Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ mirttshefoch — ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
የሰርጥ አድራሻ: @mirttshefoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 31.66K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 22

2023-03-15 18:42:02
"...በነገራችን ላይ ማህይምነትና ድቁርና ሁለቱ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ማህይም የሚል የትምህርት እድል ያላገኘ ነው። ድንቁርና ግን የትምህርት እድልም አግኝቶ በማህይምነት ግርሻ የተጠቃው ነው። ፈረንጆች ምን ይላሉ arogance (እብሪተኝነት) Ignorance (አለማወቅን) ያመጣል። arogance እና Ignorance ይመጋገባሉ። ማህይምነት ሲያገረሽብህ እብሪተኛ ትሆናለህ፤ እብሪተኛ ስትሆን ደግሞ የበለጠ ማህይምነት ያገረሽብሃል። እናም ብዙዎቻችን በዲግሪያችን ጀርባ በድቁርና ነው የምንኖረው። ሰውም እንዳይመክረን ዲግሪ አላቸው ይባላል። በእድርም ስትሄድ ዶክተር ይናገር ነው የሚባለው። ግን ሰውየው መሃይምነት ውስጥ ነው ያለው።.... እና ምንድነው እየሆነ ያለው ብላችሁ ያያችሁት እንደሆነ...መደማመጥ የሌለው፣ መነጋገር የሌለበት፣ ማንተማመነው፣ ለችግሮቻችን መፍትሔ ማናገኘው የምሁር ቁጥር እንጂ የአዋቂ ቁጥር ስለሌለ ነው። ለምን ያላችሁ እንደሆነ አብዛኞቻችን በመሃይምነት ግርሻ ውስጥ ስላለን ነው። የዲግሪ ፎቶ በየቤቱ ስትሄዱ ግድግዳ ላይ ታያላችሁ። በትክክል ያ የሚያሳየው ሰውዬው በማህይምነት መኖሩን ነው። ምክንያቱም ማረጋገጫው ያ ብቻ ነው። ሌላ ምን ያሳያል? ምን እናሳያለን ሌላ?...."

ይሄን የተናገሩት በአማራ ቴሌቪዥን ዶክተር አለማየሁ ናቸው።
ከዲግሪ ባሻገር ጎበዝ አንባቢዎች እንሁን እላለሁ፣ ስታነቡ ወይንም እንደዚህ ያለ አነቃቂ ንግግሮች ስታገኙ በፔጃችሁ ፖስት እያደረጋችሁ አስነብቡን
1.5K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, 15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 03:37:48
​​​​ #ደህና_ሁኝ
ወንድ ሁን ከማለት ወንድነቴን ንቀሽ፣
ቅድሚያ ወንድነትን እወቂ ጠንቅቀሽ፣
ባንቺ ልዩ አፈታት ባንቺ አማርኛ፣
ወንድን ወንድ የሚያሰኝ የአቅሙ መመዘኛ፣
.........................ዱላው ድብድቡ፣
......................... ዛቻ እና ስድቡ፣
ብለሽ ከደመደምሽ ካመንሺበት ደፍረሽ፣
በመታቀፍ ፋንታ መመታት ካመረሽ፣
ክፋትሽን መቻሌ ፋቅሬ ካስጨከነሽ፣
በቁልምጫው ፋንታ ስድብ ከናፈቀሽ፣
ትዕግስቴ ሴትነት ውርደት ከመሰለሽ፣
በእኔ መመዘኛ አንቺም ሴት አይደለሽ፣
ስለዚህ ደህና ሁኝ እኔም ካንቺ አልዘልቅም፣
...................ምክኒያቱም.....................፣
ሴት ስትሳም እንጂ ስትመታ አላውቅም

https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
43 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  00:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 02:59:21
ወደ ከፍታው ተተኮስ!

“ለመማር ፈቃደኛ ካልሆንክ ማንም ሊረዳህ አይችልም፣ ለመማር ፈቃደኛ ከሆንክ ማንም ሊያስቆምህ አይችልም”

መማር ማደግ ነው! መማር መለወጥ ነው! መማር መጠንከር ነው! መማር ወደፊት መገስገስ ነው! በየጊዜው የሚማርን ሰው ማንም ሰው ፣ ምንም ነገር ሊያስቆመው አይችልም!

ካለማቋረጥ በማንበብ ተማሩ!
ካለማቋረጥ ካለፈው የሕይወት ልምምዳችሁ ተማሩ!
ካለማቋረጥ ከሰዎች የትምህርትንና የምክርን እውቀት በመቀበል ተማሩ!
ካለማቋረጥ የሰዎችን ስኬትና ውድቀት በማየት ተማሩ! 
ካለማቋረጥ ሰዎች ሆን ብለው ከሚያደርጉባችሁ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተማሩ! ካለማቋረጥ ከተማራችሁ ፣ ካለማቋረጥ በማደግና ወደፊት በመገስገስ ትቀጥላላችሁ!

