄ እንደማልበድል ፤ ሰዎቸን መጉዳትም ሰዋዊ ባህሪዬ እንዳልሆነ አውቃለሁ ። ያንተ ልጅ ነኝና ነፍሴ የአባቷን ጠረን ዘወትር ትናፍቃለች ፣ ጆሮዬ የምህረት ቃሉን ሊመገብ ሁሌ ይጠብቃል ፤ አይኖቼ ታምራትህን ለማየት ያማትራሉ ፣ አፍንጫዬ መዓዛህን ይመኛል ፤ አፌ ተዓምራትህን ለመናገር ይጣደፋል ። በማልፈልገው መንገድ እየበደልኩህ ፣ እያሳዘንኩህ ፣ እያስከፋውህ መኖር ደክሞኛልና አሳርፈኝ ፤ አንተ ነፃ አውጣኝ ፤ ከዚህም አድነኝ ።"

አዎ! ጀግናዬ..! እንደ ባዳ ቆጥረከው ፣ ከጎንህ እንደሌለ ፣ በብዙ ማይል የተራራቃችሁ ፣ የምታደርገውን የማያይ ፣ ያለህበትን የማይረዳ ቢመስልህም እርሱ ግን እንደዛ አይነት አምላክ አይደለም ። የሚያሳርፍህ ቅርብህ ነው ፤ የሚያክምህ ከጎንህ ነው ፤ የሚያድንህ አጠገብህ ነው ፤ ነፃነትህ ሁሌም አብሮህ ያለው አምላክህ ነው ። ባትጠራውም ይሰማሃል ፤ ባታየውም ያይሃል ፤ ባትፈልገውም ይፈልግሃል ። እርሱን ፍለጋ ሩቅ የምትጓዝበት ፣ ይህን ያክል የምትደክምበት ምክንያት አይኖርህም ። ምድራዊ ሸክም ምድራዊ ነው ፤ ስቃይህ በሙሉ ጊዜያዊ ነው ፤ የምትድነውም በመልካሙ ስራህ ነው ። በመጠበቅ የማይሰለችህ ፣ በትዕግስቱ የማይተውህ አምላክ አለህ ።

አዎ! ለይቅርታው ብዛት ብለህ ልቦናህን መልስ ፤ ጥበቃውን ቆጥረህ ከክፋትህ ተመለስ ፤ ርህራሔውን ተመልክተህ እራስህን በመንፈሳዊነት አንፅ ። አንተንም ከሚያጠፋህ ፣ አምላክህንም ከሚያሳዝን ስራ ተላቀቅ ። ለእራስህ ቃል እየገባህ ማፍረሱ ይብቃህ ፤ በአምላክ ፊት መሸማቀቁን ፣ አንገትህን መድፋቱን አቁም ። እራስህን የምታድነው በመንፈሳዊነት እንደሆነ ተረዳ ። የያዘው ቢይዝህም ፤ ብዙ አጣብቂኝ ሁኔተዎች ቢፈታተኑህም ፤ እንደልብህ ለመሆን አቅም ቢያንስህም ለአምላክህ ምስጋናና ተማፅኖ የሚሆን ጊዜና ጉልበት ግን አታጣም ። በእርሱ የተባረከ አይጎድልም ፤ በእርሱ የተሻረለት ማንም አይፈርድለትም ፤ እርሱ ያከበረውን ማንም አይጥለውም ። ከአምላክህ ለመገናኘት ጊዜ አታጥፋ ፤ ፈጣሪህን ለመወዳጀት ገደብ አታብዛ ። መሃሪነቱን ካወክ በቂ ነውና ይቅርታና ምህረቱን ለመጠየቅ በፍፁም ወደኋላ አትበል ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.5K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 19:57:00 ከሆንከው በላይ ነህ!

