Get Mystery Box with random crypto!

ሪማቶይድ አንጓ ብግነት (rheumatoid arthritis) ሪማቶይድ አንጓ ብግነት የሰውነታችን | Health. Com/ጤናን በቴሌግራም

ሪማቶይድ አንጓ ብግነት (rheumatoid arthritis)

ሪማቶይድ አንጓ ብግነት የሰውነታችን በሽታ የመከላከል ህዋሶች በራሳቸው ላይ በሚያደርሱት ጉዳት የሚፈጠርና በመላው አካል የሚሰራጭ የብግነት በሽታ ሲሆን መገለጫውም በአንድ ጎን የሚከሰት የእጅና የእግር አንጓ ብግነት ነው ቀስ በቀስም አንጓዎችን ከጥቅም ውጪ የሚያደርግ በሽታ ነው።

ከመገጣጠሚያ በተጨማሪ ሳንባን ፣ደምን፣ ቆዳንና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን የሚያጠቃ ነው። በአብዛኛው ሴቶችን የሚያጠቃ ሲሆን በየትኛውም የዕድሜ ክልል የሚፈጠር ነው።

የሚያሳየው ምልክቶች
ከአምስት በላይ በአንድ ጎን ያሉ አንጓዎች ህመም
የአንጓ እብጠት
ጠዋት ሲነሱ ሰውነትን ማጠፍ አለመቻል
የመገጣጠሚያ እንቅስቃሴ መቀነስ
የድካም ስሜት
አጠቃላይ የጡንቻ ህመም
የክብደት መቀነስ

ከመገጣጠሚያ ውጪ ሲከሰት

ሳል ፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የደረት ህመም
የአይን እንባ መድረቅ፣ የዓይን ህመምና መቅላት
ቆዳ ላይ እብጠት፣ መጥቆርና መቅላት
የእግርና እጅ መደንዘዝ

የሚታዩ ምልክቶች

እብጠት
ሲነካ ምንም
የመገጣጠሚያ ጉዳት

የሚሰጡ ምርመራዎች

ምርመራው በአብዛኛው ከታካሚው በሚወሰደው ተረክ እና ሀኪሙ በሚያየው ምልክቶች ይለያል በተለይ ከሌሎች የአንጓ ብግነት የሚለየው የጣቶቻችን የመጨረሻውን አንጓ ባለማጥቃቱ ነው።
የላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ (rheumatoid factor, anti -CCP , ESR/CRP, CBC)
ራጅ ምርመራ

የሚሰጡ መድኃኒቶች

የህመም ማስታገሻ
የሪማቶይድ መድኃኒቶች (methotrexate, chloroquine phosphate, steroid) ፈጽሞ ያለሀኪም ትዕዛዝ መወሰድ የለባቸሁም ምክንያቱም የጎንዮሽ ጉዳታቸው የከፋ ስለሆነ ከዛም ባሻገር ክትትል በየጊዜው መደረግ አለበት።

ሪማቶይድ አንጓ ብግነት ያለበት ሰው ምን መመገብ የለበትም
አልኮል መጠጣት የለበትም
ቀይ ስጋ
ቅባት የበዛበት ምግብ
ለስላሳ
የእንስሳት ተዋጽኦ ( ወተት ፣ እርጎ ፣አይብ)
ጨው የበዛበት ምግብ
ስንዴ ገብስ እና
በፋብሪካ የተቀናበረ ምግብ መውሰድ የለበትም።

Dr. Mitiku