አዎ! ጀግናዬ..! ህይወት ትምህርት ነች ፤ ከፊትህ ያለው ቁስ ፣ የምታየው ፣ የምትጨብጠው ፣ የምትዳስሰው አካል በእራሱ መማሪያህ ነው ፤ አሰልጣኝህ ነው ፤ በአንድ አዎንታዊ መንገድ የሚቀርፅህ መቅረጫህ ነው ። እድገትን የሚመኝ ሰው መቼም ከመማር አይመለስም ፤ ከማንበብ አይገታም ፤ መሰልጠንን አያቆምም ፤ እውቀት ላይ ፊቱን አያዞርም ። ተማር ፣ እወቅ ፣ ያወከውን አሳውቅ ፤ እደግ ፣ ተመንደግ ፣ በህይወትህ ጥበብን ግለፅ ወደ ከፍታው ተተኮስ
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
92 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  23:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 02:52:52 እራስህን ፈልግ!

ከምትፈልጋቸው በላይ እራስህን ፈልግ፤ ከሚያስፈልጉህ በተሻለ ለእራስህ ታስፈልጋለህ። ከተደገፍካቸው በተሻለ አምላክህና እራስህ ላይ ተደገፍ፤ ከምትጠብቃቸው አምላክህንና እራስህን ጠብቅ። በህይወትህ ሰዎች ያስፈልጉሃል፤ ከጎንህም ሊሆኑ ይገባል። ነገር ግን አብሮነታቸው ሙሉ ማንነትህን ሊያጠፋና የነርሱ ተመፅዋችና ተረጂ ሊያደርግህ አይገባም። ከቤተሰቦችህ ውጪ ሁሌም በህይወትህ የሚከሰቱ ሰዎች ቋሚ አይደሉም። ትናንትና ዛሬ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ተገኝተሃል፤ ፍላጎትህ ለመደገፍና በእነርሱ በኩል እንዲያልፍልህ ከሆነም ከትርፍህ ይልቅ ኪሳራህ በዝቶ ታገኘዋለህ። የድጋፍህን አስተማማኝነት ካላወክ ላለመውደቅህ ምንም ዋስትና የለህም። በሰዎች የተደገፉ፣ ሰዎችን የያዙ መጨረሻቸው ምን እንደሆነ ከማንም የተሰወረ አይደለም። አምነህ ታምነህበት ሙሉ ጊዜህን ሰተሀው ስትጠብቀው የነበረው ሰው ምናልባትም አንተንም የሚረሳበት ጊዜ ሊፈጠርብህ ይችላል።

አዎ! ጀግናዬ..! እራስህን ፈልግ! አምላክህን አግኘው፤ በንፁ መንፈሱ ተመራ። አንዳንዴ ቀጥተኛ መንገዶች ብቻ ትክክል ላይሆኑ ይችላሉ፤ አቋራጭ መንገዶችም ትክክል የሚሆኑበት ጊዜ ይኖራል። ነገር ግን ዋጋቸውንና ሊያስከትሉ የሚችሉትን አደጋዎች ስናነፃፅር አቋራጭ የተባሉትና ግልፅነት የጎደላቸው፣ ከእራሳችን በላይ በዙሪያችን ያሉ ሰዎችን በማመን የገባንባቸው መንገዶች አደጋቸው ይከፋል፤ ችግር አይጠፋቸውም። ሊደግፉን የሚችሉ ሰዎችን፣ ሊረዱን የሚችሉ ባለስልጣናትን፣ ሊያግዙን የሚፈልጉ የቅርብ ሰዎችን መጠበቅ፣ ከእራሳችን በላይ ሙሉ እምነታችንን እነርሱ ላይ መጣል ለተጨባጭ እርምጃ ሳይሆን ወደፊት ለማሰብ እንኳን እንድንቸገር ያደርገናል።

አዎ! ውስጥህ ለለውጥ ዝግጁ ባልሆነበት ሁኔታ በብዙ አጋጣሚዎች ብትከበብ እንኳን ለውጥ ልታመጣ አትችልም። እራስን ከመፈለግና በእራስ ከመተማመን ውጪ የተሻለ ምርጫ እንደሌለህ እመን። ባለህ ነገር ከመጀመር ውጪ ይህ ነው የምትለው በእምነት ጠብቀህ በእጅህ የሚገባ ነገር የለም። ከእነርሱ ለምታገኘው ጥቅም በቻ ብለህ ደጃቸውን የምትጠና፣ የምትማፀናቸው፣ ሙሉ ትኩረትህንና ጊዜህን እነርሱን በመጠበቅ ላይ የምታውለው ከሆነ በእነርሱ ፍቃድና ፍላጎት ላይ የመውደቅህ እድል በጣም ሰፊ ነው። የምትጠብቀው ትልቅ ነገር ካል ከአምላክህ ጠብቅ፤ በአንተ ላይ ስራውን እንዲሰራ ፍቀድ። የተመኘሀው እንዲሆንልህ ትኩረትህን ከሌሎች ላይ አንሳ፣ እራስህን በጥልቀት ተመልከት፤ ከምትችለው በላይ ሳይሆን በችሎታህ ልክ፣ እንዳቅምህ እራስህ ላይ ስራ፤ ከሌላው ስትጠብቀው የነበረውን አበርክቶት ለእራስህ አድርግ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
103 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  23:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 05:55:01 ልክህን አስቀድም!

