Health. Com/ጤናን በቴሌግራም

የቴሌግራም ቻናል አርማ eclink — Health. Com/ጤናን በቴሌግራም H
የቴሌግራም ቻናል አርማ eclink — Health. Com/ጤናን በቴሌግራም
የሰርጥ አድራሻ: @eclink
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 324
የሰርጥ መግለጫ

👉 ይህ የTelegram channel ስለ ጤናዎ በጥቂቱ ግንዛቤ ያስጨብጣል።
👉 ማንኛውንም ጤና ነክ ጉዳይ እናማክራለን

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-22 18:25:14
#update

በትላንትናው እለት እስራኤል እና ስዊዘርላንድ የመጀመሪያዉን የጦጣ ፈንጣጣ (Monkeypox) በሽታ ሪፖርት አድርገዋል።

ባለፉት ሳምንታት በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይ፣ በጀርመን፣ በቤልጂየም፣ በጣሊያን፣ በፖርቹጋል፣ በስፔን እና በስዊድን እንዲሁም በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በአውስትራሊያ ከ100 በላይ የጦጣ ፈንጣጣ በሽታ(Monkeypox) መገኘቱን ተከትሎ ቫይረሱ ሊስፋፋ ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።

ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ቫይረሱ በሌለባቸው አገሮች ውስጥ ያለው ወረርሽኝ ያልተለመደ እንዲሁም የአሁኑ የጦጣ ፈንጣጣ(Monkeypox) ዝርያ የሚለየዉ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች ሊሆን እንደሚችል እየተገለፀ ይገኛል።

የዓለም ጤና ድርጅት በበሽታው ከተጠቁ ሀገራት እና ከሌሎች ጋር በመሆን የበሽታ ክትትልን በማስፋት የተጠቁ ሰዎችን ለማግኘት እና ለመደገፍ እንዲሁም በሽታውን እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል መመሪያ ለመስጠት እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።

የዝንጀሮ በሽታ ከኮቪድ-19 በተለየ ሁኔታ ይተላለፋል። ሆኖም ግን በንክኪ ከሰዉ ወደ ሰዉ ሊተላለፍ ስለሚችል ጥንቃቄ ይሻል ።

እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ገለፃ በሚቀጥሉት ሳምንታት በርካታ የአዉሮፓ ሀገራት የጦጣ ፈንጣጣ በሽታ ሪፖርት ሊኖር እንደሚችል ገልጿል።
#Dr. Haileleul
174 viewsedited  15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 19:19:19
ውድ የሀኪሙ ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችን ለመደሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።


✞✞✞ መልካም የትንሣኤ በዓል ✞✞✞
236 views16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 13:10:46
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!!
መልካም በዓል!!
215 views10:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 23:21:07 ሾተላይ ለምን ይከሰታል?

የሰው ልጅ ከወላጆቹ ዘረመል ተነስቶ ከ4 የደም አይነቶች ውስጥ አንዱን ሊይዝ ይችላል። እነኝህም
1. “A”
2. “B”
3. “AB”
4. “O” ተብለው ይጠራሉ።

በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ህዋሶች(RBCs) የላይኛው ሽፋናቸው ላይ Rh የተባለ ፕሮቲን (protein) ካላቸው ሴቲቱ Rh positive ናት ማለት ሲሆን እነኚህ ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ Rh negative ናት ማለት ነው።

ለምሳሌ:- ሴቲቱ የደም አይነቷ B ቢሆንና ቀይ የደም ሴሎቿ ላይ Rh ፕሮቲን ካለ B Positive ናት ማለት ነው፤ እነኚህ Rh ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ B Negative ናት ይባላል።

አንዲት ሴት ሾተላይ የሚባለው ችግር ሊከሰትባት የሚችለው እሷ Rh negative ሆና በተለያዩ አጋጣሚዎች Rh positive የሆነ ደም ወደሰውነቷ ሲገባ ሰውነቷ እነኚህን Rh positive የደም አይነቶች የሚያጠፉ(የሚገሉ) ንጥረ ነገሮች (Antibodies) ሲያመነጭ (ሲያመርት) ነው። እነኚህም እስከ እድሜልክ በሰውነቷ ይቆያሉ።