የቀድሞው ሞነክሴ የአሁኑ ፀሃፊ ፣ ፖድካስተርና የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ ጄይ ሼቲይ (Jay Shetty) ይህን ይለናል "እንደ አማራጭ ለሚመለከትህ ሰው በፍፁም ቅድሚያ አትስጠው ።"

አዎ! ከሰዎች ጋር ባለን ግነኙነት ብዙዎቻችንን ከምናተርፈው ነገር የምናጠውና የምንከስርበት ሁኔታ ይበልጣል ። ያላንተ ፍቃድ ማንም ሊጎዳህ ቢፈልግ ሊጎዳህ አይችልም ። ለመጎዳት የምትፈቅደው ፣ ሁን ብለህ የምትጠጋው ፣ የምትቀርበው ፣ የማይገባውን ስፍራ የምትሰጠው አንተ እራስህ ነህ ። ለደቂቃ የማያስታውስህን ሰው ቀኑን ሙሉ እያሰቡ መዋል ፣ ለአፍታም ትኩረት የማይሰጥህን ሰው በሙሉ ትኩረት መከታተል ፣ አንዴም ሊያናግርህ ያልፈቀደን ሰው ደጋግመህ ደጅ መጥናት ፣ መለመን ፣ መለማመጥ ጤነኝነት ይመስልሃልን ? እኔን ለማኝ እርሱን ተለማኝ ፣ እኔን መራጭ እርሱን ተመራጭ ፣ እኔን አሳቢ እርሱን ታሳቢ ያደረገው ነገር ምንድነው ብለህ እራስህን ጠይቅ ። ምናልባትም ምላሽህ ደረጃህን እንድታውቅ ይረዳህ ይሆናል ፤ እግረመንገዱንም እራስህን ለማግኘት ይጠቅምህ ይሆናል ። ቻይ ነኝ ብለህ የማትወጣው ፉክክር ውስጥ አትግባ ፤ ጊዜ አለኝ ብለህ የማይፈልግህን በመለማመጥ ጊዜህን አታባክን ፤ ለምን አልተወደድኩም ብለህ እራስህን አትጣ ።

አዎ! ጀግናዬ..! አንተ ከሆንከው በላይ ነህ ፤ ሰዎች ከሚሰጡህ ክብር በላይ ይገባሃል ፤ ካለህበት ስፍራ የተሻለ ቦታ ትደርሳለህ ፤ ዛሬ ከናቁህ ሰዎች በላይ የሚያከብረህ ይመጣሉ ፤ ዛሬ ሊያስቡህ ደቂቃ ካጠራቸው በላይ ለደቂቃዎች በመገኘትህ ትልቅ ተፅዕና የምትፈጥርበት ወቅት ይመጣል ። ማንም እንደ አማራጭ ቢመለከትህ ፣ ወደኋላ ቢገፋህ ቀዳሚ ምርጫው የሚያደርግህም እራስህን ያስቀደምክ እለት ከተፍ ይላል ። ማንንም ልትወድ ፣ ልታፈቅር ፣ ልትወዳጅ ፣ ልታደንቅ ትችላለህ በክብርህ እንዲመጣ ፣ ማንነትህን እንዲገዳደር ፣ አንተነትህን እንዲጋፋ ግን በፍፁም እንዳትፈቅድ ። ሲቀር ለሚቀር ነገር የምትቃጠልበትና ሃፍረት የምትከናነብበት ምክንያት የለም ። ክብር ያልወደደለት በገዛ ፍቃዱ ከክብሩ ይወርድ ዘንድ የግድ ነው ። እያሳመመህ ፣ እያሰቃየህ ፣ እየገደለህ የምትሸከመው አላስፈላጊ ሸክም አይኖርም ። የሚጣለውን ለመጣል ፣ አላስፈላጊውን ለመራቅ ፣ ጎጂውን ለመነጠል ድፍረት ይኑርህ ።

አዎ! ትልቁ ሃይል በእጅህ አለ ። በእራስህ ጉዳይ ፈላጭ ቆራጩ ፣ ወሳኙ አንተ ነህ ። ክብርህ ፣ ጥንካሬህ ፣ ኩራትህ ፣ ስብዕናህ ፣ ማንነትህ አንተ ጋር ነው ። ስትፈልግ የምታነሳው ፣ ሳትፈልግ የምትጥለው እድገትና ውድቀቱ በእራስህ መልካም ፍቃድ ላይ የተመሰረተ ወሳኝ የአንተነትህ መለኪያ ነገር አለህ ። የእራስህን ክልል አብጅ ፣ ቀዩን መስመር አብጅ ፣ አልሚ መሳይ አፍራሽ ፣ ወዳጅ መሳይ ጠላት ፣ አፍቃሪ መሳይ ጎጂ እንዳይሻገረው በጥንቃቄ ጠብቀው ። ማንነትህ የፍቃድህ ነፀብራቅ እንደሆነ አስተውል ፤ የህይወት መርህህ አንተነትህንና ስብዕናህን እንደሚገነባ ተረዳ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
3.3K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 03:02:37 ህንፃው ምን ቢረዝም ምን ቢፀዳ ቤቱ
መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፓልቱ
ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድን ነው ውበቱ
በዓሉ ግርማ
625 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 00:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 20:51:14 ፈልገህ ቅረበው!