አንተ ማለት ትክክለኛው ማንነትህ ነህ። ዛሬ ታይቶ የሚጠፋ ማንነት የለህም፤ በየጊዜው የሚቀያየርና ለሰዎች እይታ ብቻ የሚኖር ስብዕና የለህም። የምታደርገውን ሁሉ ሰዎች አይተው እንዲያደንቁህ አትፈልግ፤ በሰው ፊት ተወዳጅና ጥሩ ስም ያለው ለመምሰል ከአቅምህ በላይ አትኑር። ሁላችንም ደረጃ አለን፤ እያንዳንዳችን የሚወክለን የገቢ ምንጭ፣ ማንነትና ስብዕና አለን። ለእራሳችን ከመገዛታችን፣ እራሳችንን ከማስደሰታችን፣ በእራሳችን ከመኖራችን በፊት ግን ለታይታና እይታ ውስጥ ለመግባት የምናወጣው ወጪ፣ የምናባክነው ጊዜና ንብረት ሁሉ ዋጋችንን የሚያወርድ እንጂ የሚያሳድግ አይደለም። ሳይኖርህ እንዳለህ ስለታሰብክ፣ ከደረጃህ በላይ ስለተለካህ፣ በማይወክልህ ማንነት ስለታወቅክ ጊዜያዊና የውሸት ኩራት (pride) ሊሰማህ ይችላል፣ ነገር ግን በስተመጨረሻ እራስህን ስታታልል እንደነበር ትገነዘባለህ። መኖራችን ለሰዎች፣ ለስም፣ ለይውንታ፣ ለመወደድና ለክብር አይደለም። መኖራችን ከእራሳችን በላይ ሰዎችን በትክክለኛው መንገድ ለመርዳትና ለማገዝ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ልክህን አስቀድም! እንደ አቅምህ፣ በደረጃህ ተንቀሳቀስ። ሃብታም መስለህ መታየትህ ያለህንም ከማሳጣቱ ውጪ ምንም የሚያተርፍልህ ነገር የለም፤ የቤትህን ክፍተት ሳትሞላ በሔድክበት ሁሉ ካላጋበዝኩ ማለትህ ክፍተትህን አይሞላም፤ ባልሆንከው ሰውነት ለመታወቅ መጣርህ ትክክለኛውን አንተነትህን አይቀይርም። እውነት እውነት ነው፤ ምንም ብትደብቀው፣ ብታስመስልበት፣ በውሸት ብትሸፍነው በጊዜው መታወቁና መገለፁ አይቀርም። ያንቺ ባልሆነው ጌጥ ብታጌጪ አንድም ድጋሜ በእራሱ ጌጥ ለመታየት ትቸገሪያለሽ፣ ሌላም ያለጌጥ ያለውን ማንነት ለማሳወቅ አጣብቂኝ ውስጥ ትገቢያለሽ። ማንም የሚችለውን ያውቃል፤ ወጪውን ገቢውን ጠንቅቆ ይረዳል፤ መጠኑ ለእራሱ ግልፅ ነው።

አዎ! ለጊዜያዊ ከንቱ አድናቆትና ውዳሴ ብለህ እወነተኛ ማንነትህን (identity) አትጣ፤ ከምትችለው በላይ ለመኖር አትሞክር፤ አቅምህን ተረዳው፤ ችሎታህን በሚገባ እወቅ። ማስመሰል ከከፋው ውድቀት በቀር የሚያመጣው ነገር የለም። ሙሉና የተረጋጋ ህይወት የሚገኘው ሰዎች ፊት መስሎ ለመታየት በሚደረገው ጥረት ሳይሆን፣ የእራስን መልክና ገፅ፣ አቅምና ደረጃ በመቀበል በእርሱ ልክ በሚገባ በመኖር ነው። ከሌለህ የለህም፤ እንዳለህ ለማስመሰል የምታስመስልበት ምክንያት የለም። ድህነትህን አይቶ የሚርቅህ ካለ ቢመጣም አንተን ብሎ ሳይሆን ንብረትህን ብሎ እንደሆነ ተረዳ። በየጊዜው እራስህን ከማሻሻል በላይ ለታይታ በመኖርና በማስመሰል እራስህን አታድክም። መኩራት ካለብህ ባለህና እጅህ ላይ ባለው ነገር ኩራ፤ መደሰት ካለብህ ከውጭ በሚመጣ አድናቆትና ውዳሴ ሳይሆን ከገዛ ማንነትህ ከውስጥህ በሚመነጨው ጥልቅ ስሜት ተደሰት።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.0K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 05:54:32 በፍቅር እደግ!

