Get Mystery Box with random crypto!

ሽንፈት እንዳይረታህ! ህይወት ተገማች አይደለችምና ትናንት ሌላ ሰው ነበርክ ፣ ዛሬም እንዲሁ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ሽንፈት እንዳይረታህ!

ህይወት ተገማች አይደለችምና ትናንት ሌላ ሰው ነበርክ ፣ ዛሬም እንዲሁ ሌላ ሰው ሆነሃል ፣ ለውጥህ ነገም እንዲሁ ይቀጥላል ። ቀድሞ የማይታወቅ ነገር ሁሌም አጓጉዊነቱ እየጨመረ ይሔዳል ። ነገሮች እንዳሰብከው የማይሰካኩልህ ፤ እንደጠበከው የማይሆኑልህ ለበጎ እንደሆነ አስብ ። የሚከብድህ ነገር ሁሌም ከባድ አይደለም ፤ ዛሬ ያልተቻለህ ነገር ሁሌም የማትችለው አይደለም ። በማይገመተው የህይወት ጉዞ ውስጥ የማይቀየር ነገር የለም ። ጠዓም ያለው እርምጃ ፣ ትርጉም ያለው ተግባር ፣ ሰዎችን የሚጠቅም አገልግሎት ማሸነፉ የማይቀር ጉዳይ ነው ። በየትኛውም መንገድ ብትጓዝ ካመንክበት ፣ እስከ ጥግ ከሔድክበት የመጨረሻውን ሳቅ ይምትስቀው ፣ የድልን ፅዋ የምትጎነጨው አንተ ነህ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሽንፈት እንዳይረታህ ፤ ውድቀት እንዳይቆጣጠርህ ፤ የበታችነት እንዳይገዛህ ፤ በምናለብኝነት እንዳትሸነፍ ፤ በማቆም ጉዞህን እንዳትገታ ፤ አቋርጠህ ከሜዳው እንዳትወጣ ። የጀመርከው ለመጨረስ እንደሆነ አስታውስ ፤ የምትጓዘው እስከመዳረሻህ እንደሆነ አስተውል ፤ የምታቆመው ስትፈፅመው ብቻ እንደሆነ ለእራስህ ቃል ግባ ። ቀላልና ከባድ ፣ አስጨናቂና አዝናኝ ፣ አስደሳችና አሳዛኝ ገጠመኞች የህይወትህ አካላት ናቸው ። መርጠህ የምትተዋወቸው ወይም ነጥለህ የምትይዛቸው አይደሉም ። በምንም መንገድ ዘወትር እያሸነፍክ አትቀጥልም ፤ እንዴትም ያለውጣውረድ ተራራውን አትወጣውም ። እጅግ የገዘፉ ፣ ለመግፋት የሚያዳግቱ ፣ አብዝተው የሚያስጨንቁ ፣ አጣብቂኝ ውስጥ የሚከቱ አያሌ ክስተቶች በየመንገዱ ይገጥሙህ ዘንድ የግድ ነው ።

አዎ! የሚጓዝ ስው ይደናቀፋል ፤ ግፋ ሲልም ይወድቃል ፤ ይጋጋጣል ፤ ይጎዳል ፤ ይታመማል ። ነገር ግን በእንቅፋቱ ምክንያት ከመንገዱ አይገታም ፤ በውድቀቱ ምክንያት ወደኋላ አይመለስም ፤ በጉዳቱ ምክንያት ሊሔድ ካሰበበት ቦታ አይቀርም ። ምንም ያጋጥምህ በማቆም የሚመጣው ሽንፈት ፣ በማቋረጥ የሚያገኝህ ተስፋ መቁረጥ እንዳይቆጣጠርህ እራስህን አበርታ ። አንድ ሁለቴ ልትሸነፍ ትችላለህ ፣ ወደኋላም ልትመለከት ትችላለህ ተስፋ ቆርጠህ ያቆምክበት ወቅት ግን የመጨረሻው አንገት አስደፊ የስቃይ ሽንፈትህ ይሆንብሃል ። እያሸማቀቀ የሚያሳንስህ ፣ ከአቅምህ በታች የሚያኖርህ ፣ የኋሊት ጉዞህን የሚያፋጥን ፣ በጉድለቶች የሚስጨንቅህ አስከፊ ጠላት ይሆንብሃል ። ለሽንፈት እጀ እንዳትሰጥ ፤ በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ፤ ድሉ ያንተ እንጂ የሽንፈትህ ፣ የተስፋ መቁረጥህ ፣ የውድቀትህና የበታችነትህ አይደለም ። ያቆምክ እለት ሽንፈትህ ይጀምራልና ምንም እንኳን ቢከብድህ መቼም ጥረትህን እንዳታቆም ፤ እንዳታቋርጥ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q