እነኚህ የተመረቱት ተከላካይ ንጥረ ነገሮች(Antibodies) የመጀመሪያው ልጅ ላይ ምንም ተፅዓኖ ሳይኖራቸው ልጁ በሰላም ሊወለድ ይችላል ነገር ግን የሁለተኛው ፅንስ የደም አይነቱ Rh positive ከሆነ ወደ ፅንሱ በማለፍ የፅንሱን Rh positive የቀይ የደም ህዋሶች ያጠቃሉ ማለት ነው፤ ይህም ፅንሱን ለተለያየ አደጋዎች ሊያጋልጠው ይችላል።

ይህም ችግር ፅንሱ ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን ሊያመጣ ይችላል ፤ እነኚህም

በፅንሱ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ውሀ መቋጠር - Fetal hydrops
በተደጋጋሚ የፅንስ መውረድ - Miscarriage
የፅንሱ የደም ማነስ - Fetal anemia
ፅንሱ በማህፀን ውስጥ እንዳለ ጊዜው ሳይደርስ ህይወቱ ማለፍ
ህፃኑ ከተወለደ በውሃላ ቆዳው ቢጫ መሆን እና የጨረር ህክምና ማስፈለግ(phototherapy)
በከፍተኛ ደም ማነስ ምክንያት ደም ለመውሰድ መጋለጥ

ሾተላይ እንዴት ይታከማል?

Rh negative የሆነችው እናት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ነገሮች ከገጠሟት
ባለቤቷ Rh positive ከሆነ
ውርጃ ካጋጠማት
ከማህፀን ውጭ እርግዝና ካጋጠማት
ከእንግዴ ልጅ ላይ የሚነሳ እጢ(Gestation trophoblastic disease) ካጋጠማት
በእርግዝና ወቅት አደጋ ከደረሰባት፤
በክትትል ወቅት ከእንግዴ ልጅ ወይም ከሽርት ዉሃ በመሳሪያ ናሙና ከተወሰደ

Anti D የተባለ ኢሚውኖግሎቡሊን (immunoglobulin) መድሀኒት በመውሰድ ሾተላይን መከላከል ይቻላል።

በእርግዝና ጊዜ Anti D የተባለውን መድሃኒትን በ 7 ወር(28 ሳምንት) ላይ እና ህፃኑ በተወለደ ቢቻል እስከ 72 ሰዓት ውስጥ በመስጠት የሾተላይ በሽታን መከላከል ይቻላል።

Rh negative የሆነች እናት(ባል Rh positive) የእርግዝና ክትትሏ ከሌሎች እናቶች ለየት ያለ እና የሚሰጣትም ቀጠሮ በዛ ያለ ይሆናል።

ይህም በልጇ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉትን የሰውነት ውሀ መቋጠር(መጠራቀም) እና የፅንሱ ደም ማነስ ካለ ቀድሞ በማወቅ ህክምናውን በቶሎ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ እዛው ማህፀን ውስጥ እንዳለ ደም በመለገስ እና ወቶ ለመኖር ብቁ በሆነበት ጊዜ ቀድሞ እንዲወለድ በማድረግ ተጨማሪ የሆኑ የህክምና እርዳታዎች እንዲደረግለት ማድረግ ይቻላል።

መልካም ምሽት
176 views20:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 21:54:07 ፎሮፎር |Seborrheic dermatitis

ፎሮፎር ምንድነው?

ፎሮፎር እየተመላለሰ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ከሰው ወደ ሰው የማይተላለፍ የቆዳ ህመም አይነት ነው። ፎሮፎር በባህሪው ጠንካራ ያልሆነ ብዙም ምልክት የሌለው እና ትንንሽ ብናኞች ያሉት ሊሆን ይችላል፤ይህ የተለመደው አይነት ፎሮፎር ሲሆን ዳንድረፍ (dandruff) በመባል ይታወቃል።

በተቃራኒው ደግሞ ጠንካራ የሚባለው የፎረፎር አይነት አብዛኛውን የራስ ቆዳችንን እንዲሁም ሌሎች የአካል ክፍሎቻችን ላይ ጭምር ሊከሰት ይችላል፤ ቅርፊቶቹም ወፍራም እና ከራስ ቆዳችን ጋር የተጣበቁ ሊሆኑ ይችላሉ

ፎሮፎር ምን አይነት ሰዎች ላይ ይከሰታል?