ብርቱ እጆች ይደጋገፉ ዘንድ ፣ ህልመኛ ነፍሳት ይተሳሰሩ ዘንድ ፣ ንቁ አዕምሮዎች ይግባቡ ዘንድ ፣ ጠንካራ ልቦች አብረው ይጓዙ ዘንድ ፣ አዋቂዎች እውቀትን ይመጋገቡ ዘንድ የግድ ነው ። የሚመስልህን ለማግኘት ግዴታ በአዋጅ ማስነገር ፣ ማስታወቂያ ማሰራት አይጠበቅብህም ፤ ስሜትህ በእራሱ ይጠራዋል ፤ ማንነትህ በእራሱ ያቀርበዋል ። ነገር ግን ይህ ስሜት የማይዋዥቅ ፣ ማንነትህም የማይዛባ መሆን ይኖርበታል ። አንዴ ሰው አንዴ አፈር እየሆንክ የሚጠጋህን ሰው አታገኝም ። ጓደኞችህን ተመልከት ፣ በቅርበት የምትግባባቸውን ሰዎች አጢናቸው ፣ ቀለል የሚሉህን ሰዎች አስተውላቸው ቅርበታቸው ፣ ጓደኝነታቸው ፣ ቅለታቸው ያለምክንያት ይመስልሃል ? በፍፁም! የሚያመሳስላቹና የሚያቀራርባችሁ ብዙ ነገር ይኖራል ። አብረውህ ያሉ ሰዎች አብረውህ የሆኑት ፣ የቀረቡህ ፣ የተወዳጁህ በምክንያት እንደሆነ አስተውል ፤ ከዚህም በላይ ሌሎች ተጨማሪ ሰዎች እንደሚያስፈልጉህ እወቅ ።

አዎ! ጀግናዬ...! ፈልገህ ቅረበው! ያንን ያስፈልገኛል ፣ ይረዳኛል ፣ ሃሳቤ ይገባዋል ፣ ራዕይዬን ይጋራኛል የምትለውን ሰው ፈልገህ አግኘው ። ያንን የእኔ ያልከውን ፣ ይደግፈኛል ያልከውን ፣ አገናኝ የጋራ ሃሳብ ፣ ህልም ፣ ራዕይ አለን ብለህ የምታስበውን ሰው ፈልገህ ቅረበው ፣ ተወዳጀው ፣ አብረሀው ሁን ፣ አብረህ ስራ ፣ ደግፈው ፣ ይደግፍህ። ብቻህን ጊዜ የፈጀብህ ነገር በህብረት ፣ በትብብር ፣ በአንድነት ወዲያው ይጠናቀቃል ፣ ለተሻለው አፈፃፀምና ግብ ያዘጋጅሃል ፣ ለላቀው ከፍታ ያቀርብሃል ፤ ወኔና ብርታት ይሆንሃል ። ሃሳብ እንኳን ሸክም ነው ፤ ጭንቀት በእራሱ ህመም ነው ፤ ለውጥን እየፈለጉ ሳያደርጉ መቅረትም የምኞት ስቃይ ነው ።