የህይወት ክህሎት አሰልጣኙ ማይክ ፊልድስ (J. Mike Fields) ለፍቅር ያለንን አረዳድ በዚህ እንድናድሰው ያስገነዝበናል። " በፍቅር እደግ እንጂ በፍቅር አትውደቅ። " ፍቅርን ለለውጥ፣ ለእድገትና ለብልፅግና መጠቀም ከተቻለ በፍቅር ውስጥ የሚፈጠሩት አለመግባባትና መጎዳዳት እየከሰሙ ይመጣሉ፤ ችግሮች ቢኖሩም ትኩረቶች ሁሉ ወደ መፍትሔዎች ይዞራሉ፤ ክፍተቶች ቢፈጠሩም በተገቢው ጊዜ እልባትን ያገኛሉ። ፍቅር የሚጥል ሳይሆን የሚያነሳ፣ ነፍስን የሚዘራ፣ ማንነትን የሚያሻሽልና ወደ ተሻለው መዳረሻ የሚያደርስ ነው። የፍቅር አይነቶች ቢለያዩም ዋናው አላማቸው ግን አዎንታዊውን ስሜት በማስረፅ የተረጋጋና አስደሳች ህይወት መፍጠር ነው። እውነተኛ ፍቅር ሁሌም ነፍስ አለው፤ ሊለካ የማይችል፣ ሚዛን የሌለው ጥልቅ ስሜት አለው።

አዎ! ጀግናዬ..! በፍቅር እደግ፤ በመልካም ሃሳብ ከፍ በል፤ በቅን ልቦና፣ በደግ ሃሰብና በጥበብ ከፍ በል። ሰው ሁሉ ታላቁ ሃይል የተባለውን ፍቅር ቢመርጥና በእርሱ መንገድ ቢመላለስ የአለም ገፅ ምነኛ በተቀየረ ነበር። አንተ መልካም ብታስብ የሚተናኮልህ፣ የሚከፋብህ አይጠፋም፤ ተንኮሉንም ሆነ ክፋቱን የምታሸንፈው ግን በበዛው መልካምነትህ ብቻ ነው። የፍቅርን አሸናፊነት ከቃል በላይ ልትኖረው ይገባል፤ ሰዎችን በበጎነት መግዛት እንደሚቻል ማረጋገጥ ይጠበቅብሃል። የምር ፍቅርን እየኖርከው እንደሆና በውስጡም እያደክ እንደሆነ እራስህን ጠይቅ። በቅድሚያ የሚያሳድግህ የፍቅር አይነት ለእራስህ ያለህ ልባዊ ፍቅርና ክብር ነው። እንዲደረግልህ የምትፈልገውን ምንያክል ለእራስህ ታደርጋለህ? የምትመርጠውን ማንነት ምንያክል በውጥህ ፈጥረሀዋል?

አዎ! ለእራስህ ያለህ ፍቅር ባደገ ልክ የምታድገው አንተና በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ናቸው። ለማንኛውም ሰው ያለህ ክብርና ቦታ ይቀየራል፤ ግንኙነቶችህ ጤናማና የተረጋጉ ይሆናሉ፤ ህልምህን ለመኖር አትቸገርም፤ ራዕይህን ለማሳካት የሚያግዝህን ከባቢ በቀላሉ ትፈጥራለህ። ፍቅርን እንደ ትልቁ የአላማህ ማስፈፀሚያ ግበዓት ተጠቀመው። ፍቅር የማይዘው አዎንታዊ እሳቤ የለም። አብሮነት፣ መረዳዳት፣ መግባባት፣ ለውጥ፣ እድገት፣ መልካም ውጤትና ስኬት በሙሉ ከፍቅር ምንጭ የሚቀዱ ናቸው። ለሙያህ ያለህ ፍቅር ሙያህን ያሳድግልሃል፤ ለፍቅር አጋርህ ያለህ ንፁህ ፍቅር ብርታትና ስኬታማ ህይወትን ያጎናፅፍሃል፤ በዙሪያህ ላሉ ለቤተሰቦችህ፣ ለጓደኞችህና ለወዳጆችህ ያለህ ፍቅር ደስተኛ፣ ሰላማዊና አመስጋኝ ያደርግሃል። ፍቅርን በመኖር በፍቅር እደግ፤ ለስኬትህም እንደ ግበዓት ተጠቀመው፤ ወዳስቀመጥከው መዳረሻም ተሸጋገርበት።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
961 viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  02:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 03:18:11 ሃፍረት አይሰራም!