- ከሁለት ሳምንት እስከ አንድ አመት ባሉ ህጻናት እና ከጉርምስና እድሜ በላይ በሆኑ ግለሰቦች ላይ ይከሰታል
- አብዛኞቹ ፎሮፎር የሚኖርባቸው ግለሰቦች ሌላ ተጓዳኝ ህመም አይኖራቸውም አንዳንድ ጊዜ ግን ከHIV ፣ Parkinson ፣ የሚጥል ህመም (Epilepsy) ፣ ጭንቀት ገር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል

ፎሮፎር መንስኤው ምንድነው?

-የፎሮፎር መንስኤ በትክክል ይሄ ነው ተብሎ መናገር ባይቻልም ከቆዳችን ጋር ተስማምተው በሚኖሩ (normal flora) የፈንገስ አይነት (Malassezia) ምክንያት ይከሰታል ተብሎ ይታሰባል

-ፎሮፎር ወዝ አመንጪ እጢዎች (Sebaceous glands) ተከማችተው በሚገኙበት የአካል ክፍሎቻችን (የራስ ቆዳ ፣ ፊት፣ ደረት አካባቢ፣ የላይኛው የጀርባችን ክፍል ፣ የውጭኛው የጆሮ ክፍል ፣ ብብት ፣ ጡት ስር ፣ በላይኛው የጭን ክፍል እና ብልት መሀከል በሚገኘው ቦታ) ላይ ይከሰታል

ፎሮፎር እንዴት ይታከማል ?

- መድሀኒትነት ያላቸው መታጠቢያ ሻምፖዎችን (ketoconazole 2%, Selenium sulfied, Ciclopirox , Zinc pyrithione) በመጠቀም ፎሮፎርን መቆጣጠር ይቻላል።
- ሻምፖውን ተቀብተን ከ5-10 ደቂቃ አቆይተን መታጠብ ይህንንም በሳምንት ከ 2-3 ጊዜ መደጋገም ያስፈልጋል
- ከዚህ በተጨማሪ የማሳከክ ስሜት ካለው፣ጠንካራ የሚባለው የፎሮፎር አይነት ከሆነ፣ከራስ ቆዳችን ውጪ ከተከሰተ፣ተጓዳኝ ህመሞች ካሉ እንዲሁም ህጻናት ላይ ከተከሰተ የቆዳ ሐኪም በሚያዘው መሰረት ተጨማሪ መድሀኒቶች ያስፈልጋሉ።

ፎሮፎር ለምን ይመላለሳል?

መንስኤው በትክክል ስለማይታወቅ እና ምክንያት ነው ተብሎ የሚታሰበው የፈንገስ አይነት ከቆዳችን ጋር ተስማምቶ የሚኖር በመሆኑ ፎሮፎርን በህክምና ማዳን አይቻልም(not curable) ለዚህም ነው የሚመላለሰው ፤ ነገር ግን ምልክቶቹን መቆጣጠር እና የሚመላለስበትን የጊዜ ፍጥነት መቀነስ ይቻላል

ፎሮፎር እንዳይመላለስብን ምን እናድርግ?

ከላይ በተጠቀሰው መሠረት ምልክቶቹ እስኪጠፉ በሻምፖ መታጠብ ያስፈልጋል(የቆዳ ሐኪሙ ተጨማሪ መድሀኒቶችን ሊያዝ ይችላል)፤ ምልክቶቹ ከጠፉ በኋላ ሻምፖውን በሳምንት አንድ ጊዜ ወይም በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ መጠቀም ፎሮፎር እንዳይመላለስ ይረዳል

ፎሮፎር ፀጉር እንዲነቃቀል ያደርጋል?

