Get Mystery Box with random crypto!

ከሆንከው በላይ ነህ! የቀድሞው ሞነክሴ የአሁኑ ፀሃፊ ፣ ፖድካስተርና የህይወት ክህሎት አሰል | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ከሆንከው በላይ ነህ!

የቀድሞው ሞነክሴ የአሁኑ ፀሃፊ ፣ ፖድካስተርና የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ ጄይ ሼቲይ (Jay Shetty) ይህን ይለናል "እንደ አማራጭ ለሚመለከትህ ሰው በፍፁም ቅድሚያ አትስጠው ።"

አዎ! ከሰዎች ጋር ባለን ግነኙነት ብዙዎቻችንን ከምናተርፈው ነገር የምናጠውና የምንከስርበት ሁኔታ ይበልጣል ። ያላንተ ፍቃድ ማንም ሊጎዳህ ቢፈልግ ሊጎዳህ አይችልም ። ለመጎዳት የምትፈቅደው ፣ ሁን ብለህ የምትጠጋው ፣ የምትቀርበው ፣ የማይገባውን ስፍራ የምትሰጠው አንተ እራስህ ነህ ። ለደቂቃ የማያስታውስህን ሰው ቀኑን ሙሉ እያሰቡ መዋል ፣ ለአፍታም ትኩረት የማይሰጥህን ሰው በሙሉ ትኩረት መከታተል ፣ አንዴም ሊያናግርህ ያልፈቀደን ሰው ደጋግመህ ደጅ መጥናት ፣ መለመን ፣ መለማመጥ ጤነኝነት ይመስልሃልን ? እኔን ለማኝ እርሱን ተለማኝ ፣ እኔን መራጭ እርሱን ተመራጭ ፣ እኔን አሳቢ እርሱን ታሳቢ ያደረገው ነገር ምንድነው ብለህ እራስህን ጠይቅ ። ምናልባትም ምላሽህ ደረጃህን እንድታውቅ ይረዳህ ይሆናል ፤ እግረመንገዱንም እራስህን ለማግኘት ይጠቅምህ ይሆናል ። ቻይ ነኝ ብለህ የማትወጣው ፉክክር ውስጥ አትግባ ፤ ጊዜ አለኝ ብለህ የማይፈልግህን በመለማመጥ ጊዜህን አታባክን ፤ ለምን አልተወደድኩም ብለህ እራስህን አትጣ ።

አዎ! ጀግናዬ..! አንተ ከሆንከው በላይ ነህ ፤ ሰዎች ከሚሰጡህ ክብር በላይ ይገባሃል ፤ ካለህበት ስፍራ የተሻለ ቦታ ትደርሳለህ ፤ ዛሬ ከናቁህ ሰዎች በላይ የሚያከብረህ ይመጣሉ ፤ ዛሬ ሊያስቡህ ደቂቃ ካጠራቸው በላይ ለደቂቃዎች በመገኘትህ ትልቅ ተፅዕና የምትፈጥርበት ወቅት ይመጣል ። ማንም እንደ አማራጭ ቢመለከትህ ፣ ወደኋላ ቢገፋህ ቀዳሚ ምርጫው የሚያደርግህም እራስህን ያስቀደምክ እለት ከተፍ ይላል ። ማንንም ልትወድ ፣ ልታፈቅር ፣ ልትወዳጅ ፣ ልታደንቅ ትችላለህ በክብርህ እንዲመጣ ፣ ማንነትህን እንዲገዳደር ፣ አንተነትህን እንዲጋፋ ግን በፍፁም እንዳትፈቅድ ። ሲቀር ለሚቀር ነገር የምትቃጠልበትና ሃፍረት የምትከናነብበት ምክንያት የለም ። ክብር ያልወደደለት በገዛ ፍቃዱ ከክብሩ ይወርድ ዘንድ የግድ ነው ። እያሳመመህ ፣ እያሰቃየህ ፣ እየገደለህ የምትሸከመው አላስፈላጊ ሸክም አይኖርም ። የሚጣለውን ለመጣል ፣ አላስፈላጊውን ለመራቅ ፣ ጎጂውን ለመነጠል ድፍረት ይኑርህ ።

አዎ! ትልቁ ሃይል በእጅህ አለ ። በእራስህ ጉዳይ ፈላጭ ቆራጩ ፣ ወሳኙ አንተ ነህ ። ክብርህ ፣ ጥንካሬህ ፣ ኩራትህ ፣ ስብዕናህ ፣ ማንነትህ አንተ ጋር ነው ። ስትፈልግ የምታነሳው ፣ ሳትፈልግ የምትጥለው እድገትና ውድቀቱ በእራስህ መልካም ፍቃድ ላይ የተመሰረተ ወሳኝ የአንተነትህ መለኪያ ነገር አለህ ። የእራስህን ክልል አብጅ ፣ ቀዩን መስመር አብጅ ፣ አልሚ መሳይ አፍራሽ ፣ ወዳጅ መሳይ ጠላት ፣ አፍቃሪ መሳይ ጎጂ እንዳይሻገረው በጥንቃቄ ጠብቀው ። ማንነትህ የፍቃድህ ነፀብራቅ እንደሆነ አስተውል ፤ የህይወት መርህህ አንተነትህንና ስብዕናህን እንደሚገነባ ተረዳ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q