ለምትወደው ነገር ሃፍረት ፣ እፍረት ፣ ይሉኝታ ብሎ ነገር የለም ። በምትኩ ግን ስረዓት አለ ፣ ምግባር አለ ፣ ቅድመተከተል አለ ። ማድረግ የምትፈልገውን ለማድረግ ሃፍረት ከያዘህና የምትሸማቀቅ ከሆነ መቼም ሃሳብህን ማሳካትና መኖር አትችልም ። በሃፍረት ውስጥ ቀና ማለት የለም ፤ እራስን መግለፅ አይቻልም ፤ እንዳሰቡት ፣ እንዳቀዱት መጓዝ እጅግ አዳጋች ነው ። ህይወት አብዝተህ ስላሽቃበጥክላት ፣ ከሚገባት በላይ ስላከበድካት ፣ እሹሩሩ ስላበዛህባት ቀላልና አስደሳች አትሆንም ። የምትይዘው የምትጨብጠው እስክታጣ የምትሸማቀቀው ለማን ብለህ ነው ? በምታገኘው በረከት የማትኮራው ፣ በማንነትህ የማትደሰተው ፣ በጥልቁ መገለጫህ በስብዕናህ የማትረካው ለምንድነው ? አንተ ሳትቀየር ነገሮች ይቀየራሉ ብለህ የምታስብ ከሆነ አትሳሳት ። በይሉኝታ እየተሰቃየህ ፣ የሰዎችን ተቀባይነት እየተመኘህ ፣ ድጋፍን እየጠበክ ፣ እራስህን እያታለልክ በፍፁም ሌላ የሚቀየር ነገር እንዳትጠብቅ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሃፍረት አይሰራም ፤ የምትፈልገውን ለማግኘት መሸማቀቀ ፣ የሚገባህን ለማሳካት ይሉኝታና ሰቀቀን ቦታ የላቸውም ። ከልብህ መፈለግህን የምታውቀው ማንንም ሳትሰማ ማድረግ ስትጀምር ነው ። በእርግጥም ያለእርሱ መኖር እንደማትችል የምታውቀው በእርሱ ጉዳይ ይሉኝታን አሽቀንጥረህ ስትጥል ነው ። እራስህን አትሸውድ ፤ ከልብህ ከፈለክ ማንም እንደማያስቆምህ በሚገባ ታውቃለህ ። ሌላ ጊዜ የሚደረደሩ ምክንያቶች ከልብህ ለምትልገው ነገር ሲሆን ትዝም አይሉህም፤ ሰዎች የሚያወሩብህ ወሬ እንዴትም ሊቆጣጠርህ አይችልም ፤ ማናቸውም የሚያደርሱብህ ጫና ከቁብ የምትቆጥረው አይሆንም ። እይታህ ሁሉ ወደፊት ነው ፤ ትኩረትህ ፍላጎትህ ላይ ብቻ ነው ። ነገሮች እንደፈለከው ላይሆኑ ይችላሉ ፣ የጠበካቸው ሰዎች ላይመጡልህ ፣ ላይረዱህ ይችላሉ የፈለከውን ነገር ግን በእጅህ ታስገባለህ ።

አዎ! ከልቡ ለሚፈልግ ሰው ሁሌም አንድ ፍላጎቱን የሚያሳካበት ፣ ግቡን የሚመታበት ፣ እቅዱን ከዳር የሚያደርስበት መንገድ አለ ። ድፍረት ፣ ወኔ ፣ ተነሳሽነት ከፍላጎቱ የሚመነጩ ብርታቶቹ ናቸው ። ቀስቃሽ ባታገኝም እራስህን በእራስህ የምትቀሰቅሰውና የምታነቃቃው ልባዊ ፍላጎት ከማይናወጥ እምነት ጋር ሲኖርህ ነው ። ትላንትህ ትርጉም አልሰጠህም ይሆናል ፣ ታሪክህ በሃፍረትና በአይናፋርነት የለሞላ ሊሆን ይችላል ። ዛሬ ግን ሌላ ቀን ነው ። ከትናንትህ ካልተማርክ ምኑንም ከምኑ ለታዋህደው አይቻልህም ። የባከኑ የመሰሉህ አጋጣሚዎች ባይመለሱም ዛሬ አዲሶቹ ከፊትህ ተቀምጠዋል ። በማያሳምኑ ምክንያቶች ከሚመጥንህ ደረጃ ወደኋላ አትቅር ፤ በማይገልፅህ ባህሪ ተሰናክለህ አትመለስ ፤ በማይጠቅምህ አሉታዊ ልማድ የኋሊት አትጓዝ ። ከምኞት በላይ ለሙከራ ቅረብ ፣ ፍላጎትህን ከመተንተን በሻገር አድርገህ አሳክተሀው ተገኝ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.7K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  00:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 03:17:51 ልቤን መልስልኝ!