በፎሮፎር ምክንያት የፀጉር መነቃቀል የተለመደ አይደለም ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የማሳከክ ስሜት ካለ ጊዜያዊ የሆነና ተመልሶ የሚተካ የፀጉር መነቃቀል ሊያስከትል ይችላል

በመጨረሻም የቆዳ ሐኪም ሳያማክሩ መድሀኒቶችን ባለመጠቀም ቆዳዎን ከተጨማሪ ጉዳት ይጠብቁ!!

ዶ/ር ዮሐንስ ታደሰ ፤ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት

via: Hakim
184 views18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 16:16:43 ሪማቶይድ አንጓ ብግነት (rheumatoid arthritis)

ሪማቶይድ አንጓ ብግነት የሰውነታችን በሽታ የመከላከል ህዋሶች በራሳቸው ላይ በሚያደርሱት ጉዳት የሚፈጠርና በመላው አካል የሚሰራጭ የብግነት በሽታ ሲሆን መገለጫውም በአንድ ጎን የሚከሰት የእጅና የእግር አንጓ ብግነት ነው ቀስ በቀስም አንጓዎችን ከጥቅም ውጪ የሚያደርግ በሽታ ነው።

ከመገጣጠሚያ በተጨማሪ ሳንባን ፣ደምን፣ ቆዳንና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን የሚያጠቃ ነው። በአብዛኛው ሴቶችን የሚያጠቃ ሲሆን በየትኛውም የዕድሜ ክልል የሚፈጠር ነው።

የሚያሳየው ምልክቶች
ከአምስት በላይ በአንድ ጎን ያሉ አንጓዎች ህመም
የአንጓ እብጠት
ጠዋት ሲነሱ ሰውነትን ማጠፍ አለመቻል
የመገጣጠሚያ እንቅስቃሴ መቀነስ
የድካም ስሜት
አጠቃላይ የጡንቻ ህመም
የክብደት መቀነስ

ከመገጣጠሚያ ውጪ ሲከሰት

ሳል ፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የደረት ህመም
የአይን እንባ መድረቅ፣ የዓይን ህመምና መቅላት
ቆዳ ላይ እብጠት፣ መጥቆርና መቅላት
የእግርና እጅ መደንዘዝ

የሚታዩ ምልክቶች

እብጠት
ሲነካ ምንም
የመገጣጠሚያ ጉዳት

የሚሰጡ ምርመራዎች

ምርመራው በአብዛኛው ከታካሚው በሚወሰደው ተረክ እና ሀኪሙ በሚያየው ምልክቶች ይለያል በተለይ ከሌሎች የአንጓ ብግነት የሚለየው የጣቶቻችን የመጨረሻውን አንጓ ባለማጥቃቱ ነው።
የላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ (rheumatoid factor, anti -CCP , ESR/CRP, CBC)
ራጅ ምርመራ

የሚሰጡ መድኃኒቶች

የህመም ማስታገሻ
የሪማቶይድ መድኃኒቶች (methotrexate, chloroquine phosphate, steroid) ፈጽሞ ያለሀኪም ትዕዛዝ መወሰድ የለባቸሁም ምክንያቱም የጎንዮሽ ጉዳታቸው የከፋ ስለሆነ ከዛም ባሻገር ክትትል በየጊዜው መደረግ አለበት።

ሪማቶይድ አንጓ ብግነት ያለበት ሰው ምን መመገብ የለበትም
አልኮል መጠጣት የለበትም
ቀይ ስጋ
ቅባት የበዛበት ምግብ
ለስላሳ
የእንስሳት ተዋጽኦ ( ወተት ፣ እርጎ ፣አይብ)
ጨው የበዛበት ምግብ
ስንዴ ገብስ እና
በፋብሪካ የተቀናበረ ምግብ መውሰድ የለበትም።

