Get Mystery Box with random crypto!

በፍቅር እደግ! የህይወት ክህሎት አሰልጣኙ ማይክ ፊልድስ (J. Mike Fields) ለፍቅር ያለን | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

በፍቅር እደግ!

የህይወት ክህሎት አሰልጣኙ ማይክ ፊልድስ (J. Mike Fields) ለፍቅር ያለንን አረዳድ በዚህ እንድናድሰው ያስገነዝበናል። " በፍቅር እደግ እንጂ በፍቅር አትውደቅ። " ፍቅርን ለለውጥ፣ ለእድገትና ለብልፅግና መጠቀም ከተቻለ በፍቅር ውስጥ የሚፈጠሩት አለመግባባትና መጎዳዳት እየከሰሙ ይመጣሉ፤ ችግሮች ቢኖሩም ትኩረቶች ሁሉ ወደ መፍትሔዎች ይዞራሉ፤ ክፍተቶች ቢፈጠሩም በተገቢው ጊዜ እልባትን ያገኛሉ። ፍቅር የሚጥል ሳይሆን የሚያነሳ፣ ነፍስን የሚዘራ፣ ማንነትን የሚያሻሽልና ወደ ተሻለው መዳረሻ የሚያደርስ ነው። የፍቅር አይነቶች ቢለያዩም ዋናው አላማቸው ግን አዎንታዊውን ስሜት በማስረፅ የተረጋጋና አስደሳች ህይወት መፍጠር ነው። እውነተኛ ፍቅር ሁሌም ነፍስ አለው፤ ሊለካ የማይችል፣ ሚዛን የሌለው ጥልቅ ስሜት አለው።

አዎ! ጀግናዬ..! በፍቅር እደግ፤ በመልካም ሃሳብ ከፍ በል፤ በቅን ልቦና፣ በደግ ሃሰብና በጥበብ ከፍ በል። ሰው ሁሉ ታላቁ ሃይል የተባለውን ፍቅር ቢመርጥና በእርሱ መንገድ ቢመላለስ የአለም ገፅ ምነኛ በተቀየረ ነበር። አንተ መልካም ብታስብ የሚተናኮልህ፣ የሚከፋብህ አይጠፋም፤ ተንኮሉንም ሆነ ክፋቱን የምታሸንፈው ግን በበዛው መልካምነትህ ብቻ ነው። የፍቅርን አሸናፊነት ከቃል በላይ ልትኖረው ይገባል፤ ሰዎችን በበጎነት መግዛት እንደሚቻል ማረጋገጥ ይጠበቅብሃል። የምር ፍቅርን እየኖርከው እንደሆና በውስጡም እያደክ እንደሆነ እራስህን ጠይቅ። በቅድሚያ የሚያሳድግህ የፍቅር አይነት ለእራስህ ያለህ ልባዊ ፍቅርና ክብር ነው። እንዲደረግልህ የምትፈልገውን ምንያክል ለእራስህ ታደርጋለህ? የምትመርጠውን ማንነት ምንያክል በውጥህ ፈጥረሀዋል?

አዎ! ለእራስህ ያለህ ፍቅር ባደገ ልክ የምታድገው አንተና በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ናቸው። ለማንኛውም ሰው ያለህ ክብርና ቦታ ይቀየራል፤ ግንኙነቶችህ ጤናማና የተረጋጉ ይሆናሉ፤ ህልምህን ለመኖር አትቸገርም፤ ራዕይህን ለማሳካት የሚያግዝህን ከባቢ በቀላሉ ትፈጥራለህ። ፍቅርን እንደ ትልቁ የአላማህ ማስፈፀሚያ ግበዓት ተጠቀመው። ፍቅር የማይዘው አዎንታዊ እሳቤ የለም። አብሮነት፣ መረዳዳት፣ መግባባት፣ ለውጥ፣ እድገት፣ መልካም ውጤትና ስኬት በሙሉ ከፍቅር ምንጭ የሚቀዱ ናቸው። ለሙያህ ያለህ ፍቅር ሙያህን ያሳድግልሃል፤ ለፍቅር አጋርህ ያለህ ንፁህ ፍቅር ብርታትና ስኬታማ ህይወትን ያጎናፅፍሃል፤ በዙሪያህ ላሉ ለቤተሰቦችህ፣ ለጓደኞችህና ለወዳጆችህ ያለህ ፍቅር ደስተኛ፣ ሰላማዊና አመስጋኝ ያደርግሃል። ፍቅርን በመኖር በፍቅር እደግ፤ ለስኬትህም እንደ ግበዓት ተጠቀመው፤ ወዳስቀመጥከው መዳረሻም ተሸጋገርበት።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q