አዎ! ደክሞሃል ? ድካምህን የሚጋራ ብርቱ ደጋፊ ተወዳጅ ፤ ሃሳብ በዝቶብሃል ? ለሃሳብህ እውንነት ከጎንህ የሚቆመውን ሰው ቅረብ ። ስራህ ሰልችቶሃል ? በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ሰዎችን ተዋወቅ ። ብቻህን ከምትሮጥ አሯሯጭ ፈልገህ አብረሀው ሩጥ ፣ ብቻህን ከምትጀግን አንተን መሳይ ሌላ ጀግና ፈልገህ አብረሀው ጀግን ፣ ብቻህን ከምታልም ህልመኛ ፈልገህ አብረሀው በትልቁ አልም ። የተደጋገፉ እጆች ግንብ ይነቀንቃሉ ፣ የተባበረ ክንድ ጠላትን ይረታል ፤ አንድነት የእድገት መሰረት ነው ። ብቸኝነትህ ሃይልህ ነው ፤ ነገር ግን ሲደክምህ ድጋፍ ያስፈልግሃልና ከመደገፍ ወደኋላ እንዳትል ፤ ያልገባህን ጠይቅ ፤ ያልተረዳሀውን ተረዳ ፤ ያላወከውን ከማንም እንዴትም እወቅ ። ለከበደህ ነገር እጅ ከመስጠትህ በፊት ድጋፍ በመፈለግ ለማሸነፍ ሞክር ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.8K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 20:48:46 ሰበብ ባይኖርስ?

አዎ! በሔድንበት ሁሉ ድክመታችን እንዳይታወቅ ፣ ስንፍናችንን ላለማመን ፣ መጥፎ ስሜታችንን አለባብሶ ለማለፍ የማናቀርበው ምክንያት ፣ የማንደረድረው ሰበብ የለም ። ሃላፊነት መውሰድ ፣ ለእራስ ጥፋት ተጠያቂ መሆን የሚባለውን ነገር አብዝተን እንሸሸዋለን ። ተጠያቂነትን ፍራቻ ሁሌም ምክንያት የምትደረድር ከሆነ የትም እንደማትደርስ እወቅ ፤ ሰበብ እያበዛህ አንድ እርምጃ እደማትጓዝ ተገንዘብ ። የስሜቱ ባሪያና በሰበብ አስባቡ የተገዛ ሰው አንድም የእራሴ የሚለው ታማኝ ማንነት የለውም ፣ ሌላም በሰው ፊት ድፍረትና በእራስ መተማመን አይኖረውም ። በሚያሳዝን ሁኔታ የሚያቀርበው ምክንያት እንኳን ሌሎችን ይቅርና እራሱንም የሚያሳምን አይደለም ። ለገዛ እራሱ የሰጠው ግምትና የበታችነት ወደ ውድቀትና ተስፋ ቢስነት ያንደረድረዋል ። እላይ ታች ብለህ እራስህን ማዳን በሚገባህ ጊዜ ምክንያት በመደርደር የተጠመድክ እንደሆነ ከእራስህ በላይ ለእራስህ ጠላት አይኖርህም ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሰበብ ባይኖርስ ? ምክንያት መደርደር ባይቻልስ ? ለጥፋቱም ሆነ ለልማቱ ሃላፊነት አለመውሰድ ባይቻልስ ? የት በደረስክ ነበር ? የህይወትህ መልክ ፣ ገፅታው ፣ ማንነቱ ምን ይመስል ነበር ? አንተስ ምን አይነት ሰው ትሆን ነበር ? ሰበብ በእርግጥም አለ ነገር ግን በመኖሩ የሚጨምርልን ነገር ከሌለ ፣ ወደፊት ለመጓዝ ካላገዘን ፣ እንድንጠነክር ካላደረገን ፣ ካላበረታን ምንድነው ነጥቡ ? ቆዳን ማልፋት ቢያደክምም በመጨረሻ ውጤት ያመጣል ፤ ሰበብ ማብዛቱ ፣ ምክንያት መደርደሩ ፣ ሁኔታዎችን ማገለባበጡ ግን እራስን ከማታለል ፣ የእራስን ዋጋ ከማሳነስ ፣ ክብርን ዝቅ ከማድረግ ውጪ የሚያመጣልን ነገር የለም ።