Dr. Mitiku
152 views13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-14 19:37:11 የማስታወስ ችሎታችንን ከፍ ሊያደርጉልን የሚችሉ የምግብ አይነቶች
------------
1. አሳ፦ አሳ በውስጥ ለአእምሮ ጤና ጠቃሚ የሆነውን ኦሜጋ 3 /omega 3/ እዛይት በመያዙ ለአእምሮ ጤና በተለይ ደሞ ለልጆች አእምሮ እድገት ጠቃሚ ነው። እንዲሁም በአሳ ውስጥ የሚገኘው ኦሜጋ 3 የአእምሯችንን ሴሎች ከጉዳት ይከላከላል።

ስለዚህም አሳን አዘውትረን በመመገብ የአእምሯችንን ጤንነት በመጠበቅ የማስታወስ ችሎታችን ከፍ እንዲል ያደርጋል።

2. ለውዝ፦ ለውዝ ለአእምሯችን ጤንነት ጠቃሚ በሆኑ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ በመሆኑ የማስታወስ ችሎታችንን ከፍ ሊያደረጉልን ይችላሉ ከሚባሉ የምግብ አይነቶች ይመደባል።

በተጨማሪም ለውዝ በውስጡ ለአእምሮ ነርቭ ጤንነት ጠቃሚ የሚባሉትን እንደ ቪታሚን ሲ እና ቪታሚን B6 አይነት ንጥረ ነገሮች የበለጸገ በመሆኑም የማሳታወስ ችሎታችንን ከፍ ያደርጋል ተብሏል።

3. አቮካዶ፦ በአቮካዶ ውስጥ የሚገኙት የፋቲ አሲድ ቅባቶች አእምሯችን ንቁ እና ጤነኛ እንሆን በማድረግ ከፍ ያለ የማስታወስ ችሎታ እንዲኖረን ይረዳሉ።

4. ቀይ ሽንኩርት፦ ሻል ያለ የማስታወስ ችሎታ እንዲኖረን ከፈለግን በምጋባችን ውስጥ በርከት ያለ ሽንኩትር ጨምሮ መመገብ ይመከራል ምክንያቱ ደግሞ ሽንኩርት በውስጥ በያዘው አንቲኦክሲዳንት ንጥረነገር አእምሯችንን ከጉዳት ስለሚከላከል ነው።

5. አፕል፦ አፕል ወይም ፖም በውስጡ ኩዌርስቲን የተባለ አንቲ ኦክሲዳንት ንጥረ ነገር የበለጸገ በመሆኑ አእምሮን ከጉዳት በመከላከል የማስታወስ ችሎታችን እንዲጨምር ያደርጋል።

6. ቀይ ስር፦ ቀይ ስር በአይረን የበለጸገ በመሆኑ ደማችን በቂ ሄሞግሎቢን እንዲያገኝ በማድረግ አእምሯችን በቂ ኦክሲጅን አግኝቶ ጤነኛ እንዲሆን በማደረግ ለማስታወስ ችሎታችን መጨመር አይነተኛ ሚና አለው።

7. ማር፦ ማር በተፈጠሮ ሀይል ሰጪ ምግብ በመሆኑ አዘውትረን የምንወስድ ከሆነ የአእምሯችንን የማሳታወስ አቅም ከፍ እንዲል ያግዛል።

8. ውሃ፦ ውሃን አዘውትሮ መጠጣት ለአእምሯችን ጤንነት እና የማስታወስ ችሎታን ከፍ በማድረግ ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑን ውሃን አዘውተረን መጣጣት ይመከራል።

መረጃውን ያጋሩ!!!
147 views16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 19:58:59 ስትሮክ(STROKE)


1.ስትሮክ ምንድን ነው?

• የራስ ቅል (ጭንቅላት)ውስጥ ደም ሲፈስ
• ወደ ጭንቅላት ውስጥ የጓጎለ ደም ሲገባ
• ወደ ጭቅላት የሚገባው ደም ሲቋረጥ ነው።
እንደ አጠቃላይ ስትሮክ ማለት ከላይ በተጠቀሱት ምክንያት አንጎል ሲጠቃ ነው።

