Get Mystery Box with random crypto!

#ቆረቆር (Tinea capitis) ይህ በሽታ ብዙውን ጊዜ ህፃናትን ያጠቃል፡፡ በተለይ ዕድሜያቸ | Health. Com/ጤናን በቴሌግራም

#ቆረቆር (Tinea capitis)

ይህ በሽታ ብዙውን ጊዜ ህፃናትን ያጠቃል፡፡ በተለይ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን፡፡ ይህ Anthropophilic ወይም Zoophilic በተሰኘ ፈንገስ አማካኝነት የሚመጣው ቆረቆር የተሰኘው የራስ ቅል በሽታ በሌላ ስሙ የራስ ቅል የቀለበት ትል( Scalp ringworm) ተብሎ ይታወቃል፡፡ ከሌሎች የቆዳ በሽታዎች ይልቅ በጣም ተላላፊ ነው፡፡
የበሽታ ምልክቶች
መጀመሪያ ሲወጣ ትንሽ ክብ መሳይና ቅርፊት ያለበት እባጭ ሆኖ ነው፡፡ ይህም ቁስል በአጭር ጊዜ ወስጥ ይሰፋል፡፡ ቁስሉም በሙሉው በሰፋ ጊዜ ነጣ ይልና እንደ ቀለበት ክብ ወይም እንደ እንቁላል ሞላላ ይሆንና ቅርፊት ይዞ በዙሪያው የተወሰነ ዳርቻ ይኖረዋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ብዙ ቁስሎች በአንድ ጊዜ በአንድ ቦታ ላይ ይወጣሉ፡፡ቁስሉ መጀመሪያ እንደወጣ በፀጉሩ ለማወቅ አይቻልም፤ ቆይቶ ግን ቁስሉ ከወጣበት ቦታ ላይ የሚበቅለው ፀጉር ይደርቃል፡፡ ወዝ የለሽ ይሆንና እየተሰበረ ሲወድቅ በቀላሉ ሊመዘዝ የሚችል የፀጉር ቁራሽ በራስ ላይ ይቀራል፡፡ ራስን ሁል ጊዜ ያሳክካል፡፡
መፍትሔ
ቁስሉ ባለበት ቦታ ላይ የበቀለውን ፀጉር መላጨት፣ መቁረጥ፣ ወይም መንቀልና ራስን ደህና አድርጎ በሳሙና ካጠቡ በኃላ አሥር ፐርሰንት አሞንያ ያለበት የሜርኩሪ ቅባት ወይም ኋይት ፊልድ ቅባት የሚባለውን በቀን ሁለት ጊዜ መቀባት ህክምናው በሚሰጥበት በመጀመሪያው ሳምንት ውስጥ ከላይ የተጠቀሰውን ቅባት በቀን ሁለት ጊዜ በመስጠት ፈንታ በቀን አንድ ጊዜ ቲንክቻር ኦፍ አዮዲን መቀባት የበለጠ ይረዳል፡፡ አንድ ሳምንት ካለፈ በኃላ ቅባቱን መቀባት ነው፡፡ ነገር ግን ቅባቱ ከመቀባቱ በፊት አዮዲኑ ጨርሶ መወገድ አለበት፡፡ Griseofulvin ወይም Terbinafine እና itraconazole የተሰኙ የሚዋጡ መድኃኒቶች በሽታውን ለማስወገድ ወሳኝ ናቸው፡፡
በሽታውን እንዴት እንከላከል
የራስ ቁስል ካለበት ሰው ጋር አለመነካካት ወይም እሱ የነካቸውን ዕቃዎች አለመንካት የሌላን ሰው ልብስ፣ ኮፍያ፣ ማበጠሪያና የፀጉር ብሩሽ አለመጠቀም፣ ድመቶችና ውሾች ሳይታወቅባቸው ይህን በሽታ የሚያመጡትን ሕዋሳት እንደሚያመላልሱ አለመዘንጋት ነው፡፡ ይሁን እና ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በተለይ ከልጆች ወደ ልጆች የሚተላለፈው በጣም ቀላልና በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ አካባቢን የሚሸፍን ሲሆን በአገራችን ጭምር የዚህ በሽታ ዋነኛ የመተላለፊያ መንገድ ተደርጎ የሚወሰደው ይሄው ነው፡፡

ምንጭ አለርት ሆ/ል