አዎ! ያሰብከውን ላለማድረግህ ቆጥረህ የማትጨርሳቸው በቂ ምክንያቶች ይኖሩሃል ፤ ብታደርገውም ለማድረግህ እጅግ ብዙ በቂና ከዛ በላይ ምክንያቶች ይኖሩሃል ። ለሁለቱም ሚዛን የሚደፉ ምክንያት ቢኖርህም ሚዛኑ ግን አንተ ነህ ፤ እራስህ ላይ የምትወስነው ፣ አዋጩን የምትመርጠው ፣ ጠቃሚውን የምታደርገው አንተ ነህ ። የምክንያት ለውጥ አድርግ ፤ ላለማድረግ የምትደረድረውን ምክንያት ማድረግ በሚያስችሉህ ጠንካራ ምክንያቶች ተካቸው ፤ በእነርሱ ለውጣቸው ። ላለህበት ሁኔታ ያደረሱህ ነገሮች በተናጥል ሳይሆን በጋራ ለዚህ አብቅተውሃል ። አዎንታዊ ምክንያቶችህም ብቻቸውን ሳይሆን ከቆራጥነትህ ጋር ፣ ውሳኔህን በማካተት ፣ በህይወት አላማህ በመደገፍ ተዓምራዊውን ህይወት ወዳንተ ያመጣሉ ። ሰበቦችህን አሸጋሽግ ፤ ምክንያቶችህን አቀያይር ። አሉታዊዎቹን አስቀር ፣ በአዎንታዊዎቹ ተመራ ፤ ብርታቶችህን ምረጥ ጥንካሬህን አስቀድም ፤ ያሰብከውን ትልቅ ነገር አድርገህ ተገኝ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.7K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 13:53:09
“ፍቅር እስከ መቃብር” መጽሐፍን ወደ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ቀይሮ ለማቅረብ ኢቢሲ ከሰው መሆን ፊልም ፕሮዳክሽን ጋር የ41,427,600 ብር ውል ተፈራረመ።

ድራማው በአራት ምዕራፍ፣ በ48 ክፍሎች ፕሮዳክሽን ተሰርቶ ይቀርባል። በአማካይ 45 ደቂቃ ርዝማኔ ሲኖረው ለእያንዳንዱ የድራማ ክፍል (Episode) ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ 863 ሺህ 75 (ስምንት መቶ ስልሳ ሦስት ሺህ ሰባ አምስት) ብር ለመክፈል ስምምነት ላይ ተደርሷል።

‘ሰው መሆን ፊልም ፕሮዳክሽን’ በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ የድራማውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ማለትም (ከክፍል1-12) የተጠናቀቁ ሥራዎችን እንዲሁም በቀጣይ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ (48 ክፍሎች) አጠናቅቆ ለማስረከብ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል ።
533 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 09:45:05
እውነተኛ ፍቅር አንድ ሰሞን ላይ አላስቆም አላስቀምጥ ብሎ መልሶ የሚጠፋ ሳይሆን በእውቀት እየዳበረ እና በእርግጠኝነት እየታጀበ ወደ ሙላቱ እንደሚፈስ ወንዝ ሁለቱንም ጥንዶች ወደ አንድ ዘላቂ ቁም ነገር አያይዞ የሚነዳ የህይወት ዘመን ማሰሪያ ገመድ ነው..
በፍቅር ዋሉልኝ
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.6K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 05:42:54 #ምክረ_ሴት

1. ኳስ የማየት background ከሌለሽ አሁንም አትዪ የማታቂው ነገር ላይ እየዘላበድሽ አታሰድቢን

2. ወንድ ልጅ መከረሽ ማለት በጣም ተበላሽተሻል ማለት ነውና ተመለሺ

3. የባንክ accountsሽ ውስጥ 10ሺ እንኳን ብር ሳይኖር መኪና የሌለው ወንድ አላገባም አትበይ የምታገቢው ድህነትሽን ለመዋጋት አደለም መጀመሪያ ራስሽን ቻይ!

4. ስታወሪ በየመሀሉ ዝም በይ ንግግርሽ ይበልጥ ጥንካሬ ይኖረዋል (ንግግርሽ ያሰለቸው ሰውም ካለ በሰበቡ እረፍት ያገኛል )

5. እየዋሸሽ እንደሆነ ካወቅሽበት አትንገሪው just take a mental note ጀማሪ ውሸታም ከሆነ ደፍሮ አይንሽን አያይም ፣እጁን ይፈትላል ምናምን የለመደ ውሸታም ግን አይኑን በጨው አጥቦ እያፈጠጠብሽ ይዋሽሻል፥ የውሸታም ጥሩ የለውም ጀማሪም ሆነ ስልጡን፥ ውሸታም ውሸታም ነው ከህይወትሽ ንቀዪው (ተፀፀተው ይቅርታ ከጠየቁሽ ግን ይቅርታሽን አትንፈጊ)