2. ሁለት አይነት ስትሮክ አለ።

ሀ. 1ኛው ኢስኬሚክ(Ischemic) ስትሮክ የሚባል ነው።
• ይህ አይነቱ ስትሮክ በሰውነት ውስጥ ባሉና በተለያዩ የደም ቱቦዎች ውስጥ ደም ይጒጉልና ከዚያም ወደ አንጎል በመሄድ የአንጒል ህዊሳትን ሲያውክና ሲያውክ የሚፈጠር ነው። ይህም የአንጎል ህዋሳት ግልኮስና ኦክስጅን እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል። 80% የሚሆነው ስትሮክ በዚህ ምክናየት ይከሰታል።
ለ. 2ኛው ሄሞረጅክ(Hemorragic) ስትሮክ የሚባል ነው።
• ይህ ደግሞ ቀጥታ አንጎል ውስጥ ደም ሲፈስ የሚከሰት ነው።ምክናየቱ ደግሞ ከፍተኛ የደም ግፊት፡ የደም ቱቦዎች መሳሳትና መቅጠን ነው።

#ዋና ዋና የስትሮክ ምልክቶች ምን ምን ናቸው?
1. የእጅ፡ የእግርና የፊት መደንዘዝና መስነፍ
2. እይታን ማጣት
3. መናገር አለመቻል
4. ሌሎች የተናገሩንንም መረዳት አለመቻል
5. ድንገተኛና ከባድ የራስ ምታት
6. የሰውነትን ሚዛን መጠበቅ አለመቻል

ስትሮክን መከላከል ይቻላል?
• አዎ 50% መከላከል ይቻላል።
#ለስትሮክ #የሚያጋልጡ #ነገሮች
1. ከፍተኛ የደም ግፊት
2. የልብ ችግር(ሁሉም አይደለም)
3. ከቁጥጥር ያለፈ የስኳር በሽታ
4. የኰሌስትሮል መጠን መጨመር
5. ማጤስ
6. መጡኑ የጨመረ የአልኮል መጠጥ
7. ውፍረት
8. ጭንቅላትንና ልብን የሚመግቡ የደም ቱቦዎች ላይ ችግር ካለ።
• ወንድ መሆን፡ እድሜ ከ65በላይ ከሆነ፡ በቤተሰብ ካለና ጥቁር መሆን የመጠቃት እድል ከሌሎች አኳያ ይጨምራል።
#ስትሮክ ሁለት ደረጃ አለው።

1. Major Stroke የሚባል፡ ለማከብ አስቸጋሪ የሆነና ወድያው ገዳይ የሆነ ነው።
2. Minor Stroke የሚባል፡ የሚታከምና በህክምና ለውጥ ማምጣት የሚቻልበት አይነት ነው።


እንደ ማጠቃላያ


#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

#ስትሮክ ሊከሰትባቸው የሚችሉባቸው መንገዶች ሁለት ናቸው፡- በጭንቅላት ውስ በሚከሰት የደደም መፍሰ ወይም ወደ ጭንቅላት ሊደርስ የሚገባው የደም ፍሰት መቀነስ ወይም መቋረጥ ፡፡

#የስትሮክ #ህመም #ምልክቶች

ለመራመድ መቸገር ወይም ሚዛን አለመጠበቅ
ለመነጋገር መቸገር
የሰውነት ክፍል (እጅ ወይንም እግር) ያለመታዘዝ
የአይን ብዥታ
ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ የራስ ምታት
ግራ የመጋባት ስሜት

#ለበሽታው #ሚያጋልጡ #ሁኔታዎች

#እድሜ፡- በእድሜ በገፋን ቁጥር በስትሮክ የመጠቃት እድላችን ይጨምራል
#ጾታ፡- ስትሮክ በአብዛኛው በወንዶች ላይ እንደሚከሰት ጥናቶች ያመለክታሉ
#በዘር ሊተላለፍ እንደሚችልም ጥናቶች ያመለክታሉ
#የደም ግፊት መጨመር
#የኮሌስትሮል መጠን መጨመር
#ሲጋራ ማጤስ
በስኳር ህመም መያዝ
#የሰውነት ክብደት መጨመር
#ከዚህ ቀደም በስትሮክ መጠቃት

