የማስታወስ ችሎታችንን ከፍ ሊያደርጉልን የሚችሉ የምግብ አይነቶች ------------ 1. አሳ፦ አሳ በውስጥ ለአእምሮ ጤና ጠቃሚ የሆነውን ኦሜጋ 3 /omega 3/ እዛይት በመያዙ ለአእምሮ ጤና በተለይ ደሞ ለልጆች አእምሮ እድገት ጠቃሚ ነው። እንዲሁም በአሳ ውስጥ የሚገኘው ኦሜጋ 3 የአእምሯችንን ሴሎች ከጉዳት ይከላከላል። … ስለዚህም አሳን አዘውትረን በመመገብ የአእምሯችንን ጤንነት በመጠበቅ የማስታወስ ችሎታችን ከፍ እንዲል ያደርጋል። … 2. ለውዝ፦ ለውዝ ለአእምሯችን ጤንነት ጠቃሚ በሆኑ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ በመሆኑ የማስታወስ ችሎታችንን ከፍ ሊያደረጉልን ይችላሉ ከሚባሉ የምግብ አይነቶች ይመደባል። … በተጨማሪም ለውዝ በውስጡ ለአእምሮ ነርቭ ጤንነት ጠቃሚ የሚባሉትን እንደ ቪታሚን ሲ እና ቪታሚን B6 አይነት ንጥረ ነገሮች የበለጸገ በመሆኑም የማሳታወስ ችሎታችንን ከፍ ያደርጋል ተብሏል። … 3. አቮካዶ፦ በአቮካዶ ውስጥ የሚገኙት የፋቲ አሲድ ቅባቶች አእምሯችን ንቁ እና ጤነኛ እንሆን በማድረግ ከፍ ያለ የማስታወስ ችሎታ እንዲኖረን ይረዳሉ። … 4. ቀይ ሽንኩርት፦ ሻል ያለ የማስታወስ ችሎታ እንዲኖረን ከፈለግን በምጋባችን ውስጥ በርከት ያለ ሽንኩትር ጨምሮ መመገብ ይመከራል ምክንያቱ ደግሞ ሽንኩርት በውስጥ በያዘው አንቲኦክሲዳንት ንጥረነገር አእምሯችንን ከጉዳት ስለሚከላከል ነው። … 5. አፕል፦ አፕል ወይም ፖም በውስጡ ኩዌርስቲን የተባለ አንቲ ኦክሲዳንት ንጥረ ነገር የበለጸገ በመሆኑ አእምሮን ከጉዳት በመከላከል የማስታወስ ችሎታችን እንዲጨምር ያደርጋል። … 6. ቀይ ስር፦ ቀይ ስር በአይረን የበለጸገ በመሆኑ ደማችን በቂ ሄሞግሎቢን እንዲያገኝ በማድረግ አእምሯችን በቂ ኦክሲጅን አግኝቶ ጤነኛ እንዲሆን በማደረግ ለማስታወስ ችሎታችን መጨመር አይነተኛ ሚና አለው። … 7. ማር፦ ማር በተፈጠሮ ሀይል ሰጪ ምግብ በመሆኑ አዘውትረን የምንወስድ ከሆነ የአእምሯችንን የማሳታወስ አቅም ከፍ እንዲል ያግዛል። … 8. ውሃ፦ ውሃን አዘውትሮ መጠጣት ለአእምሯችን ጤንነት እና የማስታወስ ችሎታን ከፍ በማድረግ ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑን ውሃን አዘውተረን መጣጣት ይመከራል። … መረጃውን ያጋሩ!!! 147 views16:37