ፍቅር ነህ ፤ አባት ነህ ፤ ደግ ፣ አዘኛ ፣ አሳቢ ንፁህ ጌታ ፣ ፍፁም አምላክ ነህ ። ለስራህ የሚመጥን ቃል ባይኖርም ፣ የሚገልፅህ አገላለፅ ባይገኝም አንተ ግን የአማልክት አምላክ የጌቶች ጌታ ነህ ። ትናንት ነበርክ ፣ ዛሬም አለህ ፣ ነገም ለዘለዓለም ትኖራለህ ። ይቅርታህ እጅግ ግሩም ነው ፤ ሳትለመን የምትምር ፣ ሳትጠየቅ የምትፈውስ ፣ ሳይማፀኑህ ፣ ሳያለቅሱብህ ይቅር የምትል ፣ ትዕግስትህ ገደብ የሌለው ፣ ጠብቀህ የማይደክምህ ፣ ለቅንነትህ ዳርቻ ፣ ለቸርነትህ መጨረሻ የሌለህ አንተ በእርግጥም ፍቅር ነህ ፣ አባት ነህ ፣ ቸር ጠባቂ ነህ ። ስትምር ልኩን ታውቀዋለህ ፣ ይቅር ስትል ማሳረፉን ትችላለህ ። ቃል አለህ በሰማይ በምድር ልጆችህን ደጋግመህ ለመማር፣ ይቅር ለማለት ፣ ለማስተማር ። ቃልህንም ስትጠብቅ ኖረሃል ፣ ከአባትም በላይ አባት ሆነህ በቃልህ ልክ ተገልጠሃል ፤ ምህረትህንም ያለገደብ ሰጥተሃል ።

አዎ! ጀግናዬ..! የሚመጥነው ቃል ብታጣ ፣ የሚወክለው አገላለፅ ባታገኝ ፍቅር ነህ ፣ ደግ ፍፁም አምላክ ነህ በለው ። ነገር ግን ፍቅሩ እስኬት ይሆን ? ከፈጣሪ ውጪ ምህረትን ማን ያውቃል ? ይቅርታን ማን ይወክላል ? በንፅህና ማን ይገለፃል ? በትዕግስት ማን ይወከላል ? ምህረቱ እንጂ ስራችን መቼም ከፊቱ አያቆመንም ፤ ቸርነቱ እንጂ ምግባራችን ስሙን ለመጥራት አያበቃንም ፤ ርህራሔው እንጂ ማንነታችን ከቤቱ አያቀርበንም ። እለት እለት ብንበድልም እለት እለት እየማረ እዚህ አደረሰን ፤ በየቀኑ ብናሳዝነው እስከዛሬ ታገሰን ፤ ሳናቋርጥ ብናስቀይመው ፣ ከትዕዛዙ ብንወጣ ፣ ከመንገዱ ብንለየ ጥበቃው ግን ሁሌም አብሮን ነው ። ልጅ በአባቱ ይመካል ፤ በእናቱም ይፅናናል ። አባትነቱ በፈጣሪነት ውስጥ ነውና ክብርን ክብር ላይ እየጨመረ እዚህ አድርሶናል ፤ ለዚህም አብቅቶናል ።

አዎ! በእርግጥም አምላክን ምን ይገልፀው ይሆን ? ፍቅር ነው መባሉ የፍቅርን ዋጋ ከማግዘፉ በላይ እርሱን አይወክለውም ፤ ፍፁም መባሉም የፍፁምነትን ዳርቻ ቢያሳይ እንጂ ብቻውን ሊገልፀው አይችልም ። መምከር ፣ ማስተማር ፣ መገሰፅ ሲያውቅበት ፣ በምህረቱ ብዛት እያስነባ ፣ በማያልቀው ይቅርታው እያስለቀሰ ፣ በማይገደበው ቸርነቱ ልብን እየሰረሰረ ዘልዓለማዊ ትምህርትን ያስተምራል ፤ እንከን አልባውን ምክር ይለግሳል፤ በቃሉ ብቻ ሰላምን ያድላል ፣ ፍቅርን ይሰጣል ፤ ፈውስን ይቸራል ። አውቀህ የምትጨርሰው ሳይሆን የሚውቅህ አምላክ አለህ ። እውቀቱም ፍፁም ነውና ሳትነግረው የሚያስፈልግህን ያውቀል ፤ ለዛም ከሌላው የተለየ መንገድን ሰጠህ ፣ በሚመጥንህ ልክ አጠነከረህ ፣ አስተማረህ ፣ ደገፈህ ። ምህረቱን እያሰብክ ቀና በል ፤ በይቅርታው ዳግም አንሰራራ ፤ በቸርነቱ በሚገባ ተማር ። "የማያልቀው በደሌን ፍፃሜ በሌለው ምህረትህ ሸፍንልኝ ፤ ዳግም እንዳልበድል ልቤንም መልስልኝ" በለው ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
1.7K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  00:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 04:54:06 የሚጠብቁህ ነፍሳት አሉ!