#ስትሮክን #የመከላከያ #መንገዶች

የደም ግፊት መጠናችንን ማወቅ እና የደም ግፊታችን ከፍተኛ ከሆነም በሚገባ ለመቆጣጠር መሞከር፡፡ የደም ግፊት መድሃኒት የምንወስድም ከሆነ በትክክል እና ያለማቋረጥ መውሰድ፡፡
የስኳር ህመም ተጠቂ ከሆኑ የስኳር መጠኖን መቆጣጠር
ጭንቀትን ማስወገድ
ሲጋራ አለማጤስ
የአልኮል መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ መጠጦችን አለመውሰድ
የምንጠቀመውን የጨው መጠን መቀነስ
ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች ያለማዘውተር
በቀን ለ 30 ደቂቃ ያህል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም የእግር መንገድ መሄድ
የሰውነት ክብደትን መቀነስ

#dxn_
172 views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 21:53:44 'የሚጥል ህመም’ ላለበት የክብሪት ጭስ ማሸተት ይጠቅማል?

የሚጥል ህመም /EPILEPSY/

የሚጥል ህመም ያለባቸው ሰዎች ያለጊዜ የመሞት እድላቸው ከጠቅላላ ሕዝብ በ 3 እጥፍ ይበልጣል ፣ ነገር ግን ለሞት መንስኤ የሚሆኑትን ነገሮች (እንደ ከከፍታ መውደቅ ፣ መስመጥ ፣ በጋለ ነገር መቃጠል ፣ የመኪና አደጋ ፣ስብራት፣ የአየር ቧንቧ መዘጋት ፣ መደፈር እና የመሳሰሉትን) መከላከል ይቻላል።

እንዴት?

የሚጥል ህመም /EPILEPSY/ የአንጎል ነርቭ ጊዜያዊ ኤሌክትሪካል ንዝረት እንጂ የክፉ መንፈስ ውጤት አይደለም ! ከሰው ወደ ሰው ተላላፊም አይደለም። ስለዚህ የሚጥል ህመም ያለባቸው ሰዎች እራሳቸውን ስተው ባዩ ጊዜ ችላ አይበሏቸው።

መደረግ ያለባቸው የመጀመሪያ እርዳታዎች

- ከጭንቅላት ስር ለስላሳ ትራስ ነገር ማድረግ
- ሲንፈራገጥ ራሱን እንዳይጎዳ በዙሪያው ያሉ ሊጎዱት የሚችሉ ነገሮችን (እሳት፣ ኤሌክትሪክ፣ ስለታማ ነገሮችን) ማስወገድ

- እንዳይንፈራገጥ በኃይል ለመያዝ አለመሞከር (የአጥንት ወይም የጡንቻ ጉዳት ሊያስከትል ይችላልና)
- አንገት አካባቢ ያሉ የልብስ ቁልፎችን ማላላት ፤ መነፅሩን ማዉለቅ

- መንቀጥቀጡ ከቆመ በኃላ እስኪነቃ ድረስ በጎኑ ማስተኛት( የአየር ቧንቧ እንዳይዘጋ ለማድረግ)

- ክብሪት አለማሽተት (የሚጥል በሽታ ያለበት ሰው ወድቆ ሲንፈራገጥ የመተንፈሻ አካሉ በምራቅ አረፋና በምላስ ሊዘጋ ይችላል ፤ የክብሪት ጪስ ሲጨመርበት ይባሱን ይዘጋል ፤ ጪሱ በራሱም አንጎልን የሚጎዱ ኬሚካሎች አሉት)

- ህመምተኛው እስኪነቃ ድረስ አብሮ መቆየት
-ህመምተኛው ከነቃ በኋላ ማረጋጋት

- መንቀጥቀጡ ከ 5 ደቂቃ በላይ የሚረዝም ከሆነ ወይንም የታማሚዉ የቆዳ ቀለም ወደ ሰማያዊነት ከተለወጠ በአስቸኳይ አምቡላንስ መጥራት

ከ care epilepsy, ethiopia ፅሁፍ የተወሰደ.

