2023-03-03 08:08:34
ድፍረትህ ድልህ ነው! ወስነህ ወደ ትግል ከገባህና ከፊት ለፊትህ የመጣውን ነገር በሙሉ ለመጋፈጥ እራስህን ካዘጋጀህ ፣ ፍረሃትህን ስርስር እየተከተልክ የምታሳድድ ከሆነ ፣ ከትናንት ማንነትህ በተሻለ የዛሬውን መገንባት ላይ ካተኮርክ የድሉ መሰረት አንተ መሆን ትጀምራለህ ። አሸናፊነት ጥሎ ማለፍ ብቻ አይደለም ፤ ድል አድራጊነት ልቆ መገኘት ብቻ አይደለም ። አስፈሪውን ውጣውረድ የተጋፈጠም አሸናፊ ነው ፤ ላመነበት ነገር በድፍረት የሚፋለምም ባለ ድል ነው ፤ እያመመውም ፣ እየጎረበጠውም ቢሆን ወደፊት መጓዝን የመጀመሪያ ምርጫው ያደረገም አሸናፊ ነው ። በተመቻቸ ሁኔታ ውስጥ ድል አድራጊ ጀግና አይገኝም ፤ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ በሆነ ሰዓት አሸናፊ አይፈጠርም ። በፈታኝ ሁነት መሃል ደፋርና ወደፊት የሚጓዝ ሰው ከመጨረሻው ባይደርስ ፣ የአሸናፊነት ሽልማት ባይሰጠው ፣ ስሙ ከፍ ብሎ ባይነገር እንኳን ድፍረቱና ወኔው ብቻ አሸናፊ ያደርገዋል ።
አዎ! ጀግናዬ..!
ድፍረትህ ድልህ ነው! የማይሆን የሚመስለውን ፣ የማይቻል ፣ የማተገበር የሚመስለውን ነገር ፊትለፊት መጋፈጥህና ለማድረግ መሞከርህ በእራሱ አሸናፊነት ነው ። ለመማር እራሱን ያዘጋጀ ሰው የእውቀትን ፣ የመሻሻልን ፣ የማደግን እጣፈንታ በእጅ ይዞ የሚጓዝ ነው ። ሙሉ በሙሉ ለማሸነፍ ጥረትህን መጀመር አለብህ ፤ ሳትጀምር አሸናፊነት የሚባል ነገር የለም ። የድልህ መሰረት ድፍረትህ ነው ፤ ውስጥህ የሚቀጣጠለው የትልቅነት ወኔ ነው ፤ ፋታ የነሳህ የዛሬ ችግራና ስቃይህ ነው ። ዛሬ ካለህበት አጣብቂኝ ሁኔታ በተሻለ ሊያነቃቃህና ወደ ተሻለው እርምጃ ሊወስድህ የሚችል ነገር የለም ። ያለፍክበት መንገድ ፣ የደረሰብህ ተፅኖ ፣ የከፈልከው ዋጋ ፣ የወጣሀው የወረድከው አቀበት ቁልቁለት ፣ የተሰጠህ ያልተገባ ስም ፣ የከዳህ ወኔና ድፍረት በሙሉ የተሻለ ተግባር እንድትፈፅም ፣ ወደፊት እንድጓዝና ለድል እንድትበቃ የሚያደርግህ አይነተኛ ማንቂያህ ነው ።
አዎ! በእጅህ ላይ ካለው ተነስተህ ትልቁን ከፍታ መቆናጠጥ ትችላለህ ፤ ባለህ ነገር ጀምረህ የሌለህን ነገር ማግኘት ትችላለህ ። ችሎታህ በድፍረትና በወኔ ሲታገዝ ኖረሀው የማታውቀውን ህይወት መኖር ትጀምራለህ ። ጅማሬህን እንደ ድል ቁጠረው ፤ ተነሳሽነትህን እንደ አሸናፊነት ተመልከተው ፤ የማያባራውን ውስጣዊ ወኔ እንደ ትልቅ ጀብድ ውሰደው ። ትናንሾቹን እርምጃዎችህን ማክበር ስትጀምር ዋንኛው ድልህ ወዳንተ እየቀረበ ይመጣል ፤ ለእራስህ ብለህ ለከፈልከው ዋጋ እውቅና መስጠት ስትጀምር መጪው ጊዜህ ብሩህና የከፍታ ዘመን ይሆናል ። ድሎችህ በእያንዳንዱ እርምጃዎችህ ውስጥ ናቸው ። አሸናፊነትህ ለማሸነፍ ወስነህ ወደ ተግባር ከገባህበት ሰዓት ይጀምራል ። ለእያንዳንዱ ውሳኔዎችህ እውቅና ስጥ ፤ ጅማሬህን እንደ ድል ፣ ወኔና ብርታትህንም እንደ አሸናፊነት ቁጠረው ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.4K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited 05:08