ባትኖር ባለመኖር ውስጥ ምንም የለምና የምታጣው ነገር አይኖርም ፤ ብዙዎች ግን ያጡሃል ፤ ብዙ ነገር ታጎድላለህ ፤ ብዙዎች ባንተ ምክንያት ይሰበራሉ ፤ አለም ካንተ የምታገኘውን ታጣለች ፤ ገፅታዋ ይቀየራል ፤ ድርሻህ ይጠፋል ። ይህም ጉድለት ብዙዎች ላይ ተፅዕኖ (impact) መፍጠር በቻልከው መጠን እየጨመረ ይሔዳል ። ካንተ በላይ በሰዎች ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖህ ስፍራህን ይወስናል ። ቀላል ህይወት አለ ፣ ከሃሳብ በላይ ለመኖርና ለመፈፀም የሚቀል በህይወት አላማ ውስጥ ሊጠቃለል የሚችል ህይወት ። ህይወትን ታግለህ አታሸንፍም ፤ በሙላት ነፃ ሆነህ ኖረሃት ግን እጅ ታሰጣታለህ ። አለም ላይ ተፅዕኖ የምትፈጥረው ተጨንቀህና ታመህ አይደለም ። የኔ የምትለውን የህይወት አላማ ማግኘት ከቻልክ ባትፈልግም ህይወትህ ቀላልና የተረጋጋ መሆኑ አይቀርም ። ምቾት የምትለውን ምህዳር በየትኛው ውጣውረድ ውስጥ ታገኘዋለህ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ልትደርስላቸው የሚባህ ፣ ካንተ እንጅ አስተዋፅዖ የሚፈልጉ ፣ ባንተ ደርጊት አምላካቸውን የሚያመሰግኑ ፣ በመኖርህ የሚደሰቱ ፣ ባንተ በኩል ህይታቸው የሚፈካ ብዙ የሚጠብቁህ ነፍሳት አሉ ። ለእራሴ ኖሬ አልፋለሁ አትበል ። ላንተ አንድ እንጀራ ትበቃሃልች ፤ ላንተ የተወሰነ ገቢ በቂህ ነው ። ነገር ግን የመኖርህ ትርጉም እርሱ አይደለም ፤ ወደ ምድር የመጣሀው ፣ በሰውነት የተፈጠርከው ለዚህ ብቻ አይደለም ። ካንተ በላይ ለሆነ ነገር እንደተፈጠርክ ማሰብ ጀምር፤ ኖሮ ከመሞት ለሚልቅ አላማ እንደመጣህ አስተውል ። በመኖር ውስጥ ብዙ ታውቃለህ ፣ ብዙ ትማራለህ ፣ ብዙ ታደርጋለህ ፣ እንዲሁም ታድጋለህ ። የስሜት እድገትህ ግን ልህቀትህን ይጨምራል ፤ አስተዋፅዖህን ያጎላል ፤ ተደራሽነትህን ያሰፋል ። ህይወት ለብቻ ሳይሆን በመደጋገፍ የምትመራ ፣ በመረዳዳት ስሜት የምትሰጥ ነች ።

አዎ! ማናችንም ትልቅ ዋጋ አለን ፤ ዋጋችንም አሳርፈን በምናልፈው አሻራ ልክ ይመዘናል ። ለእራስ ኖሮ ፣ በልቶ ጠጥቶ ፣ አግብቶ ወልዶ መኖር ለአንዳንዶቻችን ከባድ ሊመስል ይችላል ፣ ነገር ግን እርሱን ማድረግ የህይወታችን ግብ እንደሆነ ቆጥረን ለእርሱ ብቻ ስንሯሯጥ የድካም ጊዜያችን ላይ አንደርሳለን ። መኖር ከእራስ እርካታና ደስታ በላይ ነው ፤ ህይወት መጥቶ ከመሔድ የላቀ አላማ አላት ። የሚጠብቁህን ነፍሳት በፀጋህ ማገልገል ሳትችል ለእራስህም ሳትሆን ማለፍህ ሊያሳስብህ ይገባል ። በትንሽ መኖር ሳይሆን ለብዙዎች መትረፍን የህይወት ግብህ አድርግ ። እራስህን ብቻ ማስደሰትና ማሳረፍ ብቻ ሳይሆን የሚጠብቁህንም ማሳረፍ ፣ ማስደሰትና ማርካት እንዳለብህ አስተውል ። በመኖርህ ውስጥ አገልግሎትን ፣ በአገልግሎትህም ለብዙዎች መትረፍህን በተግባር አስመስክር ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.5K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  01:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 04:52:01 ትንሿንም ቁጠራት!