6. ከጓደኞችሽ ጋር ዘና ለማለት ስትወጡ ቦታው ላይ ቀድመሽ አትድረሺ ፣ ከሁሉም ቀድመሽ ወደቤት መመለስ እንዳለብሽም አትርሺ፦ (ማንም ሰው በፈለገሽ ሰዐት ሁሉ የማትገኚ ሁኚ)

7. ለወንድ ልጅ ካንቺ ሚፈልገውን ሁሉ አትስጪው ፣ ይጠብቅ በመጠበቁ ውስጥ ላንቺ ያለው ክብር ይጨምራል (መጠበቅ የሰለቸው መሄድ ይችላል መተካት ለሚችል ነገር obsessed አትሁኚ)

8. ለሰዎች ራስሽን አታብራሪ ይልቅ ስላንቺ ለማወቅ ይጣሩ ፣ የሚታይ ስኬት ይኑርሽ(የተሸፈነ ውበት እንዳለሽ ሁሉ)
9. አብራችሁ በልታችሁ ሁሌ እሱ እንዲከፍል አትጠብቂ learn to pay bills 

10. ንፁህ ሁኚ ንፅህና ማለት ራስ የሚያሳምም deodorant ወይም ሽቶ መለቅለቅ ሳይሆን መታጠብ ነው !  it only costs you ሳሙና እና ውሀ

11. ራስሽን ውበትሽን ወይም አቋምሽን ለማሳየት ብለሽ አትገላለጪ የታየ ያልፍበታል ዛሬ ያየሽ ነገ ደግሞ አያይሽም ትዘጊዋለሽ   በዛ ላይ ፀሀይና አቧራ ከሚያጠቁርሽ ከነብነብ በይበት ትርፉ እድፍ ማብዛት ነው ( ከፊት የምታጮልቀዋ ፀጉርሽንም አስገቢያት ከኃላ ያለውም ፀጉር ያንቺ ነው ተንከባከቢው ) 

12. ልክ እንደራስሽ ሁሉ በጓደኛችሽ ስኬት ተደሰቺ (ጓደኛ መሳይ ጠላቶችሽን መልካምነትን  ታስተምሪበታለሽ )

13. አንብቢ!  ነገሮችን የማመዛዘንና ከተለያዩ ማእዘኖች አንፃር ለማየት ይረዳሻል፣ አንብበሽ ስተጨርሺ መፅሀፉ ፊት ገፅ ላይ ፊርማሽን አኑሪበት ቆንጆ ሽቶም ነስንሺበት   (የወደድሽውን መፅሀፍ ለምትወጂው ሰው አውሺ )

14. በመጨረሻም ፊትሽን ፀሀይ እንዳይጎዳው sunscreen ተቀቢ አይንሽን በ solar መነፅር ከፀሀይ ጨረር ተከላከዪው መነፅሩን አናትሽ ላይ ተሸከመሽው አትዙሪ እሺ
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.1K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 05:39:12 ሽንፈት እንዳይረታህ!

