Get Mystery Box with random crypto!

ሾተላይ ለምን ይከሰታል? የሰው ልጅ ከወላጆቹ ዘረመል ተነስቶ ከ4 የደም አይነቶች ውስጥ አ | Health. Com/ጤናን በቴሌግራም

ሾተላይ ለምን ይከሰታል?

የሰው ልጅ ከወላጆቹ ዘረመል ተነስቶ ከ4 የደም አይነቶች ውስጥ አንዱን ሊይዝ ይችላል። እነኝህም
1. “A”
2. “B”
3. “AB”
4. “O” ተብለው ይጠራሉ።

በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ህዋሶች(RBCs) የላይኛው ሽፋናቸው ላይ Rh የተባለ ፕሮቲን (protein) ካላቸው ሴቲቱ Rh positive ናት ማለት ሲሆን እነኚህ ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ Rh negative ናት ማለት ነው።

ለምሳሌ:- ሴቲቱ የደም አይነቷ B ቢሆንና ቀይ የደም ሴሎቿ ላይ Rh ፕሮቲን ካለ B Positive ናት ማለት ነው፤ እነኚህ Rh ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ B Negative ናት ይባላል።

አንዲት ሴት ሾተላይ የሚባለው ችግር ሊከሰትባት የሚችለው እሷ Rh negative ሆና በተለያዩ አጋጣሚዎች Rh positive የሆነ ደም ወደሰውነቷ ሲገባ ሰውነቷ እነኚህን Rh positive የደም አይነቶች የሚያጠፉ(የሚገሉ) ንጥረ ነገሮች (Antibodies) ሲያመነጭ (ሲያመርት) ነው። እነኚህም እስከ እድሜልክ በሰውነቷ ይቆያሉ።

እነኚህ የተመረቱት ተከላካይ ንጥረ ነገሮች(Antibodies) የመጀመሪያው ልጅ ላይ ምንም ተፅዓኖ ሳይኖራቸው ልጁ በሰላም ሊወለድ ይችላል ነገር ግን የሁለተኛው ፅንስ የደም አይነቱ Rh positive ከሆነ ወደ ፅንሱ በማለፍ የፅንሱን Rh positive የቀይ የደም ህዋሶች ያጠቃሉ ማለት ነው፤ ይህም ፅንሱን ለተለያየ አደጋዎች ሊያጋልጠው ይችላል።

ይህም ችግር ፅንሱ ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን ሊያመጣ ይችላል ፤ እነኚህም

በፅንሱ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ውሀ መቋጠር - Fetal hydrops
በተደጋጋሚ የፅንስ መውረድ - Miscarriage
የፅንሱ የደም ማነስ - Fetal anemia
ፅንሱ በማህፀን ውስጥ እንዳለ ጊዜው ሳይደርስ ህይወቱ ማለፍ
ህፃኑ ከተወለደ በውሃላ ቆዳው ቢጫ መሆን እና የጨረር ህክምና ማስፈለግ(phototherapy)
በከፍተኛ ደም ማነስ ምክንያት ደም ለመውሰድ መጋለጥ

ሾተላይ እንዴት ይታከማል?

Rh negative የሆነችው እናት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ነገሮች ከገጠሟት
ባለቤቷ Rh positive ከሆነ
ውርጃ ካጋጠማት
ከማህፀን ውጭ እርግዝና ካጋጠማት
ከእንግዴ ልጅ ላይ የሚነሳ እጢ(Gestation trophoblastic disease) ካጋጠማት
በእርግዝና ወቅት አደጋ ከደረሰባት፤
በክትትል ወቅት ከእንግዴ ልጅ ወይም ከሽርት ዉሃ በመሳሪያ ናሙና ከተወሰደ

Anti D የተባለ ኢሚውኖግሎቡሊን (immunoglobulin) መድሀኒት በመውሰድ ሾተላይን መከላከል ይቻላል።

በእርግዝና ጊዜ Anti D የተባለውን መድሃኒትን በ 7 ወር(28 ሳምንት) ላይ እና ህፃኑ በተወለደ ቢቻል እስከ 72 ሰዓት ውስጥ በመስጠት የሾተላይ በሽታን መከላከል ይቻላል።

Rh negative የሆነች እናት(ባል Rh positive) የእርግዝና ክትትሏ ከሌሎች እናቶች ለየት ያለ እና የሚሰጣትም ቀጠሮ በዛ ያለ ይሆናል።

ይህም በልጇ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉትን የሰውነት ውሀ መቋጠር(መጠራቀም) እና የፅንሱ ደም ማነስ ካለ ቀድሞ በማወቅ ህክምናውን በቶሎ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ እዛው ማህፀን ውስጥ እንዳለ ደም በመለገስ እና ወቶ ለመኖር ብቁ በሆነበት ጊዜ ቀድሞ እንዲወለድ በማድረግ ተጨማሪ የሆኑ የህክምና እርዳታዎች እንዲደረግለት ማድረግ ይቻላል።

መልካም ምሽት