ቢያንስ እየሞከርክ ነው ፤ ቢያንስ የጥረት መንገድ ላይ ነህ ፤ ቢያንስ ጉዞ ጀምረሃል ፤ ቢያንስ ጥቂት ተራምደሃል ፤ በምትፈልገው መንገድ ላይ ተገኝተሃል ፤ አዋጩን ጎዳና ይዘሃል ። ተቀምጦ ብዙዎች ሲቀየሩና ተዓምር ሲሰሩ ከመመልከት በእራስ አቅምና ወኔ ልክ የቻሉትን መሞከር በጣም አስፈላጊ ነው ። ዛሬ ብትጀምር ሁሌም ጀማሪ ሆነህ አትቀጥልም ፤ ዛሬ በጥቂቱ ብትሞክር ሁሌም ጥቂት ብቻ አየፈፀምክ አትዘልቅም ። በሂደት የሚቀየሩ እጅግ ብዙ ነገሮ ይኖራሉ ። ተቀምጦ ከማየት ይልቅ ይብዛም ይነስም በትንሹ መንቀሳቀስ ይኖርብሃል ፤ ውጤት ያምጣም አያምጣም የተቻለህን ያክል መጣርህ የግድ ነው ። የመረጥከው አቅጣጫ መጨረሻህን እንደሚያሳምረው እርግጠኛ ሁን ፤ በትንሽ የተጀመረው ተግባርህ እያደር እንደሚያድግ እመን ፤ የተሰጠህለት ሙያህ እንደሚቀይርህ ተማመን ።

አዎ! ጀግናዬ..! ትንሿንም ቁጠራት! ጥቂቷን እንቅስቃሴህንም ዋጋ ስጣት ፤ ጥቂቶቹን እርምጃዎችህንም ከግምት ውስጥ አስገባቸው ፤ ትኩረት ስጣቸው ፤ ቦታ ስጣቸው ። የትኛውም ትልቅ ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው በአንድ ወቅት ጀማሪ ነበር ፤ ማንኛውም ዛሬ ተፅዕኖ ፈጣሪ የነበረ ሰው አንድ ሰሞን እንደ ማንኛው አዲስ ነገር ሞካሪ ሰው ከእራሱ ጋር ሲሟገት ፣ ፍረሃቱን ሲታገልና በተለያዩ ውጫዊና ውስጣዊ ጫናዎች ሲፈተን ነበር ። የከፍታው ሚስጥርም ነገሮችን በጅምር ከመተው በተሻለ በሂደት እያሳደጉ መምጣቱ ነው ። በህይወትህ ዋጋ የሌላቸው እንዲሁ ጊዜ ለማሳለፍና ዘና ለማለት ብቻ የሚደረጉ ድርጊቶች በበዙ ቁጥር ጊዜህን ከማጣትህ በላይ እራስህን እያጣህ ፣ በማንነትህ እያዘንክ ፣ እራስህን እየወቀስክና በበታችነት ስሜት እየተጎዳህ ትመጣለህ ።

አዎ! የየትኛውም እርምጃህ ትንሽነት አያሳስብህ ። መሮጥ ባትችል እየተራመድክ ነው ፤ መራመድ ባትችል እየተንቀሳቀስክ ነው ። ላለመቆምህና በምንም ሁኔታ ውስጥ ሆነህም እየተንቀሳቀስክ ስላለህ የብርታት ስሜት ይሰማህ ። ከምንም ትንሿ እንቅስቃሴ ትሻላለች ፤ ደጋጋሞ የሃሳብ ጅረት ውስጥ ከመገኘት በጥቂቱ ያሰቡትን መኖር እረፍትን ይሰጣት ፤ ውጤትንም ያመጣል ። ትናንሾቹን ስራዎችህን ንቀህ፣ ጅማሬህን ዋጋ አሳጥተህ ከፍታ የምትለው ስፍራ ላይ መድረስ አትችልም ። በእጅህ ላይ ያሉ ግብአቶችህን በንቃት ተጠቀም ፤ የሰው እጅ አትጠብቅ ፤ ውስጣዊ ድምፅህን አዳምጥ ፤ ጅማሬህን አክብር ፤ ለትናንሾቹ እንቅስቃሴዎችህ ዋጋ ስጣቸው ። ያከበርከው ፣ ጋዜና ትኩረት የሰጠሀው ትንሹ ተግባርህ እንደሚያሳድግህ እመን ። በትንሽ ጀምር ፣ በሒደት እደግ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
2.4K viewsምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ, edited  01:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