ህይወት ተገማች አይደለችምና ትናንት ሌላ ሰው ነበርክ ፣ ዛሬም እንዲሁ ሌላ ሰው ሆነሃል ፣ ለውጥህ ነገም እንዲሁ ይቀጥላል ። ቀድሞ የማይታወቅ ነገር ሁሌም አጓጉዊነቱ እየጨመረ ይሔዳል ። ነገሮች እንዳሰብከው የማይሰካኩልህ ፤ እንደጠበከው የማይሆኑልህ ለበጎ እንደሆነ አስብ ። የሚከብድህ ነገር ሁሌም ከባድ አይደለም ፤ ዛሬ ያልተቻለህ ነገር ሁሌም የማትችለው አይደለም ። በማይገመተው የህይወት ጉዞ ውስጥ የማይቀየር ነገር የለም ። ጠዓም ያለው እርምጃ ፣ ትርጉም ያለው ተግባር ፣ ሰዎችን የሚጠቅም አገልግሎት ማሸነፉ የማይቀር ጉዳይ ነው ። በየትኛውም መንገድ ብትጓዝ ካመንክበት ፣ እስከ ጥግ ከሔድክበት የመጨረሻውን ሳቅ ይምትስቀው ፣ የድልን ፅዋ የምትጎነጨው አንተ ነህ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሽንፈት እንዳይረታህ ፤ ውድቀት እንዳይቆጣጠርህ ፤ የበታችነት እንዳይገዛህ ፤ በምናለብኝነት እንዳትሸነፍ ፤ በማቆም ጉዞህን እንዳትገታ ፤ አቋርጠህ ከሜዳው እንዳትወጣ ። የጀመርከው ለመጨረስ እንደሆነ አስታውስ ፤ የምትጓዘው እስከመዳረሻህ እንደሆነ አስተውል ፤ የምታቆመው ስትፈፅመው ብቻ እንደሆነ ለእራስህ ቃል ግባ ። ቀላልና ከባድ ፣ አስጨናቂና አዝናኝ ፣ አስደሳችና አሳዛኝ ገጠመኞች የህይወትህ አካላት ናቸው ። መርጠህ የምትተዋወቸው ወይም ነጥለህ የምትይዛቸው አይደሉም ። በምንም መንገድ ዘወትር እያሸነፍክ አትቀጥልም ፤ እንዴትም ያለውጣውረድ ተራራውን አትወጣውም ። እጅግ የገዘፉ ፣ ለመግፋት የሚያዳግቱ ፣ አብዝተው የሚያስጨንቁ ፣ አጣብቂኝ ውስጥ የሚከቱ አያሌ ክስተቶች በየመንገዱ ይገጥሙህ ዘንድ የግድ ነው ።

አዎ! የሚጓዝ ስው ይደናቀፋል ፤ ግፋ ሲልም ይወድቃል ፤ ይጋጋጣል ፤ ይጎዳል ፤ ይታመማል ። ነገር ግን በእንቅፋቱ ምክንያት ከመንገዱ አይገታም ፤ በውድቀቱ ምክንያት ወደኋላ አይመለስም ፤ በጉዳቱ ምክንያት ሊሔድ ካሰበበት ቦታ አይቀርም ። ምንም ያጋጥምህ በማቆም የሚመጣው ሽንፈት ፣ በማቋረጥ የሚያገኝህ ተስፋ መቁረጥ እንዳይቆጣጠርህ እራስህን አበርታ ። አንድ ሁለቴ ልትሸነፍ ትችላለህ ፣ ወደኋላም ልትመለከት ትችላለህ ተስፋ ቆርጠህ ያቆምክበት ወቅት ግን የመጨረሻው አንገት አስደፊ የስቃይ ሽንፈትህ ይሆንብሃል ። እያሸማቀቀ የሚያሳንስህ ፣ ከአቅምህ በታች የሚያኖርህ ፣ የኋሊት ጉዞህን የሚያፋጥን ፣ በጉድለቶች የሚስጨንቅህ አስከፊ ጠላት ይሆንብሃል ። ለሽንፈት እጀ እንዳትሰጥ ፤ በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ፤ ድሉ ያንተ እንጂ የሽንፈትህ ፣ የተስፋ መቁረጥህ ፣ የውድቀትህና የበታችነትህ አይደለም ። ያቆምክ እለት ሽንፈትህ ይጀምራልና ምንም እንኳን ቢከብድህ መቼም ጥረትህን እንዳታቆም ፤ እንዳታቋርጥ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.7K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 05:37:04 አይምሰልህ!

አዎ! አይምሰልህ! ከኖርከው በላይ የምትኖር ፤ ካላፍከው በላይ የምታልፍ ፤ ካገኘሀው በላይ የምታገኝ ፣ ከተደሰትክበት በላይ የምትደሰት እንዳይመስልህ ። ረጅም ጊዜ የቀረህ ቢመስልህም መቼ ይህችን ምድር እንደምትለይ ግን አታውቅም ፤ ከዛሬ የተሻለ ጠንካራና ብርቱ እንደምትሆን ብታስብም ነገ ምን እንደሚፈጠር አታውቅም ። ህይወት በነዳችህ ስትነዳ እንደ ፈረሱና እንደ ኮርቻው ተስማምታችሁ አብራችሁ መጓዝ ስትችሉ አንተ ግን የፈለካት ህይወት በዚህ ፣ የምትጓዝበት መንገድ በዛ ሆኖብህ ትገኛለህ ። አትሸወድ ፤ ምንም ጊዜ እንዳልቀረህ እያሰብክ መኖርን ጀምር ። መልካም ሰው ሁን ፤ ቅን ደግ አድራጊ አላሚ ህልሙን ኗሯ ፤ ለሰው ተራፊ ፤ የብዙዎችን ህይወት የምታቀል ጠንካራ ሰው ሁን ።