By Dr. Eyob Dagnew
219 views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 20:27:01 #ቆረቆር (Tinea capitis)

ይህ በሽታ ብዙውን ጊዜ ህፃናትን ያጠቃል፡፡ በተለይ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን፡፡ ይህ Anthropophilic ወይም Zoophilic በተሰኘ ፈንገስ አማካኝነት የሚመጣው ቆረቆር የተሰኘው የራስ ቅል በሽታ በሌላ ስሙ የራስ ቅል የቀለበት ትል( Scalp ringworm) ተብሎ ይታወቃል፡፡ ከሌሎች የቆዳ በሽታዎች ይልቅ በጣም ተላላፊ ነው፡፡
የበሽታ ምልክቶች
መጀመሪያ ሲወጣ ትንሽ ክብ መሳይና ቅርፊት ያለበት እባጭ ሆኖ ነው፡፡ ይህም ቁስል በአጭር ጊዜ ወስጥ ይሰፋል፡፡ ቁስሉም በሙሉው በሰፋ ጊዜ ነጣ ይልና እንደ ቀለበት ክብ ወይም እንደ እንቁላል ሞላላ ይሆንና ቅርፊት ይዞ በዙሪያው የተወሰነ ዳርቻ ይኖረዋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ብዙ ቁስሎች በአንድ ጊዜ በአንድ ቦታ ላይ ይወጣሉ፡፡ቁስሉ መጀመሪያ እንደወጣ በፀጉሩ ለማወቅ አይቻልም፤ ቆይቶ ግን ቁስሉ ከወጣበት ቦታ ላይ የሚበቅለው ፀጉር ይደርቃል፡፡ ወዝ የለሽ ይሆንና እየተሰበረ ሲወድቅ በቀላሉ ሊመዘዝ የሚችል የፀጉር ቁራሽ በራስ ላይ ይቀራል፡፡ ራስን ሁል ጊዜ ያሳክካል፡፡
መፍትሔ
ቁስሉ ባለበት ቦታ ላይ የበቀለውን ፀጉር መላጨት፣ መቁረጥ፣ ወይም መንቀልና ራስን ደህና አድርጎ በሳሙና ካጠቡ በኃላ አሥር ፐርሰንት አሞንያ ያለበት የሜርኩሪ ቅባት ወይም ኋይት ፊልድ ቅባት የሚባለውን በቀን ሁለት ጊዜ መቀባት ህክምናው በሚሰጥበት በመጀመሪያው ሳምንት ውስጥ ከላይ የተጠቀሰውን ቅባት በቀን ሁለት ጊዜ በመስጠት ፈንታ በቀን አንድ ጊዜ ቲንክቻር ኦፍ አዮዲን መቀባት የበለጠ ይረዳል፡፡ አንድ ሳምንት ካለፈ በኃላ ቅባቱን መቀባት ነው፡፡ ነገር ግን ቅባቱ ከመቀባቱ በፊት አዮዲኑ ጨርሶ መወገድ አለበት፡፡ Griseofulvin ወይም Terbinafine እና itraconazole የተሰኙ የሚዋጡ መድኃኒቶች በሽታውን ለማስወገድ ወሳኝ ናቸው፡፡
በሽታውን እንዴት እንከላከል
የራስ ቁስል ካለበት ሰው ጋር አለመነካካት ወይም እሱ የነካቸውን ዕቃዎች አለመንካት የሌላን ሰው ልብስ፣ ኮፍያ፣ ማበጠሪያና የፀጉር ብሩሽ አለመጠቀም፣ ድመቶችና ውሾች ሳይታወቅባቸው ይህን በሽታ የሚያመጡትን ሕዋሳት እንደሚያመላልሱ አለመዘንጋት ነው፡፡ ይሁን እና ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በተለይ ከልጆች ወደ ልጆች የሚተላለፈው በጣም ቀላልና በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ አካባቢን የሚሸፍን ሲሆን በአገራችን ጭምር የዚህ በሽታ ዋነኛ የመተላለፊያ መንገድ ተደርጎ የሚወሰደው ይሄው ነው፡፡

ምንጭ አለርት ሆ/ል
164 viewsedited  17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