አዎ! ጀግናዬ...! በእርግጥ ብዙ ሸክም አለብህ ፤ ጫናዎች በየጊዜው ይደራረቡብሃል ፤ ከየአቅጣጫው ፈተናዎች ይላኩብሃል ነገር ግን እነርሱም የህይወት አንድ አካላ ናቸው ። በህይወት እስካለህ ውጣውረድ አልባ መንገድ ልትጓዝ አትችልም ። ስቃይና መከራው የግድ ነው ። ዋጋ መክፈልህ የማይቀር ነው ። ለምንያክል ጊዜ ወደማለቅ የሚሔደውን ጊዜ እንደጭማሬና ብዙ እንደሚቀረን እንደምናስብ ለብዙዎቻችን ግልፅ አይደለም ። አዲስ ንጋት ስንመለከት ከመኖራችን ላይ አንዲት ቀን ተቀናሽ ትሆናለች ነገር ግን ስንቶቻቸን እንሆን የምትቀነሰው ቀን ሌላም ተጭማሪ እንደምታመጣልን በማሰብ ለመኖር ረጅም ጊዜ እንደቀረን ፣ ያሰብነውን ለማድረግ ብዙ ነገዎች እንደሚጠብቁን ፣ ራዕያችንን ከግብ ለማድረስ አቅም እንደሚጨመርልን የምናስብ ? ወደድንም ጠላንም ጉዟችን ወደ ህይወት ፍፃሜያችን ነው ፤ አመንም አላመንም ከዛሬ ውጪ ውድ ስጦታ የለንም ፤ ፈለግንም አልፈለግንም ወደፊታችን ሚስጥር ነው ።

አዎ! ከቁጪት የምትድንበት ፣ እስራትህን የምትፈታበት ፣ ነፃ የምትወጣበት ፣ ወደፊት የምትራመድበት መንገድ አለ። እርሱም ዛሬን መኖር ነው ። ጊዜያት ከነጎዱ ፣ እድሜ ከሔደ ፣ ድካም ሲመጣ አንድ የሚታወስህ ፣ የሚቆጭህና የሚያንገበግብህ ነገር ቢኖር ዝምታህ ነው ፤ ማድረግ የነበረብህን አለማድረግህ ነው ፤ በምትፈልገው ስፍራ አለመገኘትህ ነው ፤ ያሰኘህን ሞክረህ አለማየትህ ነው ። ሃገር የምትጠፋው በአመፀኛው ብዛት ሳይሆን በዝምተኛው ፣ በምን አገባኝ ባዩና በቸልተኛው ብዛት እንደሆነ አስታውስ ። አብዛኛው ሰው ጥፋትን ቢቃወም ፣ ብልሹ አሰራርን በትክክል ቢሟገት ፣ ለመብቱ ጠበቃ ቢቆም አሰራሩን አስተካክሎ ሀገሩን ወደ ተሻለ ስፍራ የማያሸጋግርበት ምክንያት የለም ። ትርጉም አልባ ዝምታ ፣ ጊዜውን ያልዋጀ ግዴለሽነት ፣ ጉብዝናን የገደለ ስንፍናና ግብዝነት የመጨረሻው ዋጋ እጅግ ከባድ ነው ። ረጅም ያልከው ጊዜ ወዲያው የሚቋጭ ነው ፤ የማይጨልም የመሰለህ ቀን አመሻሽ ላይ የሚደረሰው በጊዜ ነው ። ለግራመጋባት ፣ ለቸልተኝነት ፣ ለስንፍና ፣ ለሰበበኝነት ጊዜ እንደሌለህ አስታውስ ። ረጅም የመሰለህ ጊዜ ሳያጥር ቀድመሀው ተገኝ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.7K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